“ቴዲ አፍሮ ከስንት አንድ ጊዜ ብቅ የሚል ውብ ጀምበር ነው ” ውብሸት ወርቅአለማሁ “የተረሱትንም አስታዋሽ ትየባ በዘላለም ገብሬ

(ዘላለም ገብሬ) በቅርቡ አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ እና በዘሃበሻ ድህረ ገፅ ላይ በቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የሙዚቃ ስራ ላይ ያቀረበው ሚዛን ያልደፋ ሃተታ በጥንቃቄ አንብቤዋለሁ አዲስ አድማስ ምን ነካው? የሚልም ስሜት ተሰምቶኛል ምክንያቱም ምን አንደሆነ ባላውቅም ፀሃፊ አጥቶ ይሆናል ከሚል ድምዳሜ ላይ ለመድረስ እስከ መብቃት ድረስ በቅቻለሁ ፡፡ በእውነቱ ቴዎድሮስ አፍሮ በቅርቡ ከሚያሳትመው አልበሙ በተወሰነ ደረጃ ለማድመጥ አድሉ ገጥሞኝ ለማድመጥ ችያለሁ የተወሰኑትም በሰዎች ተሰርቀውበት በተለያዩ የሶሽያል ኔትዎርክ አና የሙዚቃ መረብ ውስጥ በህገወጥ ተሰራጭተው ለማድመጥም ተገደናል ፡፡

በአርግጥም ቴዲ ኣፍሮ እንዴት አና በምን ሁኔታ ሙዚቃዎቹ አንደተሰረቁበት በውል ባያውቀውም በቅርብ ጊዜ ያወጣዋል ተበሎ በብዙ መገናኛ ብዙሃን ተወርቶለት የነበረው የዚህ አልበም ስራ አንደገና በቅርቡ በተሰረቁት አራት ሙዚቃዎች የተነሳ ሙዚቃውን ለማወጣት አንዳልቻለ አና ሊያራዝመው አንደሚፈልግ ከውስጥ ኣዋቂ ምንጮችም ሲወራ መስማቴ እኔንም ሆነ ሌሎቹን አድማጮች ሊያስገርም አና ሊያስደንቅ እንደሚችል ነው ፡፡ ምክንያቱም አድማስ ላይ አንደተጫረው የሰውን ልብ ለመስቀል አና የገበያውን ሁኔታ ከፍ ለማድረግ የሚያደርገው ጥረት ነው የሚል አሳቤ በሰው ልብ ውስጥ አንዲፀነስ ማድረጉ ሊሆን ይችላል ግን እውነታው ይህ ሳይሆን የሰውን መብት አና የስራውን ክብር ካለመስጠት የሚደረገው ህገ መንግስታዊ ጥሰት አና የኮፒ ራይት ህግን አለማክበር በሃገራችን የሚደረገው ትልቁ የፈጠራ ስራን በራስ ፈቃደኝነት በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃኖች ማሰራጨት ትልቁን የኪነጥበብ ስራዎች ወደ ማቅጨጭ መድረሱ አንደሆነ ሊታወቅ በተገባ ነበር::

በእውነቱ የኢትዮጵያ የሙዚቃ ባለሙያዎችን ከተመለከትን እነማን ናቸው የራሳቸውን ሙዚቃ ብቻ በመስራት የታወቁት በደረጃ ብናወጣ ማንንም ከቦታው ልናገኝ አንደማንችል የታወቀ ነው ፡፡ ይህ ከሆነ ዘንድ ታዲያ የቴዲ ኣፍሮ በትር ለምን ሊበዛበት ቻለ ብለን አስኪ አራስችንን አንጠይቅ ፡፡እኔ ቴዲ ኣፍሮን በተወሰነ መልኩ አንደማውቀው ከሆነ አና አንደ ኪነጥበብ ባለሙያነቱ በጣም ብዙ ታላላቅ ስራዎችን ሰርቶኣል አስኪ አንደ አነ አብዱ ኪያር የየማነ ባሪያን ዘፈን መርካቶ ሰፈሬን ሲሰራ , ጎሳዬ ከጠላሽኝ ወዲያ የኣብርሃም ኣፈውርቂኝን ሲዘፍን ,የጌታቸው ካሳ ዘፈን ሲዘፈን አስቴር አወቀ ሙናዬን ሙናዬን የኩኩ ሰብስቤን ሰርቃ ዘፈን ስታወጣ ማን ነው ተው ያላቸው በአርግጥ የስራ ፈጠራ ከተሰራ አና በህጋዊ መንገድ ከወጣ በሁዋላ የህዝብ ነው አየተባለ በሃገራችን የሚሳለቅበት ሁኔታ ነው ቢሆንም ግን ባለ መብቱ ሃላፊነት አስኪጎድለው ድረስ ማሳጣት ሳይሆን በክብር ስራዎቹን ለታሪክ ማብቃት ሲቻል ብቻ ነው ፡፡ኣለመታደል ሆኖ የኢትዮጵያን የታሪክ መዛግብት ግን በክብር የሚቀመጡ ሳይሆኑ ለስም ብቻ እንዳሉ ተደርጎ የገንዘብ ማግኛ ችብቸባ የሚካሄድባቸው አቍራጭ ጎዳናዎች ሞሆናቸው ግልፅ ነው ይህ ዘረፋ በሃገራችን መካሄድ ከጀመረ ጊዜው አና ወቅቱ በውል ባይታወቅም በታሪክ መዛግብቶች ተትብዮ አንዳየሁት ከሆነ አንግሊዝ ደርቡሾች አና ጣሊያኖች በከፍተኛ ደረጃ ታላላቅ መዛግብቶችን መዝረፋቸው ይታወቃል ፡፡

