ብርቱ ሰው! (ከተመስገን ደሳለኝ)

ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ

…አራት ኪሎ በሚገኝ አንድ ካፍቴሪያ ከጓደኞቼ ጋር የደራ ወግ በመያዜ፣ የእጅ ስልኬ የ‹‹መልስ ስጠኝ›› ጩኸቱን ደጋግሞ ሲያሰማ ልብ አላልኩትም፤ እናም ጮኾ ጮኾ ሲጨርስ፣ እንደገና ይ ምራል፡፡ ይኼኔ ጥሪውን እንዳላስተዋልኩ የተረዳው ጓደኛዬ ወደ ስልኩ ሲያመላክተኝ፣ ቁጥሩን አየሁት፤ አውቀዋለው፡፡ የእስክንድር ነጋ ባለቤት የጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል ነው፤ አነሳሁት፡፡

‹‹በጣም ይቅርታ! ከሰዎች ጋር ጨዋታ ላይ ሆኜ ነው ያልሰማሁት…››

‹‹ለአስቸኳይ ጉዳይ ፈልጌህ ነበር፤ የት ነህ?››

‹‹ምነው? ምን ተፈጠረ?››

‹‹በስልክ አልነግርህም፤ መገናኘት አለብን››

‹‹እኔ አራት ኪሎ አካባቢ ነኝ››

‹‹ጥሩ! እኔም ፒያሳ ስለሆንኩ ‹ቲሩም ካፌ› እንገናኝ››

‹‹አሁኑኑ መጣሁ፡፡››

የሆነ ሆኖ የስልክ ንግግራችን ቢቋረጥም ድምጿ ከወትሮ የተለየ ስለሆነብኝ በእጅጉ ግራ ተጋባሁ፤ ምን አጋጠማት? እስክንድር ምን ሆነ? መቼም ኢህአዴግ ‹‹አስተዳድረዋለሁ›› የሚለውን ህዝብ ከፋሽስቱ ጣሊያንም በከፋ ጭካኔ እያሰቃዩ መደሰትን መገለጫው አድርጎታል፤ ታዲያ ዛሬ ደግሞ ምን ፍጠሪ እያላት ይሆን? ጥቂት ጥያቄዎች በውስጤ ቢመላለሱም፣ ጓደኞቼን በአጭሩ ተሰናብቼ በፍጥነት ‹‹ቲሩም ካፌ›› ደረስኩ፤ ቀድማኝ ስላገኘኋትም ወንበር ከመያዜ በፊት፡- Read story in PDF

 

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on July 22, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.