ብሄሬ ኢትዮጵያዊነት ነዉ – ግርማ ካሳ

ከበደ ካሳ የሚባሉ አፍቃሪ ኢሕአዴግ ግለሰብ  “አንዳንድ ሰዎች «ብሄር ..?» ተብለው ሲጠየቁ  «ኢትዮጵያዊ!!!…»  እያሉ የሚመልሱት፣ የራሳቸዉን ማንነት የኢትዮጵያ ማንነት አድርገው ያስቀመጡና በራሳቸው ማንነት የሌሎቹን ለመጨፍለቅ የሚያልሙ – የቅዠት ታንኳ ቀዛፊዎች ናቸው…. ተዛብታችሁ ሌላንም ለማዛባት ለምትፈልጉ ሁሉ ኢትዮጵያዊነት ዜግነት እንጂ ብሄር አይደልም። ኢትዮጵያ ሃገር እንጂ የአንድ ሕብረተሰብ ክፍል መለያ አይደለም።” የሚል አባባል ፌስቡክ ላይ ለጥፈው አነበብኩ።

በአንቀጽ 39 ንኡስ አንቀጽ  5 ላይ የኢትዮጵያ ፌዴራል ሕገ መንግስቱ እንዲህ ይላል ፡

“በዚህ ሕገ መንግስት ዉስጥ «ብሄር፣ ብሄረሰብ፣ ሕዝብ» ማለት ከዚህ ቀጥሎ የተገለጸዉን ባህርይ የሚያሳይ ማህበረሰብ ነዉ። ሰፋ ያላ የጋራ ጠባይ የሚያንጸባርቅ ባህል ወይም ተመሳሳይ ልምዶች ያላቸው፣ ሊግባቡበት የሚችሉበት የጋራ ቋንቋ ያላቸው፣ የጋራ ወይም የተዛመደ ሕልዉና አለን ብለው የሚያምኑ፣ የስነ-ልቦና አንድነት ያላቸውና በአብዛኛዉ በተያያዘ መልክአ ምድር የሚኖሩ ናቸው» Read story in PDF: ብሄሬ ኢትዮጵያዊነት ነዉ

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on February 7, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to ብሄሬ ኢትዮጵያዊነት ነዉ – ግርማ ካሳ

 1. በለው!

  February 7, 2014 at 9:15 PM

  >>>የኢህአዴግ አፍቃሪ ደጋፊና ተደጋፊዎች “የዕለት እንጀራችንን ስጠን ለዛሬ ብለው ይኖራሉ እንጂ…የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጭው ይላሉ እንጂ…የምን ዱቄት? ማን ፈጨው? የት ተፈጨ? ብለው አይጠይቁም! ሁድ ነዋ! የሆድ ነገር ሆድ ይቆርጥ የለምን!? ይህ የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች..ለምሳሌ. አበባ አበበች እና አባቡ አንድ ናቸው ብለው ይቀውጡታል፤ ትርጓሜው ፆታ የለው፣ መልክ የለው ቅርፅ የለው! ዋናው ቁምነገር ግን መታወቂያና ባንዲራ ይቀረፅለታል የአንገት ልብስ፣ ባርኔጣና ካኒቴራ ይሰጠዋል በባዶ እግሩ፣ በባዶ ሆዱ፣በባዶ ሜዳ ለለቅሶና ለጭፋሮ ይጠራል። በዚያውም ልክ ማንነቱን መግቢያ መውጫውን በክልል እነደተንቀሳቃሽ ከብት ተቆጥሮ ተቀምጧል። ይህንኑ ፍልስፍና ከዩኒቨርሰቲ ነጥቀው ደደቢት በረሃ የገቡት በዚያን ዘመን የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬ/መንግስቱ ኀ/ም ሽፍቶች፣ ወንበዴዎች፣ አሸባሪዎች፣ ገንጣዮች፣ ያሏቸው የአሁን ነጻ አውጭ፣የአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ልማታዊ አትራፊ መንግስቶች በገዛ ክልላቸው እንኳ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ብሔር ሰርተዋል። ግማሾች በአፓርታይድ መንደር ይኖራሉ ሌሎች ለመናገር፣ ለመፃፍ፣ ለመሰብሰብና ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ማሳወቅ መለመን ይጠበቅባቸዋል። ሁሉም ግን ከየት ነህ? ማነህ? ሲባሉ ኢትዮጵያዊ/ኢትዮጵያዊት ይላሉ እንጂ ብሔር ብሔረሰብ ነኝ አይሉም!የትም ሀገር አይባልምና~!!ፕሮፌሰር ተኮላ ሃጎስ ደግሞ ብሄር ብሄረሰብና ሕዝብ የሚለውን ለምን ሕገ መንግስቱ ዉስጥ እንደገባም ሲጽፉ የሚከተለዉን ነበር ያሉት፡
  “The phrase “the nations, nationalities and peoples” thus found in the Ethiopian Constitution is a legacy from the writings of immature and juvenile diatribe of badly educated and socially
  disfranchised and radicalized students of Haile Selassie I University of the 1970s. It is the ersatz voice of Meles Zenawi forcing himself through the 1995 Constitution on the People of Ethiopia his narrow and ignoramus ideas on the history of Ethiopia and the process of nation building”

