በጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ላይ ከተሰጠው ብይን ጀርባ ያለው ዳኛ ማነው?

(EMF) ርዕዮት አለሙ በጋዜጠኝነት ሙያ ህዝብን ስታገለግል የቆየች ጋዜጠኛ ናት። ገዢው መንግስት ግን ይህችን ጋዜጠኛ “አሸባሪ ናት” የሚል ክስ መስርቶባት 14 አመት ተፈረደባት። ሰሞኑን የተደረገው ጥናት ደግሞ አዲስ ፍንጭ ይዞ መጥቷል። ይኸውም በጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ላይ የጥፋተኝነት ብይን ሲሰጥ፤ በብይኑ ላይ የተጻፈው የእጅ ጽሁፍ የዳኛው እንዳልሆነ ተረጋግጧል። ይህ ከሆነ ታዲያ ከዚህ ብይን ጀርባ ያሉት እነማን ናቸው? በእንደዚህ አይነት የፍርድ ሂደት ሳይሆን፤ የፖለቲካ ውሳኔ ስንቶች ላይ በደል ደርሷል? ልክ ዛሬ በጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ላይ ከተፈረደባት 30ኛ ወር ሆነ። ይህንን አሳዛኝ የፍርድ ውሳኔ በመቃወም እና ህዝብም የራሱን ፍርድ መስጠት እንዲችል፤ ጥናታዊውን ጽሁፍ ከነመረጃው ለሁሉም ኢትዮጵያዊ አቅርበናል። ይህን ጽሁፍ በማንበብ የየራሳችሁን የህሊና ፍርድ ይስጡ። የዚህ ጽሁፍ ክፍል ሁለት በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ይቀርባል።
ከችሎቱ ጀርባ ያለው ጥቁር ዳኛ ማነው (ክፍል1)

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on December 23, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to በጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ላይ ከተሰጠው ብይን ጀርባ ያለው ዳኛ ማነው?

  1. Alem

    December 24, 2013 at 5:34 PM

    “ጥቁር” ዳኛ ከማለት “ስውር” ዳኛ ማለት ይሻላል። ነጮች እንደሚሉት ጥቁር መጥፎ ነው ማለት እንዳይሆን። በእንግሊዝኛ dark figure ይላሉ። ጸሐፊው በእንግሊዝኛ ያነበበውን በጥሬው ተርጉሞታል።