በጐንደር አንድ የአንድነት ፓርቲ አባልና አንድ ደጋፊ መገደላቸው ተገለጸ

በደቡብ ጐንደር አዲስ ዘመን ከተማ አንድ የአንድነት ፓርቲ አባልና በወረታ ከተማ አንድ የፓርቲው ደጋፊ አንዱ በቆንጨራ ሲገደል አንዱ በጩቤ ተወግቶ መገደላቸውን የፓርቲው ድርጅት ጉዳይ ጽ/ቤትበተለይ ለፍኖተ ነጻነት ዝግጅት ክፍል ገለፀ፡፡ የፓርቲው ድርጅት ጽ/ቤት በላከልን ሠነድ እንደገለፀው በደቡብ ጐንደር ነዋሪ የነበረውና የፓርቲው አባል የነበረው አቶ ደሴ ካሰው በጩቤ ተወግቶ ሲሞት በወረታ ከተማ ነዋሪ የነበረው የፓርቲው ንቁ ደጋፊ የነበረው መምህር ሙሳ ኢብራሂም በቆንጨራ ተመተው ሁለቱም በአንድ ቀን ጥቅምት 6 ቀን 2004 ዓ.ም መገደላቸውን ገልፀዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡን ለአካባቢው ፖሊስ ጽ/ቤት ብንደውልም ስማቸውን ለመግለጽ ያልፈለጉ አንድ ሰው ስልኩን አንስተው ማንነታችንን ካረጋገጡ በኋላ ስልኩን በመዝጋታቸው ዜናውን ሚዛናዊ ማድረግ አልቻልንም፡፡
ምንጭ፡ ፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on October 27, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.