  **እኛ ሀገር ለፖለቲካ ፍጆታ በኩረጃ የመጣች ግንጥል ጌጥ…ተረስታችሁ ማንነታችሁ ተነፍጎ የነበራችሁ ለእኛ በእኛ የተገናችሁና የምትኖሩ እኛ ከሌለን የምትጠፉ ይሏቸዋል።ሌሎችን ጨፍልቀው ደናቸውን እያቃጠሉ መሬታቸውን እየሸጡ አካባቢያቸውን በባለሥልጣን እያስወረሩ ፻ዓመት ታሪክ ፈጥረው አልቅሱ ድንኳን ጣሉ በነፃ የንፍሮ ስንዴ እናቀርባለን ይሏቸዋል። ሕክምና ትምህርት ገንዘብ ሲጠይቁ ግን ቋንቃችሁ አልገባንም ይባላሉ።

  “በአንቀጽ ፴፱ ንኡስ አንቀጽ ፭ «ብሄር፣ ብሄረሰብ፣ ሕዝብ» ማለት ከዚህ ቀጥሎ የተገለጸዉን ባህርይ የሚያሳይ ማህበረሰብ ነዉ። ሰፋ ያላ የጋራ ጠባይ የሚያንጸባርቅ ባህል ወይም ተመሳሳይ ልምዶች ያላቸው፣ ሊግባቡበት የሚችሉበት የጋራ ቋንቋ ያላቸው፣ የጋራ ወይም የተዛመደ ሕልዉና አለን ብለው የሚያምኑ፣ የስነ-ልቦና አንድነት ያላቸውና በአብዛኛዉ በተያያዘ መልክአ ምድር የሚኖሩ ናቸው»….ህገመንግስቱ ተዘዋውሮ ንብረት ማፍራት ወይም መኖር የሚለውን …የስነ-ልቦና አንድነት ያላቸውና በአብዛኛዉ በተያያዘ መልክአ ምድር የሚኖሩ ናቸው» ካለ “ሥነ ልቦናዬ አንድ አደለለም በቋንቋና በሕልውና ተከልሎ ከተሰጠህ ክልል ውጭ ከኖርክ ለመሥራት ከፈለክ ብሔር ብሔረሰብ አደለህም ልትባረር ልትጠቃም ትችላለህ።አፋን ኦሮሞ፣ ትግሪኛ፣ ጉራጌኛ፣ ሃምባሻ፣ ቆጮ ….በተለያዩ የአገራችን ግዛቶች ያሉ የተለያዩ ባህሎች፣ ቋንቋዎችን ፣ ምግቦች …ሁሉም «ኢትዮጵያዊነት» ናቸው። ሁሉም የኢትዮጵያ መገለጫዎች ናቸው። ኢትዮጵያ አንድ ወጥ አይደለችም። የተለያዩ ባህሎችን ፣ ቋንቋዎች፣ በአጭሩ የተለያዩ ብሄረሰቦች ያሉባት አገር ናት። ቢራቢሮዎችና አበባዎች የተለያዩ ቀለማቶቻቸው ዉበታቸው እንደሆነ፣ የኢትዮጵያም ዉበቷ ብሄረሰቦቿ ናቸው። ግን ልዩነታችን ውበታችን! ወይንስ ብዙሃነታችን ጥንካሬአችን!

  “የተከበራችሁ የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች…የአዲስ አባባና የአካባቢው ነዋሪዎች…የተከበራችሁ የሀረሪ ክልል መስተዳደር ነዋሪዎች..ተማሪዎችና አስተማሪዎች ..የዩኒቨርሲቲ መምህራን…የተከበራችሁ የጎዳና ላይ ተዳዳሪ ጋዶች!” አሉ አቶ ኀይለመለስ ደስአለኝ እሳቸውስ ብሔር ብሔረሰብ ተነግሮአቸው ደስስላላቸው እነጂ ምኑን ያውቁታል!!አስገራሚው የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድ ቀን ተረግዞ ተወለደና ክርስትና ተነሳን ተዘመረልን! “ብሄር ብሄረሰቦች ሆኑ የኢትዮጵያ ልጆች” በለው! ከውጭ ነው መጥተን የሰፈርነው ዜግነት ተሰጠን ማለት ይሆን!?ለምን በእኩልነትና በመፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ ልጅነት ከተገኘ አንዱ ጎሳ በሌላው ጎሳ፣ አንዱ መንደር ከሌላው መንደር፣ አድልዎ ይደርስበታል? ይታሰራል? የድንጋይ ውርወራ ፖለቲካ ለምን አስፈለገ!?ታዲያ እነኳን ፳፪ዓመት ሌላም ዘመን የሚያስቆጥር ፍዳ አደለምን!!ብዙ ቋንቋ፣ ባህል፣ ሃይማኖት፣ የታደለች የሁሉም የጋራ ቤት አንድ እናት ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!የተማረ ይግደለኝ ይቅር! የተማረ ያስተምር! ያልተማረ ይማር!!በቸር ይግጠመን