ታማኝ – ጌታቸው አበራ

እልል አለች ኢትዮጵያ – እጆቿን ዘርግታ ወደ ሰማይ፣
ታማኝ ውድ ልጇ ዘወትር – እንዳልተለያት ስታይ፤
“ይደልዎ!” አለ ሕዝቡ – ያገር-አድን ቅኔ እንደተዘረፈ ሁሉ
በ”አቋቋም”፣ በአካሄዱ… ተማርኮ በውብ ቃሉ፤

Read the poem in PDF

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on February 18, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to ታማኝ – ጌታቸው አበራ

 1. Abiy Ethiopiawi+Segawi/wemenfesawi+አቢይ+ኢትዮጵያዊ+ሥጋዊ-ወመንፈሳዊ

  February 20, 2013 at 6:43 AM

  *****ታማኝ ሰንደቄ ነው::******

  በዘመነ-ግልምቢጥ ስትታመስ ዓለም:-
  እንደኢትዮጵያ አገር የትም እሣት የለም::
  ወላፈኑ የበዛ
  ፍሙ እግረ-መጥምጥ:-
  ኑሮው የፍዳነው በየቀኑ የሚያስምጥ::
  ሞታችን ሚሊዮን
  የሲዖል ነው ግፉ:-
  ከምሁራን ሞልተው ሕዝቡ የሚጠየፉ::
  እያዩ እንዳላዩ በሙታን ከተማ:-
  ሰቆቃው ግድያው እንደጉድ ሲሰማ:-
  ጆሮ ዳባ አልብሰው እርዱን እንዳልሰሙ:-
  ተራቸው ግን ደርሶ ይሄው ተለቀሙ::
  በነዚህ መሓል ነው ታማኝ ሰው ሲጠፋ:-
  የአያ በየነ ልጅ ለኢትዮጵያ ተስፋ:-
  በወጣትነቱ ልቡን እያሰፋ:-
  እንደዚያ ሲታገል ደሙን እየተፋ:-
  ከሙያው ከኑሮው ካገሩ ሲገፋ:-
  ወያኔ ወንጀል ላይ አንቅሮ እየተፋ:-
  አጋላጭ ነው ሓቁን በሰብዓዊነቱ:-
  እያንገበገበው ኢትዮጵያዊነቱ::
  በኢትዮጵያዊነቱ:-በሰብዓዊነቱ…
  መብቱን ዜግነቱን ሕዝቡን ሲመግበው:-
  ነፃነቱን እንዲል ምሁር ሳይገድበው:-
  በድፍረት በወኔ ወገኔን ከትበው::
  ያቺን ምሽት ለእኔ
  ለሌላው ሳስበው:-
  ስንቱ ታማኝ ሊሆን
  ትግሉን አነበበው::
  እኔ ግን በግሌ
  ድሮም እንደማምነው:-
  እንደ ብርቱካኗ
  ታማኝ ሰንደቄ ነው::

  መታሰቢያነቱ ለታማኝ በየነ ተጻፈ 07/10/2010
  የኢትዮጵያ አምላክ ይህን የአንበሳ ልብ እንደሰጠህ ብልኅቱንም ሆነ ዘዴውን ከጥንካሬው ጋር ይጨምርልህ::አሜን::