ታሪክን ለማጥፋት ሃውልቱን ማንሳት?

(በማኅደረ አንድነት ራዲዮ ቀርቦ የነበረ)   የአቡነ ጴጥሮስ ሃውልት ሊፈርስ ነው የሚል መጥፎ ዜና ስሰማ ለረዥም ዓመታት ወደተለየኋት ውድ አገሬ መናገሻ ወደ አዲስ አበባ በትዝታ ጭልጥ አልኩኝ። ሌሊት አንበሶች ሲያገሱ ከሚያድሩበት መንደሬ ጀምሮ ያሉትን ሃውልቶች ማስታወስ ጀመርኩኝ። 6 ኪሎ የተተከለው የየካቲት 12 የሰማዕታት ሃውልት፣ ወረድ ብሎ 4 ኪሎ በድል አድራጊነት ንጉሰ ነገሥቱ አዲስ አበባ የገቡበት መታሰቢያ የሚል ከትምሕርት ሚኒስትር ደጃፍ የተተከለ፤ ወደ ራስ መኰንን  ድልድይ አቅንቼ የራስ መኰንን ሃውልት፤ ፊልም ከማዘወትርበት አካባቢ ከፒያሳው ስዘልቅ ከሲኒማ ኢምፓየር ፊት ለፊት ሕንዳውያን ለቀ.ኃ.ሥ በስጦታ ያበረከቱት የቀ.ኃ.ሥ ሃውልት፤ ግርማ ሞገሱ እንደ ንጉሡ የተዋጣለት የምኒልክ ሃውልት ከጊዮርጊስ ፊት ለፊት፤ የአቡነ ጴጥሮስ ሃውልት በማስታወቂያ ምኒስትር፣ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያንና የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት መካከል፤ ቸርችል ጐዳናን አሽቆልቁዬ ከቀ.ኃ.ሥ (ብሄራዊ ቴአትር) ቤት የቆመ የአንበሳ ሃውልት፤ ከምድር ባቡር ደጃፍ የሞዓ አንበሳ… ግራ ቀኝ ብል ሌሎችን ለማስታወስ አልቻልኩኝም። ግን እነዚህ ትዝ አሉኝ። ሁሉም የታሪክ ማስታወሻዎች ናቸው።

 የሞዓ አንበሳ ሃውልትና የአክሱም ሃውልት ከትግራይ በጣሊያን ተወስደው ወደነበሩበት ለመመለስ ዘመናት አስቆጥረዋል። ቀደም ሲል ከጠራኋቸው ሃውልቶች መካከል ሲኒማ ኢምፓየር ደጃፍ የነበረው የቀ.ኃ.ሥ ሃውልት በ66ቱ አብዮት ወቅት ተገንድሶ መጣሉን አስታውሳለሁ። ደርግና ወያኔ ያቆማቸው ሃውልቶች እንዳሉ ሰማቻለሁ። በቅርቡም ትችትና ተቃውሞ የተነሳባቸውም አሉ። ወደዚያ ዝርዝር ውስጥ አልገባም።

 ወያኔ ከጥንት ከመሠረቱ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት የመጣ ሃገር ከሃዲ ነው። ግፉና በደሉ ተቆጥሮ የማያልቅ ነው። ኹለቱን ብቻ ለተነሳሁበት ገለጻ በማንሳት ሃሳቤን ላፍታታው እሞክራለሁ። ኢትዮጵያዊነትን ማጥፋትና የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን መደምሰስ የጥፋት ዓላማዎቹ ዋና አርዕስት ናቸው።

 ወያኔ አዲስ አበባን እንደተቆጣጠረ የምኒልክ ሃውልት እንዲፈርስ ሙከራ ነበር። ያን ጊዜና ዕድል ሳይሳካለት ስለቀረ ልማትና ዕድገት በሚለው ማደንዘዣው በዙሪያ ጥምጥም መጥቶ ቀለበቱ ሊጋጠም ሲቃረብ ይታየኛል። ለጎጠኛ ጳጳስ ሃውልት ተተክሎ ለአገሩና ለሃይማኖቱ የተሰዋውን ጀግና መታሰቢያ ከታሪክና ከታሪካዊ ቦታው ለማጥፋት ማቀዱን ስሰማ ከፍተኛ ንዴት ነው የተሰማኝ። ሃይማኖትና ሃይማኖተኛን፤ ብሔራዊ ስሜትና አንድነትን ለማጥፋት የወያኔው ቁንጮ መለስ ዜናዊ የራዕዩ መጥፎ መንፈስ አሁንም እየተቅበዘበዘ መሆኑ በጣም ያሳዝነኛል።

