ትዝብት: ወያኔና ሰሞንኛ እንቅስቃሴው

ከይኸነው አንተሁነኝ
08/ 12/ 2012
1. ውሃ ቅዳ ውሃ መለስ ወያኔና ሰሞንኛ እንቅስቃሴው

በወያኔ ውስጥ ስልጣን የዛፍ ላይ እንቅልፍ ነው ብሎ ነበር አሉ ባለ ራዕዩ የወያኔው መሪ። ባለስልጣኖች በስልጣናቸው ቢባልጉ በወያኔ መንደር በታወቀው የግምገማ ጁዶ አማካኝነት እንዘርራቸዋለን ለማለት ይመስላል የባለራዕዩ ጎጠኛው መለስ ንግግር። የሚደንቀውና ይህን ጉዳይ አሳሳቢ የሚያደርገው ግን ልክ አሁን በወያኔ መንድር እንደሚታየው ባለጌው ከጨዋው አጅግ በዝቶ በሚታይበት ጊዜ ምን ይደረጋል የሚለው ነው። ሙሰኛው ከሀቀኛው፣ ልግመኛው ከሰራተኛው፣ አስመሳዩ ከደህነኛው በተለይም መሪው ከተመሪው በዝቶ እጅግም ገዝፎ በሚታይበት ጊዜ እራስን ፈጽሞ ከመለወጥ የተሻለ አዋጭ ዘዴ በወያኔ መንደር ምን ይሆን? ለዚህም ቢሆን ግን ሁሉ በእጁ ሁሉ በደጁ የሆነው ወያኔ መላ ያጣ አይመስልም፤ የወያኔ የግምገማ ወንፊት ለወያኔዎች ተቃርኖ የሌላት (woyane friendly) ናትና። ድሮም ቢሆን በወያኔ ውስጥ ግምገማ ምልክት ማሳያ አቅጣጫ ጠቋሚና መስመር ሰጭ እንጅ ቀጭ አልነበረችም ሆናም አታውቅም የወያኔ ተፈጥሮ ለዚህ የተመቻቸ ስላልሆነ።

Read more in PDF

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on December 8, 2012. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.