ቴሌፎኑ ‘ለግዜው’ ጥሪ አይቀበልም (ክንፉ አሰፋ)

ethio-telecom

(በመከራ መስመር ሲገኝ እንዲህ ያስደስታል)

“የደወሉላቸው ደምበኛ ለግዜው ጥሪ አይቀበሉም።…” የምትለዋ አሰልቺ የቴሌ መልእክት ያላጋጠመው ቢኖር  ወደ ኢትዮጵያ ስልክ ደውሎ የማያውቅ ሰው ብቻ መሆን አለበት። ኮ/ል መንግስቱ ሃይለማርያም ወደ ቀድሞ ወዳጆቻቸው መደዋወል ጀመሩና በመሃል ተስፋ ቆረጡ አሉ። አስር ለሚያህሉ አርሶአደሮች እና የሰራዊቱ አባላት ዘንድ ደውለው አልተሳካለቸውም። ለሁሉም ጥሪ ያገኙት ምላሽ “የደወሉላቸው ደምበኛ ለግዜው ጥሪ አይቀበሉም።” የሚል ሲሆንባቸው ራሳቸውን ነቀነቁ። ሰው ሁሉ የጨከነባቸው መሰላቸው። እንዲህም አሉ።  “የሃገሬ ሰው እንኳን የስልክ ጥሪ፤ የእናት ሃገር ጥሪስ መች ተቀበለ።”

ለአመታት በተከታታይ በሁለት ድጅት  እያደገች ያለች ሃገር የስልክ መስመር ችግር ይገጥማታል ብሎ ማሰብ ይከብዳል። ችግሩን በደንብ ላልተረዳው፣ ሰው የሞባይል ስልክ የሚገዛው እንዲሁ ይዞ ለመታየት ነው ያስብል ይሆናል።  ይህ አባባል በከፊል ትክክል ነው። ዘመናዊ ስልክ በመያዝ ለላንቲካነት ብቻ የሚጠቀሙበት  ሰዎች አይጠፉም።    የቻይናው ቀፎ ከሞዴል አርሶ አደሮች አልፎ ተራው አርሶ-አደር እጅ ላይም ገብቷል።  አብዛኞቹ ግን ተንቀሳቃሽ ስልካቸውን አይጠቀሙበትም።  ለዚህም ይመስላል በርካታ ተንቀሳቃሽ ስልክ የሚይዙ ሰዎች እንዲሁ ለእይታ እና ለላንቲካ ብቻ የሚመስላቸው። አገልግሎቱን በተመለከተ ግን 99 በመቶ የሚሆነው ችግር የመዋቅር ችግር ነው።  Continue Reading –>

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on April 21, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.