ትናንት ተቃውሞ አድርጋችኋል ተብለው የታሰሩ ሙስሊሞች ከፊሎቹ ዛሬ ፍ/ቤት ቀረቡ!

(ኢ.ኤም.ኤፍ) በትላንትናው እለት አዲስ አበባ ላይ፤ አክራሪዎችን ለመቃወም በሚል ሽፋን ሰላማዊ ሰልፍ መደረጉ ይታወሳል። ይህ ሰልፍ ከጅምሩ የተጠራው ህዝቡን ቤት ለቤት እንዲወጣ ግዳጅ ጭምር ተደርጎበት መሆኑን የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ይመሰክራሉ። በግዳጅ ከወጡት ውጪ ያሉት የኢህአዴግ ደጋፊዎች ደግሞ የኢትዮጵያ 200 ብር እንደተከፈላቸው ተገልጿል። በዚህ መሃል “ድምጻችን ይሰማ” የተባለው አስተባባሪ አካል ባደረገው ጥሪ መሰረት፤ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ኢህአዴግ በጠራው  ስብሰባ ላይ ደጋፊዎቹ ተገኝተው፤ ተቃውሟቸውን እንዲያሰሙ ተጠይቆ ነበር። በርግጥ ህዝበ ሙስሊሙ በኢህአዴግ ሰልፍ ላይ እንዲገኝ ጥሪ ማቅረብ ማለት፤ “በሬ ካራጁ ይውላል።” እንደማለት ነው ሲሉ ነበር። ሆኖም የተጠራው ጥሪ ተጠርቶ ሙስሊም ወገኖች አንዳንዶቹ ወደ መስቀል አደባባይ እንዳይሄዱ ገና ከመንደራቸው ሲታገዱ፤ ሌሎች እንደምንም መስቀል አደባባይ የተገኙት ደግሞ እየታፈኑ፤ በአውቶቡስ እየተጫኑ ወዳልታወቀ ስፍራ ተወስደው ነበር። ዛሬ “ድምጻችን ይሰማ” ባደረሰን ዘገባ መሰረት፤ ታሳሪዎቹ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተገልጿል።( የዜናውን ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)

arrest3

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on September 2, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.