በኦታዋ ኢሳትን ለመርዳት ከ6500 ዶላር በላይ ተሰበሰበ

የኦታዋ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን፡ ከአርብ ኤፕሪል 29 እስከ ቅዳሜ ኤፕሪል 30 ባደረጉት የተሳካ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት የወርሀዊ መዋጮ ቅጽ የሞሉትን ሳይጨምር ከስድስት ሺህ አምስት መቶ ብር መሰብሰባቸውንና ከዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ጋርም የተሳካ ውይይት ማድረጋቸው ተገለጸ።

ከዝግጅቱ አስተባባሪዎች አንዱ ወጣት ተክለሚካኤል እንደገለጸው በዚህ በሁለት ቀን በተካሄደው ዝግጅት በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በሁለት ቀን በተሰናዳው ዝግጅት ላይ ተገኝተው የገንዘብ እርዳታ ከማድረጋቸውም በላይ በወቅታዊ የአገራችን ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ በሰሜን አፍሪካና በመካከለኛው ምስራቅ አገራት መገናኛ ብዙሀን እየተጫወቱ ያሉትን ወሳኝ ሚና መሰረት አድርገው አሁንም በነጻነት ትግላችን ለማሸነፍ ነጻ መገናኛ ብዙሀን አስፈላጊ መሆናቸውን ገልጸው፡ ብቸኛው የኢትዮጵያዊያን ሳተላይት ቴሌቪዥን በህይውት እንዲቆይና ግቡን እንዲመታ ሁሉም በያለበት መተባበር እንዳለበት የሚያሳስብ ንግግር አቅርበዋል።

የሳቸውንም ንግግር ተከትሎ አንዳንድ ከዝግጅቱ ጋር ግንኙነት የሌላቸው ጥያቄዎች ቢጠየቁም ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ሰፊ ማብራሪያና በማስረጃ የተደገፈ መልስ ሰጥተዋል። በተለይም ሰሞኑን ለመገንጠል ከሚታገሉ እንደ ኦነግና ኦብነግ ያሉ ሀይሎች ጋር የሚያደርጉትን ውይይት በተለመከት ተጠይቀው ሕወሀት ትልቁ ሀገር የመከፋፈል ስልቱ የአንድነት ሀይሎችንና የብሄር ድርጅቶችን ማለያየት በመሆኑ፤ ከዚህ ቀደም “እኛ ኢትዮጵያዊያን አይደለንም” የሚሉ ድርጅቶች አሁን ግን “የኛ ኢትዮጵያዊነት ከሌሎች ያነሰ አይደለም” ሲሉ በደስታ መቀበል እንጂ ከነሱ ጋር ተሰለፋችሁ ተብለን ልንወቀስ አይገባም ብለው አብራርተዋል።

በእለቱ ከዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ጋር በእንግድነት እንደሚገኝ የተጠበቀው ታማኝ በየነ፡ በመጓጓዣ ሰነድ ችግር ምክንያት ለስብሰባው ሊገኝ ያልቻለ ሲሆን ዶ/ር ብርሀኑ ነጋም በረራቸው በመሰረዙ ምክንያት ከሚኖሩበት ከተማ ሌሊት ዘጠኝ ሰዓት ሲነዱ አድረው ኦታዋ ከተማ መግባት እንደቻሉ ታውቋል፡፡ ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ኦታዋ በቆዩበት ሁለት ቀናት ከካናዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤት ሰዎችና ከሌሎች የሰብአዊ መብት ድርጅት ተወካዮች ጋር ንግግር ማድረጋቸውም ታውቋል። ስለሁለቱ ቀን የኦታዋ የኢሳት ርዳታ ማሰባሰቢያ ዝግጅትና ህዝባዊ ውይይት ሰፊ ሪፖርት እንደሚቀርብ አዘጋጆቹ ጠቁመዋል።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on May 2, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.