ተዋርደን አንቀርም!!! ኢ/ር ይልቃል ጌትነት (የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር)

ተዋርደን አንቀርም!!!
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት (የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር)

**********************************
ሳውዲ አረቢያ በዜጎቻችን ላይ እያደረሰች ያለውን ግፍና በደል በሰላማዊ ሰልፍ ለመቃወም ፓርቲያችን በወሰነው መሰረት ለሚመለከተው ክፍል አሳውቀን ነበር፡፡መቸም ህዝባችን በጭቆና ውስጥ ስለኖረ በመብቱና በግዴታው መሀል ያለውን ድንበር በውል ካለመረዳቱ የተነሳ ሰልፉ እንዲደረግ ስለመፈቀዱ በተደጋጋሚ ስንጠየቅ ነበር፡፡ህጉ የሚለው ግን ማስፈቀድ ሳይሆን ማሳወቅ ብቻ ነው፡፡በተቃራኒው መንግስት በተለያዩ ጉዳዮች ሳቢያ በእለቱ ለሰላማዊ ሰልፉ የደህንነት ከለላ መስጠት የማይችልበት ሁኔታ ከገጠመው ሰልፉን ለጠራው አካል ችግሩን ገልጾ ቀኑ እንዲተላለፍለት ይጠይቃል፡፡በመሆኑም ይህን መሰል ጥያቄ ከሚመለከተው መስሪያ ቤት ለፓርቲያችን ባለመቅረቡ በሙሉ ልብ ቅድመ-ዝግጅት ማድረጉን ተያያዝን፡፡

ሁሌም ቢሆን መንግስት ሰበብ ፈልጎ ሊወነጅለንና ከመስመር ሊያስወጣን እንደሚፈልግ በሚገባ እናውቃለንና በጥቃቅን ጉዳዮች ላይ ሳይቀር ጥንቃቄ እናደርጋለን፡፡ለሚመለከተው መስሪያ ቤት ባሳወቅን በአስራ ሁለት ሰአታት ውስጥ ምላሽ ስላልመጣ ሙሉ በሙሉ ህጋዊነታችንን አረጋግጠናል ማለት ነው፣እነሱ ደግሞ ጠብ-መንጃ በእጃቸው አለና የፈለጉትን ሁሉ ማድረግ ይችላል፡፡

Read story in PDF: ተዋርደን አንቀርም!!!

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on November 25, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