ይህ ማለት የታሪክ አሻራችን ከየት ይጀምራል የሚለውን ለማወቅ እስኪያቅተን ድረስ የሃገራችንን መሰረታዊ ሂደት አንዴት አንደሆነ ለማወቅ ታግተን ኖረናል፡፡መቼም ቢሆን ምነው መሰመሩን ጣስክ ብላችሁ አንዳትሉኝ ወደ ዋናው ምእራፍ ላምራ እና ,ቴዲ ኣፍሮ ከሚሰራቸው ስራዎች መወደድ ምክንያት ባሻገር በመላው ኢትዮጵያዊ አና ኤርትራውያን ዜጎች ከፍተኛ ተወዳጅነትን ኣግኝቶኣል ለምን ተብሎ ቢባል ለሰላም ማቀንቀኑ አና የኢትዮጵያን አና የኤርትራን ኣንድነት ክልቡ መመኘቱ ሊሆን ይችላል ያም ብቻ ሳይሆን በሃገራችን ያለውን የዘር ክፍፍል በቃ አንድንለው በሙዚቃ ስራ ውስጥ የተላከ መሲህ ነው የሚል አሳቤ በሰዎች ላይ ተፈጥሮ ኢትዮጵያዊው ቦብ ማርሌይ ሲሉም አወድሰውታል፡፡ ባለፈው ሁለት አመታት በወያኔ እጅ ላይ ወድቆ በእስር ላይ በነበረብት ወቅት አኔ በምገኝበት ከተማ የሚገኝ ቺካጎ ፐብሊክ ሬዲዮ( የቺካጎ ብሄራዊ ሬዲዮ)ትልቅ የሬዲዮ ጣቢያ ስለ ቴዲ ሲተነትን አንደሰማሁት ከሆነ አኛ ለእሱ ከሰጠነው በላይ ክብር አና ስም መለገሳቸው የስራውን ጠሊቅነት አንደገና ልመረምር በቅቻለሁ አነሱም ከሙዚቃው ከፍተኛነት እና ሙዚቃዊ ቃና ብስለት መልእክቱን ስሜታዊነት በሚገባ ተረድተውታል ብዬ በሙሉ ልቤ አምኜ ተቀብዬዋለሁ ፡፡

