ቦይንግ 767 – እገታ እና እንድምታው (ክንፉ አሰፋ)

abera

Hailemedhin Abera

          አንድ የኢህአዴግ ካድሬ፣  ቤት ለመከራየት ወደ አንዲት ወይዘሮ መኖርያ ይሄዳል።  ስፍራው እንደደረሰ ሌላ ተከራይም ከወይዘሮዋ ቤት ብቅ እንዳለ አስተዋለ። ሌላኛው ተከራይ ሰይጣን ነበር።  ሁለቱ ተከራዮች ሰርቪስ ቤቱን ለመያዝ እንደ ጨረታ ብጤ ጀመሩ።  ሰይጣኑ 400 ሲጠራ፣ ካድሬው ግን 500 ሊሰጥ ተስማማ።  በመጨረሻ፣ ወይዘሮዋ ቤቱን ለሰይጣኑ በትንሽ ዋጋ ማከራየቱን መረጡ። የወይዘሮዋ ውሳኔ እንግዳ ነገር ነበር።  ለሰይጣን፣ ለዚያውም በትንሽ ዋጋ ቤታቸውን ለመስጠት የወሰኑበትን ምክንያት ሲጠየቁ፤ “ሰይጣኑ አልወጣ እንኳን ቢል በጸበል ይለቃል። ካድሬው ገብቶ ቤቴን አልለቅም ቢለኝ ምን ላደርግ ነው?”  ነበር ያሉት ወይዘሮዋ። ከፍ ባለ ገንዘብ ለኢህአዴጉ ሰርቪስ ቤታቸውን ቢያከራዩት ኖሮ ባጭር ጊዜ ዋናውን ቤታቸውን ለቀው የመውጣት ክፉ እድል ይገጥማቸው ነበር።

          ዶ/ር መረራ ጉዲና ባለፈው ሳምንት ዘ ሄግ ላይ ስለ ወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ ሲነግሩን ጣል ያደረጓት ቀልድ ናት። የዚህች ቀልድ የፖለቲካ እንድምታ ቀላል አይደለም። መልእክትዋ ሲጠቃለል የኢትዮጵያን ህዝብ እየለቀቀ መሆኑን ትነግረናለች። እየከፋ የመጣው የኑሮውና የፖለቲካ ሁኔታ የህዝቡን አእምሮ ብቻ አይደለም እየነካው ያለው። ህዝቡ እየተገፋ ሃገርሩን ለቆ እንዲሰደድ እየተገደደም ይገኛል።  በተለይ ደግሞ ሃገሪቱ በድህነት ያስተማረቻቸው ምሁሮችዋንና ባለሞያዎችዋን እንደዋዛ እያጣች ከመጣች እነሆ ሁለት አስርተ-ዓመታት ተቆጠሩ።

እለተ ሰኞ የካቲት 10፣ 2006 ዓ.ም.።

የአለም ዜና ርዕስ ሁሉ ትኩረት የጣለው በኢትዮጵያዊው ፓይለት ጉዳይ ላይ ነበር። እንደዚህ አይነት ክስተት ሲፈጸም አዲስ አይደለም። ግን ይኽኛው ልዩ ነው። ይዘቱ ለየት ይበል እንጂ  በ 1998 (እ.ኤ.አ.) ዩዋን ቢን በተባለ ቻይናዊ ፓይለት ከተፈጸመው ድርጊት ጋር ይመሳሰላል። የ30 አመቱ ወጣት የበረራ ቁጥር CA905 የሆነውን የቻይና አውሮፕላን በመያዝ የታይላንድን የአየር ጠረፍ ሰብሮ ገባ። የ27 አመት እድሜ ያላት ሚስቱን ይዞ ታይዋን ላይ ያረፈው ፓይለት ለዚያ አደገኛ ውሳኔ የሰጠው ምክንያት የኢኮኖሚ ችግር ነበር።  የደረጃ እድገት፣ የደሞዝ ጭማሪ፣ የመሳሰሉ ከራስ ወዳድነት ያላለፉ ጥያቄዎች በማንሳት የፓይለቱ የራሱን ክብር ዝቅ አደረገው።   ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ…

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on February 22, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