3 Responses to ተዋርደን አንቀርም!!! ኢ/ር ይልቃል ጌትነት (የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር)

 1. andnet berhane

  November 25, 2013 at 10:35 PM

  ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት እንደ መሪና ያለብህን ሃገራውዊና ወገናዊ ግዴታ በመወጣት የምታደርገው ጥረት እንዲሁም ባልደረቦችህ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች የሚያስመሰግን ተግባሮችን አከናውናችኋል ያባቶቻችሁን ያያቶቻችሁን ፈር በመከተል አሻራውን አስቀምጥችኋል:
  ውድ ኢትዮጵያውያን ሰማያዊ ፓርቲ ተገቢውን የትግል ስልት ነድፎ በምባር ሲጋፈጥ ለመጀመርያ ጊዘእ ኬምባገነኑ ቆንጮ ሞት በኋላ የመጀመርያው ሲሆን ስራአቱን አብረክርኮ ትግሉን ለማክሰም እየተደረበት ያለው ጫና ሳይበገር የሕዝብን ተሳትፎነት ልበሙልነት እየጠየቀ ባለበት ወቅት ሕዝብ የበኩሉን ሃገራዊ ግዴታ መወጣት ያለበት በፍርሃት ስይሆን በልበሙልነት ሲሆን ብቻ ነው::
  ትግል በሰላም ብቻ የሚወጣ ሳይሆን መቁሰል መሞት መታሰር ግዴታ አለው የስራአቱ ጋሻ ጅግሬዎች የታዘዝሁትን ለማድረግ ወደ ኋውላ አይሉም ደሞዝተኞች ናቸው ሃገራዊ ፍቅር ወገናዊ ክብር አይገባቸውም ምክንያቱም የስነ አይምሮ የስነ ልቦና ድክመት ያለባቸው ለመሆኑ የሚያስረዳው ከሰው መፈጥራቸውና ወንድም እሕት አባት እናት ልጅ እንዳላቸው ለመመዘን ባለመጫላቸው: ይህ ስራአት ይወድቃል ሃገርና ሕዝብ ግን ለዘላለም ይኖራሉ: ከዚህ ስራአት በኋላ ከሕዝብ መኖራቸውና መቆጨታቸው አይቅሬ ቢሆንም ዛረእን ባለመጠቀማቸው ለልጆቻቸው ለጠቅላላ ህብረተሰባቸው መለያቸው ምን ይሆን?
  እንግዲህ ሰልፍ ስትወጣ በግምባር በድፍረት በትባት ይህን ይገዥ መደብ አገልጋይ አንተ የርሱ ደሞዝ ከፋይና አላንተ ስራ እንድሌለው ተግባሩም አንተን ደሕንነትክን ለመጠበቅ እንጂ ሊያጉላላህና ሰላምክን አካልክን ሕይወትክን መብትህን ልጋፋና ሊጎዳህ እንዳልሆን በቃል ባንድነት አስረዳው አንድነትክንና የሱንም መብት ለማስከበር እንድሆነም አሳውቀው በትርም ሲሰነዝር ተከላከል ለመሸሸ አትሞክር በጽናት ስትቆም ሞራሉን ሕሊናቢስነቱን እንዲመዝን ታደርጋለህ:”ድርቢያብር አንበሳ ያስር” ሕዝብ ባንድነት ሲተባበር ያለውን ታንኩም አውሮፕላንም የታጠቀው ጋሻጃግሬ ዋጋ አይኖረውም: ልንዴም ለመጨረሻ ለሰላማዊ ሰልፍ ከወጣህ መመለስ የምትችለው የመብትህ ጥያቄ መልስ ስታገኝ ብቻ ነው
  ሰማያዊ ፓርቲ የትግል መርሆ ጠንክሮ ከሌላው ፓርቲዎች ጋር በመተባበር መስራቱ አስፈላጊ በመሆኑ በተናጠል የሚደረገው ወያነእን የልብ ልብ ስለሚሰጠው የሃገራችን መከራ የሕዝባችን ስቃይ እንዲያበቃ ባንድነት ለመስራት የተበቀ ትግል ታደርጉ ዘንድ በኢትዮጵያ አምላክ እማጸናለሁ:

 2. bezawit

  November 26, 2013 at 1:30 AM

  ውድ አድሚን
  ስላምና ጢና እየተመኘሁ;
  እባካችሁ ለአቶ ይልቃል ጊትነትና መሰሎች የማረግ ስም ኤ/ር ፐሚባለውን
  መጠቀም እንዲአቆሙ አሳስቡልኝ;
  ምክንያት1ኛ የተለያዩ ባለሙያዎች በኢትዮጵያችን ሞልተዋል እንዲሁም በሰማያዊ
  ብሎም በአንድነት ወ.ዘ.ተ ይህ አይነት አጠራር በመስርያ ቢት አንጂ ለፖለቲካ መጠቀሚያ በጣም የሚያስፍር ማእርግ ከቅንጅት ግዚ የመጣ የመከፍፈያ ስልት ነው ብየ ነው የማየው;አካውታንቱን;እኮኖሚስቱን;ነርሱን;ጋዚጠኛውን;ስይኮሎጂስት….
  ምን ሊባል ነው እረ እያስተውልን ቢሆን አይሻልም ወገኖቸ; ወይንስ እንደዚህ አይነት ማእረግ በኢትዮጵያ ብቻ ነው:ፕሪዘዳንት አኦባማ ለምን ጠበቓ ተብሎ አልተጠራም? ወይ ጉድ የሰው ልጅ መግኛ ብታ ኢትዮጵያ; ስለሆነ የውቐት ወይም የሙያ ተመክሮ እንድ ማረግ ተይዞ እ/ር ብቻ ነው ለፖለቲካ የሚሰጠው?

