ብፁዕ አቡነ ማትያስ ከአሜሪካን መልስ በደህንነት ቢሮ ለ72 ሰአታት ታስረው ተፈቱ

ኢትዮጵያ ውስጥ ኢትዮጵያዊ አሸባሪ የለም::” ብፁዕ አቡነ ማትያስ
“ከኦሮሞ እና አማራ ጳጳሳት ጋር ትፈተፍታላችሁ::” አቶ ጸጋዬ በርሄ ..የአፋኝ ደህንነቶች ሹም

በጳጳሳቶች እና በፌዴራሉ ሚኒስትሮች መካከል በስብሰባ ላይ በተነሳው አለመግባባት እና የጳጳሶቹ ድምጽ በደል እና ግፍን በማስተጋባቱ እንዲሁም ለመጣው ችግር ሁሉ ተጠያቂው የኢሕኣዴግ መንግስት ነው:ማለታቸውን ተከትሎ እንዲሁም ጳጳሱ አሜሪካን ተጉዘው ከመጡ በኋላ የሚያሳዩትን የቁጥብነት ባሕሪ ተከትሎ እንዲሁም በቤተክህነት ውስጥ የሚወስዱትን አስተዳደራዊ እርምጃ ያልጣመው ኢሕኣዴግ በአቶ ጸጋዬ በርሄ የሚመራው የአፈና እና የቶርች ቡድን ብጹእ አቡነ ማትያስን ለ72 ሰአታት በደህንነት ቢሮ በቁጣ እና በስድብ በማስጠንቀቂያ አሰቃይተው እና አንገላተው ወደ መኖሪያቸው እንደመለሱዋቸው ከደህንነት ቢሮ ምንጮቻችን ገልጸዋል:: ጳጳሱ ለ72 ሰአታት ከመኖሪያቸው ሲታጡ በጠቅላይ ቤተክህነት ውስጥ ሰዎች “አቡኑ ለህክምና ውጪ አገር ሂደዋል” የሚል ወሬ ሲያስወሩ ነበር::

ብፁዕ አቡነ ማትያስ በደህንነት ቢሮ ውስጥ በተሰጣቸው ማስጠንቀቂያ መሰረት ከአገሪቱ የመንግስት አካላት ጋር እንዲሁም ከጠቅላይ ቤተክህነት ውስጥ ካሉ የትግራይ ተወላጆች ጋር በቅርበት እንዲሰሩ የተነገራቸው ሲሆን በዙሪያቸው ያሉ የሲኖዶስ አባላትን ፊት እንዳይሰጧቸው እና አማራ እና ኦሮሞ ጳጳሳቶች እንቅስቃሴያቸው ሁሉ ከአቡነ መልከጻዲቅ እና ከተቃዋሚ ሃይላት መሆኑ አውቀው ጥንቃቄ እንዲወስዱ እንዲሁም አስተዳደራዊ ስራዎችን ለንብረዑድ ኤልያስ አብርሃ እንዲያስረክቡ ተነግሯቸዋል:: ከሳቸው ጋር በረዳትነት አቡነ ሳሙኤል እንዲሰሩ መመሪያ የተሰጣቸው መሆኑ ታውቋል::


ምንጭ፡ ሚኒሊክ ሳልሳዊ

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on December 29, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

6 Responses to ብፁዕ አቡነ ማትያስ ከአሜሪካን መልስ በደህንነት ቢሮ ለ72 ሰአታት ታስረው ተፈቱ

 1. ajire

  December 29, 2013 at 7:07 AM

  እንዲህ ነው እንጂ፣ በለው!

 2. tokchaw

  December 29, 2013 at 1:46 PM

  Abette Weyanae abette!! abette !! Egizabehere. yelehema! Men ale ende Melesse betetergachew! Menqsawen megrefe papasaten medebdeb; mefenkete erri belu zematebelu gugmanguge metaben

 3. ረታ

  December 29, 2013 at 3:34 PM

  ይገርማል: ይህ ነገር አስፈሪ ነው:: ሰዎቹ አበዱ እንደ?

 4. ለታ አያና

  December 29, 2013 at 3:59 PM

  እስኪገባው ውገረው:: በሃይማኖቱ ጥንካሬ የሌሌው እንደተንገዋለለ ይኖራል:: ለዘረኝነት መገዛት ዋጋው ይሕንን ይመስላል::

 5. Yemane

  December 29, 2013 at 6:20 PM

  I can’t belive that !! I thought he is One of weyanie members and Most of Websites had reported before that as he assighned from the ruling Party .gude sayisema meskeremm aytebamm allu!,,

 6. ተውብል

  December 29, 2013 at 8:37 PM

  ወያኔ መሬት እየለቀቀ ሄደ ትንሽ ቆይቶ ስብሃት ነጋን ፓትሪያርክ ብሎ ሳይሾም አይቀርም::