በጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደ ላይ የሀሰት ምስክርነት ተደመጠ

አዲስ አበባ: በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛው ምድብ ችሎት በሀሰት በሽብርተኝነት በነ አማን አሰፋ መዝገብ ውስጥ ተከሶ ጉዳዩን እየተከታተለ በሚገኘው በጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደ ላይ የሀሰት ምስክርነት እንደተሰማበት ምንጮች አስታወቁ፤፤

በጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደ ላይ በሀሰት እንዲመሰክር አቶአማኑኤል የተባለውን ግለሰብ የማዕከላዊ መርማሪ የሆኑት አቶተክላ እና አቶ ሳሙኤል ባለቤቱን በሃሰት ወንጅለው በማሰር በሀሰት ካልመሰከርክበት ሚስትህን አንፈታልህም በማለት እንዲመሰክርበት ማስገደዳቸውን ከዚህ በፊት ዘግበን ነበር፡፡ የሀሰት መስካሪውም ባለቤቱን ነፃ ለማውጣት ሲል ፍርድ ቤት በመቅረብ የተባለውን መፈፀሙን ምንጮች ዘግበዋል፡፡

አቶ አማኑኤል ድምፃችን ይሰማ የሚታገለው ከተሳካለት በሰላማዊ ትግል ካልተሳካለት ደግሞ ሙስሊሞችንበማስታጠቅ መንግስትን ለመገልበጥ ነው ብሎ የመሰከረሲሆን ይህንንም አላማ ጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደ ያውቃል በማለት በሃሰት መስክሮበታል፡፡
የምስክሩን ቃል ፍርድ ቤቱ ካደመጠ ቡሃላ መስቀለኛ ጥያቄ ተከሳሹ ሰለሞን ከበደ የጠየቀው ሲሆን በሀሰት የመሰከረውንበሙሉ ማስተባበሉን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ በዚህምድርጊቱ አቃቤ ህጉ ጥርስ የነከሰበት ሲሆን ለፍርድ ቤቱ ዳኛ እኔ ጨርሻለው በማለት ከችሎቱ ለመውጣት ቢጠይቅም አቃቤ ህጉ ይፈልግሃል ቆይ በሚል ካስቆዩት ቡሃላ ከችሎቱ መጠናቀቅ በኋላ የት እንዳደረሱት እንደማይታወቅ ተሰምቷል፡፡

ከጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደ ጋር በማዕከላዊ አብረው በታሰሩበት ወቅት ስለ ህዝበ ሙስሊሙ ህጋዊ የመብት ጥያቄ በቂ ግንዛቤ አግኝቶ እንደነበር መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ይህንንም ተገን በማድረግ ነበር የማዕከላዊ መርማሪዎች በሰለሞን ላይ በሃሰት እንዲመሰከር ያስፈራሩት እና ያስገደዱት፡፡
ሆኖም በሃሰት ከመሰከረ ቡሃላ በመስቀለኛ ጥያቄ ጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደ ስላፋጠጠው በሃሰት የሰተውን ምስክርነት ቃሉን በሙሉ ማስተባበሉ ተዘግቧል፡፡ እውነት ብትደበቅም ባልተተበቀችበት ቦታ ብቅ ማለቷ አይቀርም፡፡

ዘገባ፡ አቡ ዳውድ ኦስማን

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on November 12, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.