ቴዲ አፍሮ ነጠላ የጴንጤ መዝሙር አለመልቀቁን አረጋገጠ

(EMF) ሰሞኑን በቴዲ አፍሮ ስም የተለቀቀው የፕሮቴስታንት ወይም በተለምዶ የጴንጤ መዝሙር፤ የቴዲ አፍሮ አለመሆኑን፤ ቴዲ አፍሮን ያነጋገሩ የኢ.ኤም.ኤፍ ምንጮች ገልጸዋል። “በይቅርታ ተቀበለኝ” የሚለው መዝሙር በቅድሚያ የተለቀቀው በፕሮቴስታንት ክርስትና አማኞች ድረ ገጽ ላይ ሲሆን፤ ከዚያ በማከታተል በ24 ሰዓት ውስጥ በፌስ ቡክ እና በሌሎች ማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ ዜናው በሰፊው መሰራጨቱ ይታወቃል። ድርጊቱም “ከክርስትና አማኞች የማይጠበቅ…” በሚል ተኮንኗል።

ሆኖም “ስለመዝሙሩ ቴዲ አፍሮ ምንም አያውቅም። ሌላ ሰው የቴዲ አፍሮን ድምጽ አስመስሎ የዘፈነው ነው።” ተብሏል። በእርግጥም ይህ ከተነገረን በኋላ መዝሙሩን በድጋሚ ስንሰማው፤ ዘማሪው ድምጹን ብቻ ሳይሆን የአዘፋፈን ስልቱን ጭምር የቴዲ አፍሮን አስመስሎ ለመጫወት ጥረት ማድረጉ በግልጽ ያስታውቃል። ይህ ዜማ ቴዲ ቀደም ሲል ከተጫወተው “ንገሪኝ ካልሽማ” ከሚለው እና ከሌሎቹ ዜማዎቹ ቆንጠር ቆንጠር ተደርገው ከተወሰዱ በኋላ የተገጣጠሙ መሆናቸው ነው የተገለጸው። ዘማሪው ዘፈኑን ጥሩ አድርጎ ቀይሮ ቢጫወተውም፤ ይህንኑ የድምጽ ክሊፕ ከቴዲ አፍሮ ምስል ጋር በማቀናበር የተለቀቀው ቪዲዮ ተራ ዝናን ለማግኘት የተደረገ አሳፋሪ ተግባር መሆኑን ብዙዎች ይስማሙበታል።

በዚህ ነጠላ ዜማ ምክንያት፤ ቴዲ አፍሮ “ሃይማኖቱን ቀይሯል፤ ከ’ንግዲህ አይዘፍንም” የሚል ወሬ በሰፊው ከመሰማት አልፎ፤ በሌሎች የአሜሪካ ክፍለ ግዛቶች የሚያደርጋቸው ዝግጅቶች የሚሰረዙ መሆናቸው በወሬ ደረጃ ቢሰራጭም፤ በቅርብ የሚደረጉት የኦሃዮ፣ የቦስተን እና የላስ ቬጋስ የሙዚቃ ዝግጅቶች የሚደረጉ መሆናቸውን የቴዲ አፍሮ ፕሮሞተሮች በተለይ ለኢ.ኤም.ኤፍ ገልጸዋል።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on December 11, 2012. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

2 Responses to ቴዲ አፍሮ ነጠላ የጴንጤ መዝሙር አለመልቀቁን አረጋገጠ

  1. ግርማ ካሳ

    December 13, 2012 at 2:22 PM

    ይሄ በጣም የሚባርቅ መንፈሳዊ መዝሙር ነዉ:: ድምጹ የቴዲ አፍሮ ይመስላል:: ይሄን መዘመሩም ጴንጤ አያሰኝዉም:: መልእክቱ ለማንም ክርስቲያን የሚሆን ነዉ:: “ልቤን ሰጥቻለሁ (ለእግዚአብሄር)” የሚል ነዉ:: ይሄንን አይደለም በግእዝ በቅዳሴ የምንለዉ ??

  2. ብርሃኑ

    December 14, 2012 at 12:37 PM

    በጣም የሚገርመው ነገር የዚህ የፕሮቲስታንት እምነት አራማጆች አንድን መንገደኛ የነሱን እምነት ተከታይን በማዘጋጀት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቢተክርስቲያን ጳጳስ አስመስለው የክህደት ተግባር መፈጸማቸውን ስናስብም በቲዲ አፍሮም የፕሮቲስታንት መዝሙር ዘመረ እና ፕሮቲስታንት ሆነ በማለት ህዝብን ማደናበር እነዚህ ሰዎች ዛሪም ከኦርቶዶክስ ቢተ ክርስቲያን ላይ አለመውረዳችውንና ቢቻል ከሚያፈራርሱ ጋር በማበር ለማዳከም የማይመለሱ መሆናቸውን ያረጋገጠልን ጉዳይ ነው:: ደግሞም ቲዲ አፍሮ ጲንጢ ቢሆንስ ምን የሚያስደንቅ ነገር አለ ከቀየረም ቀየረ ይባላል እንጂ እሱን ተከትሎ የሚጠፋ ሰው የለም::