ቴዲ አፍሮ ወንድ ልጅ አገኘ፤ ስሙንም ሚካኤል አለው!

(EMF) ዛሬ ኤፕሪል 6 ቀን፣ 2013 ዓ.ም. ወንድ ልጅ አግኝቷል። ሴፕቴምበር 27፣ 2012 አምለሰት ሙጬን በሰርግ ያገባው ቴዲ አፍሮ የመጀመሪያ ልጁን ስም ሚካኤል ብሎታል። በፎቶው ላይ አምለሰት ሙጬ ልጇን በሰላም እንደተገላገለች በነርሷ እየተረዳች ይታያል። በሁለተኛው ፎቶ ላይ ቴዲ አፍሮ ዛሬ የተወለደ ልጁን አቅፎ ይታያል። የሚገርመው ነገር ቴዲ አፍሮ አምለሰትን ከማወቁ እና ከማግባቱ አመታት በፊት ጀምሮ ወንድ ልጅ ካገኘ ስሙን “ሚካኤል” እንደሚለው ደጋግሞ ይናገር ነበር። አሁንም እንደተመኘው ወንድ ልጅ አግኝቶ ስሙን ሚካኤል ብሎታል። በዚህ አጋጣሚ ኢ.ኤም.ኤፍ.  አምለሰትን “እንኳን ማርያም ማረችሽ! ማርያም በሽልም ታውጣሽ!” ሲል፤ ቴዲንም “እንኳን ደስ ያለህ!” እንላለን።

አምለሰት ሙጬ ልጇን በሰላም እንደተገላገለች በነርሷ እየተረዳች

አምለሰት ሙጬ ልጇን በሰላም እንደተገላገለች በነርሷ እየተረዳች

 

ቴዲ አፍሮ ወንድ ልጁን አቅፎ

ቴዲ አፍሮ ወንድ ልጁን አቅፎ

 

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on April 6, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to ቴዲ አፍሮ ወንድ ልጅ አገኘ፤ ስሙንም ሚካኤል አለው!

 1. Abiy Ethiopiawi+Segawi/wemenfesawi+አቢይ+ኢትዮጵያዊ+ሥጋዊ-ወመንፈሳዊ

  April 7, 2013 at 6:36 PM

  ****ዘሚካኤል መጥቷል!!!****
  ቴዎድሮስ የምወድህ ሙያህን አክባሪ:-
  የፍቅር አርዓያ አግዚአብሔርን ፈሪ::
  ቤተሰብ ለማፍራት እንዲያ እንደጀመርከው:-
  እንዲህ በአብራክህ ቤትህን ይባርከው::
  ሲባርከው ደግሞ አትጣ ምቀኛ:-
  በሙያህ እንድትነቃ ቆመህ እንዳ’ተኛ::
  እንኳን ደስ አላችሁ አንተና አምለሰት:-
  ዘሚካኤል መጥቷል:-
  ሁሉም ሰው ይደሰት::

  ለቴዎድሮስ ዘሚካኤል