በእውነቱ ቴዲ አፍሮ አንደ አነ አስቴር ኣወቀ ለገበያ ሽሚያ በየአመቱ ስቱዲዮ ቆሙ ሙዚቃ ቀርፆ ለህዝብ የሚያቀርብ ሳይሆን ለህዝብ የቱ ይገባዋል ብሎ መጠኑን ለክቶ አውጥቶ አና አውርዶ ኣንድ አና ሁለት ጊዜ ሳይሆን ለኣንድ ነጠላ ዜማ አስከ ስድስት አና ሰባት ጊዜ በጭንቀት ስቱዲዮ ገብቶ ቀረፃ የሚያደርግ ሲሆን ከዚያ በፊት ግን እቤቱ ውስጥ ባለችው ትንሽ ስቱዲዮ እራሱን በራሱ አጥንቶ አና ፈትሾ የሚገባ አና ለሙዚቃ ስራው የሚጠበብ ሲሆን ከፍተኛ ጊዜውንም ለዚሁ ስራ ብቻ የሚያውል የሙዚቃ ጠቢብ ነው ፡፡ በሌላም በኩል እንመልከት ከተባለ በአሁን ሰአት በሙሉ ባንድ መስራት እንደ ፋርነት በተቆጠረበት እና በኪቦድር ብቻ እየተሰራ ሙዚቃዊ ቃናው በጠፋበት ስራ የሙዚቃ ከተፋ ለገንዘብ መሰብሰቢያ በዋለበት ወቅት ይህ የሙዚቃ ሰው ተጀምሮ አስከሚጨረስ በሙሉ ባንድ ስራውን የሚያከናውን ታላቅ ሰው መሆኑን ልንገነዘብ እንችላለን ፡፡የቀድሞዎቹ ወይንም አንጋፋዎቹ እየተባሉ ከሚጠሩት አንዱ የሆነውን ማህሙድ አህመድ እንኵን ከሙሉ ባንድ ይልቅ በኪቦርድ ብቻ መስራትን በመረጠበት ዘመን ቴዲ አፍሮ ግን የስራውን ክብር ለማሳየትም ሆነ የእራሱን የስራ ይዘቶች እንዳይወርዱበት ለማድረግ ከነሙሉ ባንዶቹ አለም አቀፍ ኮንሰርቶችን ለማቅረብ መብቃቱ ለሙያው ሟች መሆኑን ያሳያል፡፡

ለዚህም እራሱ መረጃ ነው ይህም ብቻም ኣይደለም በቅርቡ በአትላንታ አና በዲሲ ኣካባቢዎች ያደረጋቸው የኮንሰርት ክፍያዎቹ የስራዎቹን ታላቅነት ሊያሳዩን ይችላሉ የሚለውን እምነቴን የበለጠ ያጠነክርልኛል ማንም ሰው በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከ15,000 USA DOLLARS በላይ የተከፈለው ማንም የሙዚቃ ሰው የለም ማንም ይህንንም የክፍያ ጣሪያ የነካ የለም ነገር ግን ቴዲ አፍሮ የዚህን ሶስት አና አራት እጥፍ ለመድረስ የበቃው የስራውን ብስለት ,የአድማጩ ብዛት ከእለት ወደ እለት እያየለ መምጣቱ ፍቅርን የሚሰብክ መሲህ መሆኑን የተረዳ ሁሉ አሱን የፍቅር አማልክት ብለው ይከተሉታል ፡፡የቴዎድሮስን ስራዎች በትንሹ ቀንጨብጨብ አናድርግ አና ስራዎቹን በትንሹ እናወድስ እና የሚሰራቸውንም ስራዎች በጥልቀት እንመልከታቸው፡፡ እድሉንም ካገኘን የስራዎቹን ሂደቶች ሙዚቃውን እየሰማን ቢሆን ሊመረጥ ይችላል ፡፡

በተለይም ታላላቅ ሰዎች የምንላቸው የሃገራችን ሰዎች ስለ ቴዲ ኣፍሮ ከተናገሩት ቀንጨብ አያደረገን ሰራዎቹንም ማየቱ ሚዛናዊ ሊሆን ይችላል እና በቅድሚያ የእውቁ እና አንጋፋው ድምፃዊ ዶ/ር ጥላሁን ገሰሰ በኣንድ ወቅት በአርቲስት ኣዳነች ወልደ ገብርኤል የህትመት ድርጅት አዲ ፕሮሞሽን እየታተመ በሚቀርበው ጠብታ በተሰኘው መፅሄት በቅፅ 2 ቁጥር 14 ህዳር 2000 ኣመተ ምህረት ላይ ሰለ ቴዲ አፍሮ ተጠይቆ ካቀረበው ጥቂቱን እንውሰድ “ልጁ እንደተመለከትኩት የእድሜ ማነስ ሳይሆን ቁምነገር ያለው ተግባር ለመፈፀም አንደሚችል አውቃለሁ ፡፡በድምፁም ሆነ በስራው አደንቀዋለሁ፡፡ ሊሰራ የፈለጋቸውን ነገሮች ሁሉ አስቦ በራሱ ዜማ አና በራሱ ግጥም በራሱ ድምፅ ኣገናኝቶ መስራት የሚችል ብቁ ኣርቲስት ነው ማለት እችላለሁ፡፡ የአቴንስ ኦሎምፒክን አስመልክቶ ሰለ እነ ቀነኒሳ አና ሃይሌ ገ/ስላሴ የሰራውን ዘፈን ለመጀመሪያ ጊዜ ስመለከት በእውነት እዛው አቴንስ ድረስ ሄዶ ውድድሩን ተመልክቶ የሰራው እንጂ እንደማንችንም በቴሌቪዥን አይቶ ያቀረበው አልመሰለኝም ፡፡ለሃይሌ ገ/ስላሴም የሰራው ቀላል አይደለም ፡፡ትልቅ አርማ ነው ነው ፡፡ለሙያው ከማንም በተሻለ መልኩ ለኢትዮጵያ አትሌቶች ትልቅ ማስታወሻ ሰርቶአል ፡፡ ቴዲ ቁምነገር ከመስራቱም ሌላ ራሱን የሚጠብቅ ያልሆነ ቦታ የማይገኝ የሚውልበትን ቦታ ጠንቅቆ የሚያውቅ በመሆኑ አኮራበታለሁ ፡፡” ሲል አወድሶታል! በሌላም በኩል የማስታወቂያ ስራ ባለሙያ የሆነው አንጋፋው ውብሸት ወርቃለማሁ በበኩሉ “ሰለ እሱ ለመግለፅ በቂ ሃይል ያለው ቃል የሚገኝ አይመስለኝም ልጁ አኮ ከስንት አንድ ጊዜ ብቅ የሚል ውብ ጀምበር ነው ፡፡ባቀረባቸው አራት ምርጥ መታሰቢያ ስራዎች ለሃይሌ ,፡ግርማዊነታቸው፡ ለቀነኒሳ እና ለቦብ ማርሌይ በዘፈናቸው ስራዎች አንዳከብረው አድርጎኛል ፡፡

