በደል ይረሳል ወይስ ይለመዳል (3) ከይኸነው አንተሁነኝ

ኩልል ካለው ብሩህ ሰማይ የተንጠለጠለችው ደማቅ ፀሐይ ባጀብ የወጣች ያህል አካባቢው በሙሉ ግሏል። የአዲስ አበባው ጥቁር አስፋልት ከሙቀቱ የተነሳ ከርቀት ሲመለከቱት የባህር ግማሽ አካል መስሎ ለዓይን የሚያሰጋ ነጸብራቁን ከመርጨቱም በላይ ሙቀቱ የተጫሙትን ጫማ አልፎ ውስጥ እግርን መለብለብ ጀምሯል። ሽምጡን ጨርሶ እንደተመለሰ ላብ ያጠመቀው ሰጋር ሰንጋ ፈረስ አልፎ አልፎ በሬንጅ ቅላጭ የተወለወለው አስፋልት ከጫማ ጋር ፍቅር እየያዘው ለእርምጃ አስቸግሯል። እዚህም እዚያም ከሚሯሯጡት ጥቂት ታክሲዎችና የከተማ ባሶች በቀር ሁሉም ጸጥ እረጭ ብሏል። የሰው እንቅስቃሴ ላመል ነው። ሁሉም በየቤቱና ቴሌቪዥን ባለበት መዝናኛና የቀበሌ ክበቦች ታድሟል። በያለበት ዓይኖቹን በየቴሌቪዥን መስኮቶች ላይ ሰክቶ ቀጥሎ የሚመጣውን ትእይንት በጉጉት ይጠባበቃል። 1997ዓ/ም የበጋ ወራት እለተ ሰንበት ከስአት ነበር ጊዜው።

Click here to read the story.

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on December 14, 2012. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.