 ተንኮለኛ መሪ፣ ደደብ መሀንዲስ፣ አድር ባይ ግንበኛ፣ ለዲናር የሚሸጥ በዲናር የሚገዛ ራዕይ አልባ የባንዳ ጥርቃሞ ታሪክን ለማጥፋት ቢጥሩም ከድካማቸው በኋላ ውጤት አልባ እንደሚሆኑ ጥርጥር የለኝም። ለዚህም ያለኝን ትዝብት ላቅርብ።

 የአገር ፍቅር፣ የሕዝብ መውደድ ያለው ወንድማችን ጥላሁን ገሠሠ ከሕይወት ሲለየን በተደረገለት ታላቅ አሸኛኘት በሚወዳት ባንዲራው ባረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ሰንደቅ ዓላማ በክብር ሲያርፍ የባንዲራ ክብርን ለኹላችንም አሳይቶን ነበር። ሰንደቅ ዓላማችንን ጨርቅ ነው እያለ ያጥላላ የነበረው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ አስከሬኑም ይኹን ባዶ ሳጥኑ የከዳውን ኢትዮጵያዊነት በሚያጎናፅፈው ሰንደቅ ዓላማ ተሸፍኖ ነበር ከእኲይ ሥራው የተሸኘው።

 ምኒልክም ኾኑ አቡነ ጴጥሮስ የተዋጉት ፋሺስትን፣ ዘረኛንና ጠላትን ነበር። በታሪክ አጋጣሚም ኹለቱም የተዋጉት ጣሊያንን ሲሆን ምኒልክ በዐድዋ ላይ ባስገኙት ድል ኢትዮጵያ በሌሎች ነጮች ላለመደፈር ጋሻ የኾነላት ነበር። ባንዳና የባንዳ ልጆች ያልተጠየቁት ወይንም የማይመልሱት ጥያቄ ቢኖር ዛሬ በጎሣ ላይ የተመረኮዘ አገዛዝ በአገሪቱ ላይ ያንሰራፉት አምባገነኖች ኢትዮጵያውያን ከዳር ዳር ሆ! ብሎ በመነሳት በኢትዮጵያዊነታቸው ብቻ ዐድዋ ባይዘምቱ ኖሮ የትግራይ ዕጣ ምን ይኾን ነበር? እንደ ኤርትራ የጣሊያን ቅኝ? ከሆነም ደግሞ ትግሉ ለትግራይ ሕዝብ አርነት ወይስ “ኢትዮጵያ ወይ ሞት”?

 በትግራይ ሕዝብ አርነት ስም የተደረገው የ17 ዓመት ትግል የት እንዳደረሰው እያየን ነው። በኢትዮጵያዊነት ስም ታግሎ ቢሆን ኖሮ በሕወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ሥር የትግራይ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጭቆና ሳይወጣ ስቃዩ እስካሁን ባልቆየ ነበር። ቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔ እንደሚለው ለትግራይ ሕዝብ ጠላቱ ሳይሆን ዐድዋ ከተማ ድረስ ሄዶ ለኢትዮጵያ ነፃነት የተሰዋ ሲሆን ትግራይ ለ’ኔ ምኔ ነው ብሎ ባይዘምት ኖሮ እንደተቀኙ የአፍሪቃ አገሮች የታሪክ ጠባሳ አሻራውን አድምቆ ይቀር ነበር።

ለምንድነው የራሳችንና ወገናችን የኾነውን የምናጣጥል፣ የምንንቅ? በሌላው ታሪክና ሃውልት የምንደነቅ? የራስን ግን ጠንቅቀን የማንጠብቅ?

 በምኒልክ ላይ አነጣጥሮ የነበረው የሃውልት ማፍረስ በአቡነ ጴጥሮስ ዞሮ የምኒልክን ጀርባ ሊወጋ ደፋ ቀናው እንቅልፍ ባሳጣኝ ወቅት ስለ ሕንዶቹ… እነዚያ ለቀ.ኃ.ሥ መታሰቢያ ያስቀረፁት ሕንዶች ሙምባይ ውስጥ የሠሩትን የሚያሳይ ቪዲዮ ተመለከትኩኝ። እስቲ ስለ’ሱ በትንሹ ላስተዋውቃችሁ።