ዘፈኖቹ አጥንት ሰብረው ይገባሉ ፡፡አእምሮው ከዘፈነላቸው ሯጮች በላይ አንደሚፈጥን ይሰማኛል፡፡ ….በመጨረሻም ዘር ቆጥሬ ዘውድ ብጭን አና ቢዘፍንልኝ አልጠላም” ብለው አድናቆታቸውን ቸረውታል ፡፡በሌላም በኩል የዘፈን ግጥም ደራሲው ይልማ ገብረ አብ በበኩሉ የውስጥ ፍላጎቱን መግለፅ በሚችልበት አቅሙ ለመግለፅ ቢሞክርም ጭራሹን ቃላቶች ያጣ በሚመስል አንደበቱ አንዲህ ብሎት አክብሮቱን አስፍሮአል “የህዝቡን የልብ ትርታን ማድመጡን አደንቀዋለሁ ማሞገስ ሳይሆን አሱን መግለፅ ስለምፈልግ ነው ይህንን የምናገረው” ሲል ቀጠል ኣድርጎም “የጥሩ ስልት ባለቤት ነው በአራረቡም መድረክ ያሳምራል ስለሙያው ትንሽ ተነግሮ ብዙ የሚሰሙት ነው፡፡ ህይወቱን በአድሉ ኖረባት ወይስ ለአድሉ ሰጣት? ለሚለው ትክክለኛ መልስ ለማግኘት ቴዲን መቃኘት ያስፈልጋል ::አንደ አኔ ምልከታ የሙያን ጥሙን ለመወጣት ሲል ህይወቱን ለእድሉ ሰጥቶኣል ፡፡በእድሉ ሰራበት እንጂ አልኖረባትም ፡፡”በማለት የልቡን ስሜት ለመግለፅ ተገዶአል ፡፡በእርግጥም ስለ ቴዲ አፍሮ አንዲህ ተወርቶ አና ተነክቶ የማያልቅ ታሪክ መዳሰሱ ድፍረት ይሆናል ፡ ከቴዲ አፍሮ ባሻገርም ብዙ ሰዎች የስራ ፈጠራቸውን በተለያዩ አጋጣሚ አና ክስተቶችን በመጠቀም የፈጥእራ ችሎታዎቻቸውን ያስመዘኑበት አና አለምን ያስደነቁበት ወቅት አለ ግን ያ ማለት ሁል ጊዜ በሙዚቃ ህይወት ውስጥ ያለውን ሰው ሁሉ ይገጥማል ማለት አይደለም ለማድረግም ትልቅ ብቃት አና ጥረትንም ይጠይቃል እንደ አብነት ማንሳት ከቻልን ተወዳጁ የ ሮክ አቀንቃኝ ኤልቪስ ፕሪስ የህይወት አልፈት ወቅት ይህ ክስተት ሆኖኣል ፡ የልእልት ዲያናም ድንገተኛ አና አሰቃቂ ሞት አስገራሚ ክስተትን ፈጥሮአል በሌላም ታዋቂ አና የአለም ፈርጥ የሆነችው ተወዳጇ ተዋናይ ማርሊን ሞንሮ ራሷን ማጥፋት ተከትሎ አስደናቂ የሆኑ ክንውኖች ተፈጥረዋል ፡፡ብቃት ያላቸው አቀንቃኞች ብቃታቸውን ብቻም ሳይሆን የሙያዊ ብስለታቸውን ለአለም አስተጋብተውበታል ቴዎድሮስ አፍሮም ይህንን ተጋርቶታል ,ታዲያ ቴዎድሮስ ካሳሁን ከአነዚህ ክስተቶች ውስጥ ለየት የሚያደርገው በአንድ ዘፈን ብቻ ተገድቦ ስራውን ያቀርበ ሳይሆን በተደጋጋሚ ታሪክ ቀመስ የሆኑትንም ሆነ አስገራሚ ክስተቶችን አንዲሁም ለሰው ያልታዩ ግን ግርምትን ሊፈጥሩ የሚችሉ ነገሮችን አንስቶ ጥሎ ለህዝብ ጆሮ ሲያቀርባቸው አንቱታን ሊያስቸሩት በቅተዋል ይህ ልጅ ሊያድግ ብቻም አይደለም ይመነደጋል ብቃቱም አንደ ጠሊቅ የብርሃን ጨረር ይፈነጥቃል አንጂ ይጨልማል የሚል ማንም ሰው የለም አይኖርምም ፡፡

