ተበድለን ይቅርታ አንጠይቅም !

ፍትህ እና የሰብዐዊ መብት ጉዳይ ህዝቡ እርሙን ባያወጣም ከተቀበሩ ከ 21 አመታት በላይ ሆኗቸዋል። ይህ ያለው መንግስት እነዚህ ለህዝብ የሚስፈልጉ መሰረታዊ ነገሮችን በመቅበር ህዝቡ እንዳይተነፍስ በማድረግ አፍኖ መግዛቱን በማን አለብኝነት ተያይዞታል ። በሃገራችን ስለ መብት መጠየቅ ወንጀል ሆኗል ። ስለ መብት ደፍረው በሚጠይቁት ላይ የአሸባሪነት ታርጋ ይለጠፋል ፤ወደ ወህኒ ይወረወራሉ ፤ ከህግ ውጭ ኢ-ሰብዐዊ ግፎች ይፈጽምባቸዋል ፤ ከዛም አድርባይ ምሁር ነን ባዮችን በመጠቀም ተበዳዮች ይቅርታ ጠይቀው እንዲወጡ ይደረጋል ።ይህ የተለመደ ሰላማዊ ታጋዮችን ከጨዋታ ውጭ ማድረጊያ መንገድ ነው። ተበድለን ይቅርታ አንጠይቅም !

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on April 17, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.