በጠመንጃ አስገዳጅነት የእውነት እጆች ቢታሰሩም፤  ህዝብ እውነታውን ይረዳል፤ ታሪክም ሃቅ ይፈርዳል!!

(በስደት ላይ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች የተሰጠ መግለጫ)

ቀን ጃኑዋሪ 25፣ 2012

በኢትዮጵያ ውስጥ ነጻ የሆነ አስተሳሰብ እንዲነግስ፤ በተለይ የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች ታላቁን ሚናተጫውተዋል። ሃሳብን በነጻነት መግለጽ የአንድ ሰብዓዊ ፍጡር መሆኑንን፤ ይህም በአኩሪ ኢትዮጵያዊያን የትግልውጤት የተገኘ እንጂ፤ የኢህአዴግ ችሮታና ስጦታ እንዳልሆነ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው አሰምተዋል። አልፎተርፎም  ስልጣን ከጠመንጃ ውስጥ በሚወጣ ጥይት ሳይሆን፤ ከምርጫ ሳጥን በሚገኝ የህዝብ ድምፅ መገኘትእንዳለበት በብዕራቸው ጫፍ መስክረዋል፤ አስተምረዋል። ይህን መሰረታዊ አስተሳሰብ መመሪያው አድርጎ ወደፊትየሚገሰግስ ህብረተሰብ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን በመፈጠሩ፤ ለነጻነት የሚደረገው ትግል ወደፊት እንጂ ወደ ኋላየማይቀለበስበት ደረጃ ላይ ነው።

(Click here to read the press release in PDF)

ላለፉት ሃያ አመታት የኢትዮጵያ ነጻ-ፕሬስ ጋዜጠኞች ከፋፋይ የሆነውን የኢህአዴግ ዘረኛ አስተዳደርበማውገዛቸው ለህዝብ ያላቸውን ወገንተኝነት አረጋገጡ እንጂ፤ የአገራቸውን ጥቅም በግል ጥቅም የቀየሩበትአጋጣሚ ከቶ የለም። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ፤ በስልጣን ላይ የሚገኘው አስተዳደር፤ ጋዜጠኞችን በአገር ክህደት፣በዘር ማጥፋት፣ ህዝብን በመንግስት ላይ በማነሳሳትና በሽብርተኝነት እየፈረጀ ጋዜጠኞችን ለእስር፣ ለእንግልትናለስደት መዳረጉን ይህ ትውልድ የሚመሰክረው ሃቅ ነው።

በ’ርግጥ ጋዜጠኞች፤ የገዢዎችን ጭንብል አውልቀው አጋልጠዋል፤ ከሃገር ጀርባ የሚፈጽሙትን ደባዎችአውግዘዋል። ይህ የእውነት ነበልባል የፈጃቸው፤ የሃቅ ብዕር ያቃጠላቸው አምባገነን ገዢዎች ግን እንቅልፍየነሷቸውን የብዕር አርበኞች በሰበብ ባስባቡ ማሰር፣ ማንገላታት እና ከአገር እንዲወጡ ማድረግ ተቀዳሚተግባራቸው፣ ዋነኛ አማራጫቸው አድርገውታል።

የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች የከፈሉትን መስዋዕትነት ለመረዳት ለሃያ አመታት የከተቧቸው ድርሳናትምስክሮች ናቸው። ለዚህ የጋዜጠኞች ውለታ የኢህአዴግ አስተዳደር “አሸባሪ” የሚል ቅፅል ሰጥቷቸውበማሰር፤ እውነት የሚናገሩ የፕሬስ ትሩፋቶችን ለማጥፋት የሞት ሽረት ግብግብ ላይ ይገኛል። ስለሆነምበሃሰት ክስ፣ በይስሙላ ፍርድ ቤት፣ ለሆዳቸው ባደሩ ዳኞችና ታጣቂዎች እየተመሩ እውነትን ለመግደልዛሬም ያለመታከት እየሰሩ ያሉትን ወገኖች አንድ ነገር ልናስታውሳቸው እንወዳለን። ወርቅ በእሳትእንደሚፈተነው ሁሉ፤ የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞችም በእሳት ተፈትነዋል። በዚህም የእሳት ፈተናእንደጨርቅ አልነደዱም፤ እንደወርቅ አንጸባረቁ እንጂ። እነሆ በህዝብ ላይ የሚደርሰውን የግፍ በትርተጋሩ፤ መራር የሆነውን የመከራ ፅዋም ስለህዝብ ብለው ተጎነጩ። እነሱ ታሰሩ፤ እነሱ ተሰደዱ፤ተንገላቱም። ሃሳብን በነጻነት ለመግለጽ  የሚደረገው ትግል ግን፤ ከቶውኑም አይቋረጥም።

