በእሁዱ ጨዋታ 3 ታዋቂ የናይጄርያ ተጫዋቾች አይሰለፉም

(EMF) ወደ አለም ዋንጫ ግጥሚያ ለሚወስደው ወሳኝ ፍልሚያ፤ የኢትዮጵያ እና የናይጄርያ ቡድኖች በመጪው እሁድ አዲስ አበባ ላይ ይጫወታሉ። በአንዳንድ የውጭ ድረ ገጾች ላይ፤ “ማን ሊያሸንፍ ይችላል?” የሚል የጥናት ናሙና (Poll) እየተደረገ ነው። በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ ናይጄርያን የማሸነፍ እድሏ 10 በመቶ መሆኑን ከዚህ ጥናት መረዳት ተችሏል። በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንም ሆነ አሰልጣኙ የእሁዱን ጨዋታ ሊያሸንፉ እንደሚችሉ በርግጠኝነት በመናገር ላይ ናቸው።

Ethiopia VS Nigeria

Ethiopia VS Nigeria

የኢትዮጵያዎቹ ጥቁር አንበሶች ከሁለት ሳምንት በፊት፤ የአካል ጥንካሬ ሲሰሩ ነበር። ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ደግሞ በቴክኒክ ላይ አተኩረው ስልጠና ወስደዋል። በዚህ ሳምንት ደግሞ ሁለቱንም በማዋሃድ የአካል እና ቴክኒክ ስልጠና እየተሰጣቸው መሆኑን አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ተናግሯል። በንግግሩ መጨረሻም፤ “እኔ ብራዚል የምትባለው አገር ሄጄ አላቅም። ከነቡድኔ እዚያ መሄድ እፈልጋለሁ።” ብሏል። ተጫዋቾቹ በሙሉ በሚገርም ሞራል ውስጥ ናቸው፤ ሁሉም ናይጄርያን እንደሚያሸንፉ በርግጠኝነት ሲናገሩ ይሰማል።

ይህ በ እንዲህ እንዳለ ነው እንግዲህ፤ ከናይጄርያ ደግሞ አሳዛኝ ዜና የተሰማው። ሶስት ታዋቂ ተጫዋቾቻቸው ከዚህ በፊት ቢጫ ካርድ በማየታቸው፤ በአዲሳባው ጨዋታ ላይ አይሰለፉም። ግብ አግቢያቸው ኢማኑኤል ኤምኒክ፣ ተከላካዮቹ ኤልደርሰን እና ጋድፍሬ ኦቦቦና በመጪው ጨዋታ ላይ አይሳተፉም። ይህ ለኢትዮጵያ ቡድን ጥሩ አጋጣሚን ሊፈጥር ይችላል። ስለ ናይጄርያ ቡድን ጥንካሬ ብዙ ሊባል ይቻላል። ካለፈው የአፍሪካ ዋንጫ በኋላ፤ ስለኢትዮጵያውያኑ ግን አንድ ትንሽ እና አስፈሪ ነገር ይባላል – “The giant killers”  እያሉ ይጠሯቸዋል። እናም የመጪው እሁድ ጨዋታ፤ የዳዊት እና የጎልያድ ያህል ትልቅ ልዩነት ያለው ቢሆንም፤ “The giant killers”  ሊያሸንፉ የሚችሉበት አጋጣሚ ሊፈጠር ይችላል። ለሁሉም ግን እስከ እሁድ ሞራል በመስጠት እና በጸሎት ጭምር እናስባቸው።

 

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on October 8, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

4 Responses to በእሁዱ ጨዋታ 3 ታዋቂ የናይጄርያ ተጫዋቾች አይሰለፉም

 1. sami

  October 9, 2013 at 7:10 AM

  You need to check your source for this article. I believe those three players had their first yellow cards. The news states that if these players get yellow cards, then they wont be playing on the second leg of the match that will be held in Nigeria. But, they will be playing in addis. Getaneh will not be playing on sunday due to his injury. Good luck waliyas.

 2. Angolela

  October 9, 2013 at 10:00 AM

  Ethiopia streches both hands to the almighty God for Walias to win. Nothing is impossible!!

 3. girum teshome

  October 10, 2013 at 7:07 PM

  በዚህ ጨዋታ ናይጄሪያ ኢትዮዽያን 3 ለአንድ አሳምራ ታሸንፋለች::

 4. Asheber Asamenew

  October 12, 2013 at 5:12 PM

  I wish good luck to Ethiopian team.
  I hope they will win the game 1/0.
  Let God be with them.
  Asheber from DC.