በደላላ ሃገር ሰትመራ – በታደለ መኩሪያ

በትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባር ሽፋን፤ ዛሬ ይህቺን ጥንታዊት ሃገር ኢትዮጵያን እየመራት ያለው ወያኔ የሚባል ቡድን ነው። ይህ የጭንጋፍ ስብስብ በትግራይ ሕዝብ ልባስ የኢትዮጵያን ለም መሬትና ቡቃቅላ ልጆቿን በደላላነት ለሳውዲ አረቢያ ሲያቀርብ መቆየቱን ዓለም ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ሐቅ ነው። የዚህ ቡድን የጥቅማጥቅም ተቋዳሾችና አልጠብባዮች ጋር በመተባበር ቤሔራዊ ኩራታችንን አደጋ ላይ ጥለውታል።እነዚህ የዕንግዴ ልጆች ሆድ አደሮች ፤ትውልድም፣ የገዛ ልጆቻቸው የሚያፍሩባቸው ናቸው። ይህቺን በደምና አጥንት የቆመች ሃገር በአደባባይ እንድትዋረድ አደርገዋታል፤የቤሔራዊ ውርደት እንድንከናነብ አድርገውናል፤ በአባቶቻችን መሰዕዋትነት ለዘመናት አንገታችንን ቀና እንደላደረግን ዛሬ በውርደታችን አፍረን አቀርቀረናል። ውርደታችንን ከማይጠገን ደረጃ ያደረሰው ደግሞ የአዲሰ አባባ ከተማ ኗሪ ሕዝብ በልጆቹ ላይ በሳውዲ አረቢያ በተፈጸመው የግድያ፤የአስገድዶ መድፈርን፣ የንብረት ዘረፋውን ተቋሞ ለማሰማት ወደ ሳውዲ ኢንባሲው በሄዱት ዜጎች ላይ ድብደባና እስራት መፈጸሙ ወያኔ የሳውዲ አረቢያ ደላላ ጥቅም አስጠባቂ፣ አለቅላቂ ቡድን መሆኑን ፍትው አድርጎ አሣይቶናል። Read story in PDF:በደላላ ሃገር ሰትመራ…

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on November 24, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to በደላላ ሃገር ሰትመራ – በታደለ መኩሪያ

 1. አቢይ ኢትዮጵያዊ+ሥጋዊ-ወመንፈሳዊ

  November 24, 2013 at 8:18 AM

  የጉጅሌዎችን የጠቆረ-የደም ፅዋ ታሪክ የማያውቅ ኢትዮጵያዊ የለም።ኢትዮጵያ ሐገራችንም የምትመራው በሕቡዕ ከሚሽሎከለኩት የእንግሊዞች ሴራ ጀምሮ መጥረቢያ ከሚያቀበሉአቸው ጣሊያውያን ድረስ፣ሌሎቹንም የኤሮፕ አገሮች ጨምሮ እነዚህን ባንዳ-አሽከሮች እንዳሽቆጠቆጧቸው ያደባባይ ሚሥጥር ነው።እናም አብዝተን ልንናገርባቸው ይገባናል፤ታአሪክ ይመዘግበዋል።