እነ እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬ እና ርዕዮት አለሙ በሃሰት ክስ “አሸባሪ” ተብለው ለእስር ቤት ቢዳረጉም፤መላው ህዝብ እውነተኛ ማንነታቸውን ስለሚያውቀው፤ ነጻ ጋዜጠኞቻችን ከታሰሩበት የጨለማ ክፍሎች ውጪ፤በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው ምን ጊዜም አብረዋቸው ይቆማሉ።

እንደሌሎች የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች ሁሉ፤ እነሱም በእሳት የተፈተኑ ወርቆች በመሆናቸው፤ ህዝብ ታላቅየኢትዮጵያዊነት ኒሻን ያጎናጽፋቸዋል። ከ’ንግዲህ ታሪክ እና ትውልድ የአምባገነኖችን ክፋት ሲያነሳ፤ በመሰዊያውገበታ ላይ የቀረቡ የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞችን ግን ከፍ አድርጎ በክብር ይዘክራቸዋል። ዛሬ በህግ ሽፋን ሃቅየሚናገሩ አንደበቶች ቢዘጉም፣ በጠመንጃ አስገዳጅነት የእውነት እጆች ቢታሰሩም፤ ህዝብ እውነታውን ይረዳል፤ ታሪክም ሃቅ ይፈርዳል!!

ካለፉት ሃያ የነጻነት ትግል አመታት እንደተማርነው፤ ኢህአዴግ የተሸነፈ ሲመስለው ህዝባዊ ንቅናቄዎችንለመግታት ሲል ፍትህን ያዛባል፤ እጁም በደም ይነክራል። አሁንም በብዕር አርበኞች ላይ የወሰደው እርምጃሽንፈቱን እንጂ፤ መሪነቱን አያሳይም። በጠመንጃ አገዛዝ እና በህግ ሽፋን፣ በኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች ላይያደረሰውና እያደረሰ ያለው መከራም ተሸናፊነቱን ይበልጥ አጉልቶ ያሳያል። ኢህአዴግ የግፍ እና የበደል በትሩንባበዛው ቁጥር፤  የነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞችንና የኢትዮጵያን ህዝብ የድል ነጥብ ከፍ ያደርገዋል። ይህ ፋይዳ ቢስ ክስ እናየሚሰጠውም ፍርድ አምባገነኖች በሽብር ቆፈን ውስጥ ለመሆናቸው ጉልህ ምስክር ነው። እነሆ ኢህአዴግበፍርሃትና በሽብር ውቅያኖስ ላይ ሲቀዝፍ፤ በነጻ አስተሳሰብ ላይ የተመሰረተው ህዝባዊ መነቃቃት ደግሞ፤ የማያቋርጥ የጥሪ ደወሉን ከዳር እስከዳር እያስተጋባ፤ የነጻነት ትግሉን ይቀጥላል። ለዚህም ህዝቡ ከኢትዮጵያ ነጻፕሬስ ጋዜጠኞች ጎን በመቆም፤ የአንድነት ቃል ኪዳኑን እንዲያድስ  ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ካለፉት ሃያ የነጻነት ትግል አመታት እንደተማርነው፤ ኢህአዴግ የተሸነፈ ሲመስለው ህዝባዊ ንቅናቄዎችንለመግታት ሲል ፍትህን ያዛባል፤ እጁም በደም ይነክራል። አሁንም በብዕር አርበኞች ላይ የወሰደው እርምጃሽንፈቱን እንጂ፤ መሪነቱን አያሳይም። በጠመንጃ አገዛዝ እና በህግ ሽፋን፣ በኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች ላይያደረሰውና እያደረሰ ያለው መከራም ተሸናፊነቱን ይበልጥ አጉልቶ ያሳያል። ኢህአዴግ የግፍ እና የበደል በትሩንባበዛው ቁጥር፤  የነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞችንና የኢትዮጵያን ህዝብ የድል ነጥብ ከፍ ያደርገዋል። ይህ ፋይዳ ቢስ ክስ እናየሚሰጠውም ፍርድ አምባገነኖች በሽብር ቆፈን ውስጥ ለመሆናቸው ጉልህ ምስክር ነው።

እነሆ ኢህአዴግበፍርሃትና በሽብር ውቅያኖስ ላይ ሲቀዝፍ፤ በነጻ አስተሳሰብ ላይ የተመሰረተው ህዝባዊ መነቃቃት ደግሞ፤ የማያቋርጥ የጥሪ ደወሉን ከዳር እስከዳር እያስተጋባ፤ የነጻነት ትግሉን ይቀጥላል። ለዚህም ህዝቡ ከኢትዮጵያ ነጻፕሬስ ጋዜጠኞች ጎን በመቆም፤ የአንድነት ቃል ኪዳኑን እንዲያድስ  ጥሪያችንን እናቀርባለን።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on January 25, 2012. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.