 ሻትራ ፓጂ ሺባጂ ይባላል። በ17ኛው ክፍለ ዘመን ምዕራባዊ ሕንድን ይገዛ የነበረ ንጉሥ ነበር። በታሪክ ከፍተኛ ሥፍራ የተሰጠው በመኾኑ በከተማው ውስጥ ሃውልት ተተክሎለታል።  20 ሚሊዮን ሕዝብ በሚርመሰመስበት የሙምባይ ከተማ ውስጥ ከአይሮፕላን ማረፊያው አጠገብ ይገኛል። የከተማዋ ኢኮኖሚና የሕዝቡ ብዛት ማደጉን አላቋረጠም። የአይሮፕላን ማረፊያው አሮጌ በመሆኑ ከዕድገቱ ጋር ለመራመድ አልቻለም። ስለዚህ አዲስ አይሮፕላን ማረፊያ መገንባት አስፈለገ። ግን አራት ዐበይት ችግሮች አጋጠሙት። 1ኛ፦ በረራው መደናቀፍ የለበትም   2ኛ፦ የሕዝቡ እንቅስቃሴ መገታት አይኖርበትም   3ኛ፦ ኗሪዎች መፈናቀል አይገባቸውም   4ኛ፦ የታላቁ ንጉሥ ሻትራ ፓጂ ሺባጂ ሃውልት ከቦታው መነሳት የለበትም። እነኚህን ኹሉ መሰናክሎች እንዴት አልፎ ተደናቂና ትልቅ ዘመናዊ የአይሮፕላን ማረፊያ መሥራት ይቻላል?

 በአገራችን ያሉ ባለሥልጣናት ሕዝብን ከቀዬው፣ ከቤቱ ያፈናቅሉታል፤ በሃገሩ ቤት አልባ ስደተኛ ያደርጉታል። በዓለም ተደናቂ ታሪክ ለትውልድ ያስተላልፉልንና ፋሺስትንና ቅኝ ገዢዎችን ያሳፈሩልን የእነአፄ ምኒልክና አቡነ ጴጥሮስ ሃውልቶች ቋሚ ምስክርነታቸውን እየሰጡ የኢትዮጵያዊነት ኲራታችንን እያንፀባረቁ እንዳይኖሩ ሊያጠፉት ሽር ጉድ ይላሉ፤ ሸረኞቹ።

 ሕንዶቹ ግን ተገንብቶ የሚፈርስ መገንቢያ ገንብተው፣ ኗሪው ከመንደሩ ሳይፈናቀል፣ መጓጓዣው  አገልግሎቱ ሳይቋረጥ በረራው ሳይሰናከልና ሃውልቱ ሳይፈርስ መሀንዲሶቻቸው በቀየሱት ዘዴ ግንባታው ሲጠናቀቅ የሚያሳየውን ቪዲዮ እዚህ በመጫን ይመልከቱ።

  ወያኔ ኢህአዴግ በቀየሰው እቅድ መሠረት ሚያዚያ 24 ቀን 2005 ዓ.ም. ሃውልቱን ከነበረበት ሥፍራ አንስቶታል።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on May 4, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

2 Responses to ታሪክን ለማጥፋት ሃውልቱን ማንሳት?

 1. ይጥር5

  May 6, 2013 at 3:16 PM

  lier dergist

 2. T.Goshu

  May 6, 2013 at 8:29 PM

  Well, I do not know how and why we still look surprised and horrified by the ruling circle of which its very nature , behavior, policy, practice is c kind of devastating action do speak much more all kinds of words we use to describe . Yes, the very wicked and evil-driven inner circle of the regime is unequivocally telling the innocent people of Ethiopia that it is only and only at their will that everything should get done. They told and are telling us that whatever they want do is not peoples’ business . In other words, they are telling the people that there is nothing to think let alone to do something that stands against their will .

  The very paradoxical and puzzling thing is when it comes to the very silence and excessive fear we as a people are suffering from. We are not even willing and able to learn from our Muslim compatriots who keep making their voices heard more than a year. Have we observed their clear, simple but powerfully legitimate demands? a) no messing the dirty politics with their religious belief b) the right to elect the head of their religious affairs and make it responsible and accountable to them, and c) to have a sense of ownership and responsibility on their educational institution.

  Unfortunately enough, the we( the followers of the ETOC) do not look deeply worried and seriously angry about the destruction of Waldiba, witnessing the very muddling of our “religious leaders ” in a very dirty political game , and now the removal of the statue of the great religious leader and patriotic father ,Abune Petros and much more mess . We just keep being shocked and frustrated as if all the misery /suffering is a normal way of life.