3 Responses to ቦይንግ 767 – እገታ እና እንድምታው (ክንፉ አሰፋ)

 1. Dany

  February 22, 2014 at 9:31 AM

  በ EAL የተከሰተው ሁነታ ክልብ ማስተዋልን ይጠይቃል .ከሁሉ በፊት ድርጅቱ የሃገሪቱዋ ነው ,የተሰማራበትም መስክ ከፍተኛ ዉድድር ባለበት በአለም አቀፍ ንግድ ላይ ነው.ዛሬ ደርጅቶች ይፈጠራሉ ,ይዋሃዳሉ ,ያድጋሉ ,ይከስማሉ ..ወዘተ
  ስለዚህ EAL ክፉ እጣ እንዳይገጥመው ምን መደረግ አለበት :
  1.በተቀዋሚ ጎራ ያለነው ደርጅቱ የወያነ ነው በማለት boycot እስከማለት ደርሰናል-ይህ አቁዋም ትክክል አይመስለኝም ድርጅቱ ተዳክሞ ክገበያ ከወጣና market share ሩን አንዴ ካጣ በህዋላ ለመመለስ እንደ ቴሌ እና መብራት ሃይል ቀላል አይሆንም.የአለም ገበያ እንደ ሃገር ውስጥ ገበያ አይደለማ !!
  2.ወያኔ ድርጅቱን የሚፈልገው foreign currency ለማጋበስ ነው .ታዲያ ይህን አላማ የበለጠ የሚሳካው በአለም ደረጃ ድርጅቱን Competitive ማረግ ሲቻል ነው .ለዚህ ቁልፉ የድርጅቱ አመራር መሰረት በ Merit ላይ የተመሰረተ ሲሆን ነው .ይህ ተግባራዊ ሆኖ ቢሆን እን ሃይለመድህን እና መሰሎቹ ከሃገር ውጥተው የዉጭ Airline ኖችን ባላገለገሉ.
  ስለዚህ መንግስት ለራሱ ጥቅም ሲል ,አሁን የተፈጠረዉን ሁኔታ መነሻ በማድረግ ,በይፋ ያለችሎታ ምደባን ,የአንድ ዘር የበላይነትን ,የፓርቲን ጥርነፋ,cronyism የመሳሰሉ ጎታች ስርአቶችን የሚያስወግድ system ይትከል. ይሄን የሚተርጉሙ ባለሞያዋች በሃገር ውስጥም በዉጭ ይገኛሉ !! Reconsider Ato Girma Wake or others of equal caliber and business acumen.