ቴዲ አፍሮ ከሰራቸው ስራዎች መካከል ቀነኒሳ (አልሆንልህ አለኝ ) (ሞናሊዛ ) (ግርማዊነትዎ) (ገብረስላሴ) (ሻሸመኔ) (በአስራ ሰባት መርፌ ) (ካብ ዳህላክ ) ከቅርቦቹ ከሰራቸው አና በኣዲሱ ኣልበም ውስጥ ከሚካተቱት ስራዎች ደግሞ (ፊዮሪና) ( ፅዮን ሙሽራዬ ) (ቼ በለው )ከተመለከትን ሁነቶችን አና ሂደቶችን ከላይ የጠቀስኵቸው ሂደቶችን የሚፈጥሩትን መሰረታዊ ውጥናቸውን ብቻ ብንመለከተው ይህ ሰው ከየትኛው አለም የተፈጠረ ሰው ነው ያሰኛል ፡፡ በእርግጠኝነት አዲስ ከሚያወጣው አልበም ውስጥ “ቼ በለው”ን ብናደምጥ የህዝብ ዘፈን አንደመሆኑ መጠን አሁንም የሰው ዘፈን ዘረፈ ከማለት አንደበታችን አንደማይታሰር ይገባኛል በአርግጠኝነት የማውቀው ይህ ዘፈን የህዝብ ዘፈን ነው ከጥንት ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ በጦር አውድማ ላይ የጦር ጃንደረባዎች እና ጋሻጃግሬዎች ሲፎክሩ ፡ሲሸልሉ ኖረውበት ፡ የተላለፈ ትልቅ ዜማዊ ቅርስ ነው ማንም ሰው ሊሰራበት የሚችል የህዝብ ዜማ መሆኑ አርግጥ ነው ፡፡ ታዲያ ኣሁንም ቴዲ ይህንንም ዘፈን አና ዜማ ሰረቀ ብለን ልንለው እንችላለን ? ስለ እውነት መነጋገር ከቻልን አንደቢራቢሮ ለዘመናት ያክል ከኢትዮጵያ የሙዚቃ ደረጃ ላይ ጠፍቶ መደመጥን ካቆምንበት ዘመናትን ተቆጥረው ባለበት ወቅት ድንገት ይህ ወጣት አንደገና በአዲስ መልክ በመስራት ወደ ሙዚቃ ደረጃ አንዲሰማ አድርጎታል። በሌላም በኩል ያየነው የዘፈነው ዘፋን ማንነቱም በማይታወቅበት ሁኔታ በነበረበት ሰኣት አና በተረሳበት ወቅት እንደገና ማንነቱን እዲታወቅ ረድቶታል ፡፡ይህም ትልቅ ችሎታ አና ብቃቱ አንደሆነ ማንም የሚያውቀው አና አሌ ሊባል የማይችለው ሃቅ ነው ፡፡በቀጣይም የምናነሳው ፊዮሪናንም ብናነሳ አይደለም በኢትዮጵያኖች ዘንድ በራሳቸው በኤርትራውያንም ዘንድ አስከነ መፈጠሩ የተረሳ ሲሆን ከእዚህ አለም በሞት ከተለየበት ጊዜ ጀምሮ ዘፈኖቹ ለሰሚ ጆሮ አጥቶ የነበረ የጥንት ድንቅ ሙዚቃ የነበረ ሲሆን ዛሬም ቴዲ በድጋሚ ወደ ህላ መለስ ብለን የቀድሞዎቹን ስራዎች እንድንዳስስ እረድቶናል ፡፡ ከቴዲ ድንቅ ስራዎች ውስጥ በኢትዮጵያ ውስጥ ስለ ኣለው ወቅታዊ ጉዳይም ሆነ በሌሎችም አሳቤዎች ላይ ላነሳቸው ጠቅላላ ሃሳብን ተመልክቶ ብዙ ሊባልላቸው የሚገቡ ነግሮች አንዳሉ ከግንዛቤ ማስገባት ይቻላል ፡፡ አንደምሳሌም ፍቅር ያሸንፋል የሚለው ልዩ ቃሉ በሙዚቃ ቃናው በግጥሙ ብስለት ስንመለከተው “ፅዮን ሙሽራዬ” በሚለው ርእሱ እንዲህ ያቀነቅነዋል:

