በጋምቤላ የምስጢር ደኅንነት ሠራተኛው ተገደሉ

በጋምቤላ ክልል በምስጢር የደኅንነት አባል ሆነው ይሠራሉ የተባሉት አቶ ጌታቸው አንኮሬ ባልታወቁ ሰዎች በድንገት መገደላቸውን ተከትሎ ቀደም ሲል በክልሉ የነበረው ውጥረት በከፍተኛ ደረጃ መባባሱ ተገለጸ። የክልሉ ባለሥልጣናትና ካድሬዎችም ስጋት ላይ ወድቀዋል።

የደቡብ ክልል ተወላጅና የህወሃት አባል በመሆን በክልሉ ለረዥም ዓመታት በምስጢር የደኅንነት ሠራተኛነታቸው የሚታወቁት አቶ ጌታቸው ጥር 24 ቀን 2012 ዓ.ም. አመሻሽ ላይ ህይወታቸው ያለፈው በፕሬዚዳንቱ አቶ ኦሞት ኦባንግ መኖሪያ ቤት ውስጥ ስብሰባ ላይ ቆይተው የመኖሪያ ቤታቸው ግቢ ውስጥ እንደገቡ ነው።

ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ የመረጃ ምንጮች ከስፍራው እንዳስታወቁት የአቶ ጌታቸው ህይወት ሊያልፍ የቻለው በመኖሪያ ቤታቸው ቅጥር ግቢ ውስጥ ባልታወቁ ሰዎች በተደጋጋሚ በጥይት ከተደበደቡ በኋላ ነው። በከተማዋ እምብርት ግድያውን ያከናወኑት ክፍሎች ለምን ጥቃቱን እንደፈጸሙ ከየትኛውም ወገን በግልጽ የተነገረ ነገር የለም። Read Full in PDF…

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on February 4, 2012. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.