 2. AleQa Biru

  February 22, 2014 at 5:44 PM

  አቶ ክንፉ አሰፋ፣
  የዶ/ር መረራ ቀልድ አስቃኛለች። ስቄ ሳበቃ ግን “ፖለቲከኞች የኮሜዲያንን ስራ ከወሰዱ ማን ፖለቲከኛ ሊሆን ነው?” ብየ አሰብኩ። ወዲያው ግን “ጋዜጠኖቻችን አሉልን” ብየ ተጽናናሁ። ቂቂቂ ….ይህች ደግሞ እኔ ጣል ያደረግኋት ቀልድ ነች፦)
  ወደ ዋናው የጦማርህ ፍሬ ነገር ስመለስ፣ አንዳንድ ግድፈቶች አሉ ብየ አምናለሁ። ለምሳሌ፦
  • ገጽ 2 ላይ የሚከተለው ዓርፍተ-ነገር ሰፍሯል። “ሃይለመድህን አበራ ‘እብድ ነው’ የሚሉም አልጠፉም፤ ልክ እንደ አፈቀላጤው ሬድዋን። “ አፈቀላጤው ሬድዋን የተባለው የኢህአዴጉ ሬድዋን ሁሴን ነው ብየ እገምታለሁ። እና መቼ እና የት ነው አቶ ሬድዋን ሁሴን ረዳት አብራሪው “እብድ ነው” ያሉት? ለአገር ውስጥ ሜዲያ የሰጡትን ገለጻ እዚህ ሊንክ ላይ ማዳመጥ ይቻላል። https://www.youtube.com/watch?v=v6rJxDOWHbM እዚህ ላይ እንዲታወቅልኝ የምፈልገው ጥብቅና የቆምኩት ለእውነት እንጂ ለአቶ ሬድዋን ሁሴን፣ ለኢህአዴግ ወይም ለመንግስት አለመሆኑን ነው።
  • አሁንም ገጽ 2 ላይ እንዲህ ተብሏል። “ሃይለመድህን በአንዲት ቅጽበት እና በአንዲት ቃል ብቻ ላለፉት 20 አመታት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ይፈጸም የነበረውን ግፍ ሁሉ ለአለም አሳወቀ።” ምንም እንኳ ረዳት አብራሪው የፈጸመውን ድርጊት በምን ሰበብ እና ለምን ምክንያት እንደሆነ ከራሱ አንደበት ባንሰማም ምናልባት አንተ እንዳልከው ሊሆን ይችላል ብለን እንውሰድ ለጊዜው። ከዚህ ተነስተን ግን ቢያንስ 2 ጥያቄዎች ማንሳት እንችላለን፦
  1. የውጩ ዓለም ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው/ስለሌለው የዴሞክራሲ ሁኔታ እስከ ዛሬ አያውቅም ነበር ማለት ነው?
  2. ለመጀመሪያው ጥያቄ መልሱ “አዎ” ከሆነ፣ እሺ አሁን የዓለም ህዝብ ስለኢትዮጵያ አወቀ። ከዚያስ ምን የተለየ ነገር ይፈጠራል ብለን እንጠብቃለን?
  በእኔ እይታ የዓለም ህዝብ በተለይም ልዩነት ሊፈጥሩ ይችላሉ ተብለው የሚገመቱት ታላላቅ መንግስታት የኢትዮጵያን ሁኔታ እኛ ከምናውቀው ባላነሰ ያውቃሉ። እያወቁም ግን የራሳቸው ብሔራዊ ጥቅሞች እስከተጠበቁ ድረስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ብለው ምንም ነገር ላለማድረግ ወስነዋል። ስለዚህ የረዳት አብራሪው ድርጊት (ጠለፋም ተባለ እገታ) ለእነዚህ “ተጽዕኖ ፈጣሪ” ናቸው ለምንላቸው መንግስታት አንዳችም የሚጨምረው ዕውቀት ይኖራል ብየ አልገምትም። የተወሰነ ዕውቀት እንኳ ጨመሮላቸው ይሆናል ብንል፣ የራሳቸው ብሔራዊ ጥቅሞች አደጋ ውስጥ እስካልገቡ ድረስ በኢትዮጵያ ላይ ያላቸውን ፖሊሲ የሚቀይሩበት ምክንያት አይኖራቸውም።
  • በመጨረሻም መግለጽ የምፈልገው ኢትዮጵያ ውስጥ እውነትም ጭቆና እና ብዙ ግፍ አለ ብየ አምናለሁ። ነገር ግን አውሮፕላን መጥለፍ (ወይም ማገት) ያለውን ችግር ያብሰው እንደሆን እንጅ ከጭቆና እና ግፍ የምንወጣበት አቋራጭ መንገድ ነው ብየ ለአንድም ሰከንድ አላምንም። እንደዚህ አይነት ድርጊቶች በተደረጉ ቁጥር አለመተማመን እና አለመረጋጋት እየጨመረ ይመጣል። በዚህም ሰበብ የመንግስት ጭቆና እየባሰና እየጠነከረ ይሄዳል። በመጨረሻም አገሪቱ ወደ ትርምስ እና ውድቀት ምናልባትም ጐረቤት ሱማሌ ወደ ተጓዘችበት መንግድ ታመራ ይሆናል። ይህ ደግሞ ኢህአዴግ ቢወድቅ አገሪቷን በተሻለ መንግድ የሚመራ አማራጭ ድርጅት/ቡድን/ፓርቲ አለ በማንልበት በአሁኑ ወቅት ለማንም አይጠቅምም።
  የተሻለ ሀሳብ ካላችሁ ለመስማት እና ለመማር ዝግጁ ነኝ።
  አለቃ ብሩ …

 3. tsehay

  February 23, 2014 at 4:04 PM

  ከወያኔ ጋር እጅና ጓንት ሆኖ ህዝብን ከመበደል መራቅ በራሱ ጥሩ ነው:: አብረው ህዝባቸውን እየጨቆኑ ያሉት የሌሎች ብሄር አባላት እየጣሉት ቢሄዱ ወያኔ ለብቻው ቀርቶ ይጋለጥ ነበር