 3. በለው!

  November 26, 2013 at 2:30 AM

  **************************
  ምንኛ አፍዝ አደንግዝ አምክን ነው የዚያ..የሞተ ራዕይ?
  እረ ጎበዝ ተዋረድን ረከስን ርሃብም ስደትም በእኛ ላይ
  የጠፋበት አንድ ጀግና ቆራጥ ዜግነት ዳርድንበር ሰንደቅን የሚያይ
  ሁሉም ጆሮውን ቀስሮ ደነቆረ ላይሰማ?ዓይኑን አፍጥቶ ታወረ ላያይ?
  እውነት ነው ህወአትሻቢያ ቅጥረኛ ባንዳ ሆድ-አደር፣ አድርባይ
  በጣም ሀፍረት ነው ቅሌት ይህ ሁሉ ምሁር ካድሬ በበዛበት
  ከዓረብ አብሮ ዜጋን በሕግ መሸጥ የተቃወመን መደብደብ ማገት
  የፓርቲያቸው ማኒፌስቶ የብሔር ብሄረሰብ ሕገመንግስት
  የሀገር የህዝብ ማስከበሪያ ወይንስ የኢንቨስተር መብት
  ከከፋፋይ ጎጠኛ አድር-ባይ ሆድ-አደር ትምኪት
  አዎን!ተዋርደን አንቀርም!ኢትዮጵያን ከባንዳ ሳናነፃት
  ******
  ሌላው ቢቀር እንደምን ከበደ እንቢኝ ማለት!?
  መንግስት ተብዬውማ ምን ቸግሮት አተረፈበት
  በቋንቋ በባሕል በቀለም በሃይማኖት በታትኖት
  የሰውን ልጅ ተናጋሪ እንስሳ በክልል አጥሮት
  ብቻውን ነግዶ አትራፊ ባለሀብት አውራ አርገውት
  ብሔራቸውን ነገዳቸውን ለገንዘብ ሸጠውለት
  ዙሪያውን ከበው ሕዝባቸውን በልተው እያባሉት
  አሁን በህወአት/ወያኔ/ሻቢያ እያመካኙ ከንፈር የሚመጡት
  ጎበዝ ንቃ ያስጠቃህ ያንተው ብሄር ዘመድ እንደሆነ እወቅበት !።

  ******
  “ይሁን ስንል.. ያልፋል ስንል..ይሻላል እያልን
  ስቃይ መከራን አባብለን በመቻቻል ይቻላል ተንበርክከን…
  ማን ተሸካሚ? ማን ጫኝና አስጫኝ? እንደሆነም ሳይታወቀን
  ቀን ቀንን እየወለደው ዐመታት አስቆጠርን
  ታሰር፣ ተገረፍ፣ ሙት፣ እሺ !እንቢኝ ማለት አቅቶን
  እንደዋዛ ለመድነው ንቀትና ውርደትን
  ተንበርከን ጭነውብን ሰቅለነው ተቀምጠን
  ተደላድለው ጋለቡብን አሁን ማን ያውርድልን !?
  ጫናው ቢበዛ በገር ውርደት ሁለተኛ ዜጋ መሆን
  ይሻላል ብለን እርቀን ልንሞት ቤታችንን ጥለን ጠፋን
  የዱላም ገድ ከጭቆናም ዘረኝነት አሁንም ገረፉን::
  ዓረብ ከፋ ወገኔን እጅ እግሩን አንቀቱን በሜንጫ ቀላው
  ስብዕናውን ገፎ ውሻ አድርጎ አዋርዶ ገደለው !
  የአባቶችን አደራ የበላ የሚያወርሰው ምንም የሌለው
  ጣት መቀሰር፣ መጠላለፍ፣ መወነጃጀል፣መነጣጠል ለጅብ ነው
  እደግመዋለሁ ሀዘን ይብቃና ትውልዱን ንቃ በቃኝ በል በለው!።
  ****************
  ‘እንቢኝ ላሉ ከምስጋና ጋር በለው!’