ቴዎድሮስ አድሃኖም ቢያጥቡት የማይጠራ… (ኤፍሬም ማዴቦ)

የኢትዮጵያ ህዝብና እናስተዳድረዋለን የሚሉት አምባገነን ገዢዎቹ ተስማምተዉና አንዱ ሌላዉን አክብሮ የኖረበት አንድም የታሪክ አጋጣሚ የለም። የእስከዛሬዉ ታሪካችን ምዕራፍ በጥቅሉ ሲታይ ታሪካችን የሚቋጨዉ ህዝብ ተረገጠ፤ ተጋዘ፤ ገዢዎች ደግሞ ረገጡ፤ገዙ፤ አሰሩ፤ አጋዙ እየተባለ ነዉ። አዎ! የኢትዮጵያ ህዝብ እስከዛሬ ባለዉ ታሪኩ ተግዟል፤ ተረግጧል፤ ተንቋል፤ ተንቋሿል። የዘንድሮዉ በተለይ ባለፉት ሁለትና ሦስት ሳምንታት እየደረሰብን ያለዉ ብሄራዊ ዉርደትና ንቀት ግን ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ ልዩ ከልዩም ልዩ ነዉ። በቀዳማዊ ኃ/ሥላሤ ዘመን የኢትዮጵያ ህዝብ ልክ እንደዛሬዉ ሰብዓዊ መብቱ ተረግጧል፤ ፍትህ ተነፍጓል፤ ነጻነቱን ተገፍፏል፤ ሆኖም አገር ዉስጥም ከአገር ዉጭም ፈላጊና ባለቤት አንደሌለዉ የቤት ዉስጥ እንስሳ የወገንም የባዳም እጅ አልተረባረበበትም። አንገፍግፎን አንፈልግም በቃ ብለን ያስወገድነዉ የቀዳማዊ ኃ/ሥላሤ ስርዐት በስልጣን ላይ በነበረበት ግዜ “ኢትዮጵያ” የሚለዉ ስምና “ኢትዮጵያዊነት” አገር ዉስጥም ሆነ አዉሮፓ፤ አሜሪካና አፍሪካ ዉስጥ እጅግ በጣም የተወደደና የተከበረ ስም ነበር። ዛሬ ወያኔ ነጻ አወጣኋችሁ፤ እኩልነት አመጣሁላችሁ እያለ በሚሰብክበት ዘመን ግን የኢትዮጵያ ሀዝብ አገር ዉስጥም በዉጭ አገሮችም ባለቤት አንደሌለዉ ፈረስ ማንም የሚጋልብበት ፈላጊ እንደሌለዉ ዕቃ ያገኘ ሁሉ እንዳሰኘዉ እጁን የሚያሳርፍበት የተናቀ ሀዝብ ሆኗል። ለመሆኑ ለምንድነዉ ኢትዮጵያዊነት እንደዚህ እንደ ተራ ዕቃ የቀለለዉ? ኢትዮጵያዉያንስ ለምንድነዉ በየሄዱበት እንዲህ አይነት ዉርደትና ስቃይ የሚደርስባቸዉ? መልሱ ቀላል ነዉ። “ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ” ወይም “ባለቤቱ ያቀለለዉን አሞሌ ባለዕዳ አይቀበለዉም” ነዉ። Click here … to read the story in PDF.

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on November 28, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.