” ትዝታዬ አንቺ ነሽ ትዝታም የለብኝ
እመጣለሁ እያለሽ እየቆየሽብኝ
ጽዮን ሙሽራዬ መቼ ይሆን መምጫሽ
ፍቅር የተራበው ጨነቀው ልጅሽ
አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ነው አርማዬ
ልጄ ብለሽ ጥሪኝ አለሁ ኢትዮጵያዬ
ስቀሉት አርማዬን እንደማርያም ልጅ
ስቀሉት አርማዬን አውጡና እንጨት ላይ
ፍቅር ከሰው ሁሉ ከፍ በሎ እንዲታይ “አያለ ዜማውን ማቀንቀኑን ይቀጥላል፡፡
ቴዲ እናመሰግንሃለን ፡፡

ይህን ዜማ ከሰማን ስለ ሃገሩ ያለውን ስሜታዊ ፍቅር እና የሰው ልጅ መብትን የሃገሩን ባንዲራ ክብር የሚሰብክበት ትልቁ ዜማው ሲሆን በዚሁ ዜማ ውስጥ በተመሳሳይ መልኩ ሌላ የሰራው ዘፈን በተመሳሳይ ዜማ የፍቅር ስራው ታላቅነቱን አሳይቶበታል ፡፡ሌሎቹንም በታላቁ በኦሮሞ አባ ገዳ አና አንዲሁም ትዝታዎቹን ስንሰማ አኛነታችንን ማወቅ አስኪሳነን ድረስ ቀልባችንን ሊገዛው ይችላል አና በቅርቡ ያወጣዋል ተብሎ የሚታሰበው ይኸው አዲሱ አልበም ትልቅ ፋይዳ አንዳለው ከመግለፅ አልሽሽግም ከቀድሞዎቹ ስራዎቹ በላይ ድንቅ ድንቅ ድንቅ ተብለው የሚገለፁ ብቻም ሳይሆን በክብር ሊወደሱ የሚችሉ ስራዎች አንዳሉት አይቻለሁ ስለዚህ በአድማስ ላይ በተለጠፈለት ጭፍን አመለካከት ላይ ዝም ብሎ በደፈናው ከመመልከት ይልቅ ቴዎድሮስ ምን ሰራ እንዴት ሰራው መቼ አና በምን ሁኔታ ብሎ ማስተዋል ሊቅነት ሲሆን በሌላም በኩል አንድ አሱ ላይ ብቻ ትኩረትን ከማስተዋል ይልቅ ሌሎቹ ዘፋኞች ለምን አንደ አሱ ጥረት ለማድረግ አልሞከሩም ለምንስ እሱ የደረሰበት ደርጃ ላይ ሊቀመጡ አልቻሉም የሚለውንም በጥልቀት ማየት ምላሹን ሊሰጣቸው ይችላል ፡፡ በእርግጥም ሙዚቃ ሂዎቴ የሚለው ዜማዊ ቃል የሰራው ለቴዲ ብቻ ነው ለሌሎቹ ሙዚቃ ሞቴ ቢሆን ይሻላል ፡፡

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on January 10, 2012. Filed under COMMENTARY. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.