(ቪድዮ) ሙስሊሞች በክርስቲያን ወንድሞቻቸው ታጅበው ቃሊቲን አጥለቀለቋት

(ዘ-ሐበሻ) የታሰሩ መሪዎቻቸው እንዲፈቱ እየጠየቁ ያሉት ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ከክርስቲያን ወንድሞቻቸው ጋር በመሆን ዛሬ እሁድ ቃሊቲ መሪዎቻቸውን ለመጠየቅ ግር ብለው በመሄድ መንግስትን ቆሌውን እንደገፈፉት የአዲስ አበባ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ዘግበዋል። በሺዎች የሚቆጠሩት እነዚሁ ኢትዮጵያውያን የታሰሩትን ለመጠየቅ በቃሊቲ ሲሄዱ ብዛታቸውን ያዩ የማረሚያ ቤቱ ጠባቂዎች በመደናገጥ “እስረኛ ሊያስመልጡ ይችላሉ” በሚል ስጋት ተጨማሪ የጥበቃ ኃይል እንዲመጣላቸው ሲጠይቁ ኢትዮጵያውያኑ ግን ፍጹም በሆነ ጨዋነት የመንግስትን ጠብ አጫሪነት ወደኋላ በማለት “በብዛታቸው የተነሳ እንደማያስገቧቸው ሲነግሯቸው” በሰላም ተመልሰዋል።

ክርስቲያኖች እና ሙስሊሞች እያሳዩት ያለው አንድነት መንግስትን እንዳስደነገጠው በተደጋጋሚ መገለጹ አይዘነጋም።

እስራኤል ሃገር የምትኖረው ዘጋቢያችን ሊያ ተሰማ የዛሬውን የቃሊቲ ቪድዮ አድርሳናለች።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on November 19, 2012. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.