ለቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ከ100ሺህ በላይ ህዝብ በስታዲየም

tedy_concert_20091.jpg

አውራምባ ታይምስ (አዲስ አበባ)፡- ከእስር ከተለቀቀ በኋላ የመጀመሪያው የሆነውና ዛሬ ምሽት ከ12፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚካሄደውን የድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ኮንሰርት ለመታደም ከአዲስ አበባና ከመላው አገሪቱ የተሰባሰበ በመቶ ሺህ የሚቆጠር ህዝብ ከንጋት አንስቶ በአዲስ አበባ ስታዲየም ዙሪያ ተጥለቅልቋል፡፡

በሺህ የሚቆጠሩ የቴዲ አፍሮ አድናቂዎች ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ የኮንሰርቱን ትኬት ለማግኘት ብዙ ጥረት ቢያደርጉም አውራምባ ታይምስ ያነጋገራቸው የኮንሰርቱ የፕሮሞሽን ኃላፊ አቶ ምትኩ ግርማ ግን ‹ትኬት አስቀድመን አንሸጥም የትኬት ሽያጩ የሚከናወነው ኮንሰርቱ በሚካሄድበት ዕለት በስታዲየም ነው ይህ የሆነበት ምክንያት ደግሞ ትኬቱ በህገወጥ መንገድ ዋጋው እንዳያሻቅብ ነው› ማለታቸው ይታወሳል፡፡ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከጧት ጀምሮ ከባድ ዝናብ እየጣለ ቢሆንም በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የኮንሰርቱ ታዳሚዎች ግን ለዝናቡ ቦታ ሳይሰጡ በኢትዮጵያ ባንዲራ እንዲሁም የቴዲን ምስል በያዙ ቲሸርቶችና ኮፊያዎች ደምቀው በረጃጅም ሰልፎች እየተጠባበቁ ነው፡፡

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on October 12, 2009. Filed under NEWS. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.