  ቅማሎቹን ትተን፣
  አንጠግብም ፎክተን።
  አህያውን ፈርተን-ለምን ዳውላውን?
  +++++++++++++++++++++
  እነዚህ ቅማሎች፣የተቅመለመሉ፤
  ከሸበጥ ከልዋጭ ዛሬ ፈቀቅ ያሉ፤
  ዘርፈው አዘርፈው ሕዝብ እየገደሉ፤
  በአገራችን ንብረት፣ሐብታም ነን የሚሉ፤
  ሰርተው-ያገኙት ሳይሆን ከድሆች አፍ ነጥቀው፤
  በሚሊዮን ገድለው በሚሊዮን ሰርቀው
  ያደባባይ ሚሥጥር መሆኑም ቢታወቅ፤
  ሁሉም ልቡ ፈራ በደም ለመጠየቅ።፡
  ለምን’ስ ይዋሻል በሰበብ አስባቡ፤
  አጋዚ ቅማሏ ቆማ ካጠገቡ፤
  የምን መፎከት ነው ይለይለት እንጂ፤
  ወያኔ ይፈራርስ በሕዝብ አመፅ-ፈንጂ።
  እናም እናስተውል እንወቅ ለይተን፤
  ቅማሎቹን ትተን፣
  አንጠግብም ፎክተን።
  ደማችንን መጠው፣መጠው ሲያስመጥጡን፤
  ያውም ሳውዲ ልከው በዶላር የሸጡን፤
  አልበቃ ብሏቸው እያስቀጠቀጡን፤
  ከግድያ ስንተርፍ በቁም-መሞት ቀጡን።
  እስከመቼ እንተወው ወያኔ-ባንዳውን፤
  አህያውን ፈርተን-ለምን ዳውላውን?
  ዳውላና አህያን በፍርሃት ሲስሉ፤
  የአባቶች ትርጉሙ ጠሊቅ ነው አባባሉ።
  የዘመኑ አህያ ዳውላውስ ማነው?
  አይተን እንዳላየን በቀን የፈራነው።
  አህያው አጋዚ ዛሬም የመሸበት፤
  በቀን ሰው ይመስላል፣
  ቆዳው ዥብ አለበት።
  ችግራችን ደግሞ ተነግሮ ያላለቀው፤
  ዳውላው እኛ ነን የማንደብቀው።
  ጅቦቹ በቀትር ጅብ አህያም ናቸው፤
  ወቸገል ከሞተ አጡ የሚያናምናቸው።
  እርኩሶች በቀን-ፊት ሰዎች ይመስላሉ፤
  የሕዝብ ደም ሲመጡ ማታ እየገደሉ።
  የትናንቱን ታሪክ መዝግቦታል አለ፤
  እነማን ተገድለው ማን እንዳስገደለ።
  ወገን ሲሻ ርቆ የዕለት እንጀራውን፤
  ሰላሙን ሰርቀውት ንብረት ያፈራውን፤
  ባገሩ አዋርዶ ባሪያ-ሁን ያለውን፤
  አህያውን ፈርተን-ለምን ዳውላውን? ? ?
  እናም እናስተውል እንወቅ ለይተን፤
  ቅማሎቹን ትተን፣
  አንጠግብም ፎክተን።
  ይኸውና ደግሞ ግድያቸው ዘልቆ፤
  በስደትም ታየ ባደባባይ ታውቆ።
  እኮ ጀርባ ማከክ በስቃይ መማቀቅ፤
  ቅማሏ ደም መጥጣ ጥጉን ስትደበቅ፤
  እዚህ እዚያ ቢፎከት ሺህ ቢገላበጡ፤
  ቅማሎቹም በዝተው ደሙን እየጠጡ፤
  መፎከቱ ብሶ ቆዳን መላጥ ሲደርስ፤
  ደም መክፈሉ አይቀርም እስካልሞተች ድረስ።
  እናም እስከመቼ ችግሩን ስታዩ፤
  ምክንያት ከሰበብ ቀራችሁ ሳትለዩ።
  በሰበቡ ጮኸን ውግዝ ብንለውም፤
  በቁም ከመሞት ቢሻል:-
  መፍትሔ አይኖረውም።
  ምሥጢሩ ይሄው ነው የአህያ የዳውላው፤
  ፍርሃት ነፃነትን ባሪያ አድርጎ በላው።
  ወገን አርቆ-ሲሻ የዕለት እንጀራውን፤
  ሰላሙን ሰረቁት ንብረት ያፈራውን፤
  ባገሩ አዋርዶ ባሪያ-ሁን ያለውን፤
  አህያውን ፈርተን-ለምን ዳውላውን? ? ?
  ለምን’ስ ይዋሻል በሰበብ አስባቡ፤
  አጋዚ ቅማሏ ቆማ ካጠገቡ፤
  የምን መፎከት ነው ይለይለት እንጂ፤
  ወያኔ ይፈራርስ በሕዝብ አመፅ-ፈንጂ።
  እናም እናስተውል እንወቅ ለይተን፤
  ቅማሎቹን ትተን፣
  አንጠግብም ፎክተን።

  +++++++መታሰቢያነቱ+++++++++
  በሳውዲና በዓለም ላይ
  በስደት ላይ ለሞቱና አሁንም ለሚሰቃዩ ወገኖቼ።
  ተገጣጠመ፣
  ሕዳር ፬ ፳፻፮