በኢትዮጵያ የዋጋ ማስተካከያ የኬንያ ነጋዴዎችን ኪሳራ ውስጥ ከተተ! ወደ ኢትዮጵያ ምርታቸውን መላክ ያቆማሉ!

(ኢትዮ እማማ) የወያኔ መንግሥት ከገና ዋዜማ ጀምሮ ተግባራዊ ባደረገው የዋጋ ቅነሳ መመሪያ መሠረት በሸቀጣ ሸቀጥ ችርቻሮ ንግድ ላይ የተሠማራ የሀገሪቱ ነጋዴዎች ብቻ ሳይሆኑ ወደ ኢትዮጵያ ምርቶቻቸውን የሚልኩ ነጋዴዎች በአሁኑ ወቅት ኪሳራ እያጋጠማቸው መሆኑን ገለጹ።

የኬኒያ ጅምላ ላኪ ነጋዴዎች በሚሊዮን የሚጠጋ ሽልንግ ኪሳር ውስጥ መግባታቸውን ዘ ስታንደርድ የተሰኘው ጋዜጣ ገለጸ። እንደ ጋዜጣው ዘገባ ኬኒያ ውስጥ ከሚመረቱት ውስጥ ሳሙና፣ ፓስታ ፣ማካሮኒ፣ዘይትና የዱቄት ወተት ላይ ኪሳራ ማምጣቱን ገልጿል።

የአምራቾች ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት ፖላይ ካርፕ ኢጋዚ ለጋዜጣው እንደገለጹት “የኢትዮጵያ መንግሥት ያወጣው የአንዳንዱ የዋጋ ተመን የዓለም አቀፍ ገበያን የማከለ አይደለም” ባይ ናቸው።

በዚህም የተነሳ በኬንይ ውስጥ በብዛት የሚመረተው ፓስታ ፣ማካሮኒ፣ዘይትና የዱቄት ወተት ላይ በላኪውች ዘንድ ከፍተኛ ኪሳራ አምጥቷል ። ይሁንና በሳሙና ፣በስክርቢቶ፣በደብተር፣በጫማ፣በሕክምና መድሐኒቶች ወዘተ. ላይ ግን የወጣው ዋጋ ተመጣጣኝ ስለሆነ በነዚህ አምራቾች ላይ ችግር አልማምጣቱን ጋዜጣው ገልጿል።

የአምራቾች ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት ፖላይ ካርፕ ኢጋዚ የኢትዮጵያ መንግሥት ያወጣውን የዋጋ ተመን እንደሚያስተካክል ተሰፋ እንደሚያደርጉ ገልፀው ይህ ካልሆነ ግን በኬኒያ አምራቾች ላይ ይህ ነው የማይባል ኪሳራ ሊያመጣ ይችላል ብለዋል።

ይህ ማለት ደግሞ የኬንያ አምራቾች ይህ ከመሆኑ በፊት የራሳቸውን እርምጃ ሊወስዱ ይችላሉ። ነጋዴዎቹ ዋጋውን አሳንሰው ለመሸጥ ስለማያዋጣቸው ወደ ኢትዮጵያ የሚልኩትን ምርታቸውን ሊያቆሙ አሊያም ሊቀንሱ ይችላሉ። በዚህም የተነሳ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በጎረቤት ሀገሮች ጭምር የኑሮ ውድነትንና ስራ አጥነትን ጭምር ሊያባብሰው እንደሚችል ከወዲሁ ተገምቷል።

የዋጋ ማስተካከያ በየትም ዓለም ያል ቢሆንም የወያኔ መንግስት መጀመሪያ የራሱን የውስጥ ችግሮች ሳይፈታ ማለትም ከነጋዴ ጋር አብሮ እኩል ከመቸርቸር አልፎ ነጋዴውን ተገቢ ባልሆነ በየኬላ ጣቢያዎች ተገቢ ያልሆነ ቀረጥ ማስከፈል፣ የአቅርቦት ችግር አለመቅረፍ፣የገንዘብ አቅምን ማዳከም፣ብሔራዊ ባንኩ ለልምት እያለ በርካታ ገንዘብ አላግባብ እንዲፈስ ማድረግ ፣ በስማ በለው በየአመቱ በርካታ በጀቶችን መመደብ፣ ወዘተ. የመሳሰሉትን ችግሮች በየአመቱ እንደተሸከመ ፤ለሕዝብ አሰቢ በመምሰል ዳሩግን እድሜውን ለማርዘም ሲል ብቻ ዛሬ ደግሞ ነጋዴን ከሕዝብ ለማባላት የዘየደው ዘዴ ካልሆነ በስተቀር በአሁን አካሄድ የምስጊኑን ሕዝብ ችግር ይቀርፋል ብሎ የሚያስብ ወገን ካለ የዋሀ መሆኑን ባለሙያተኞች ያሰምሩበታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአዲስ አበባ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ 103 ንግድ ቤቶችን መዝጋቱን ሮይትርስ ዛሬ ገለፀ። ንግድ ቤቶቹ የተዘጉት በመንግሥት ከተተመነው ዋጋ በላይ በመሸጣቸውና የዋጋ ዝርዝር ባለመለጠፋቸው እንዲሁም ደብቀው በመጋዘናቸው ውስጥ በማከማቸታቸው እንደሆነ የአዲስ አበባ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ዳሪክተር ሺሰማ ገብረስላሴ ገለፀዋል፡፡ ይህ የመጀመሪያ እርምጃ እንደሆነና በቀጣይነት እንደሚቀጥልና የንግድ ፍቃዳቸው እስከመሰረዝ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ተናገረዋል ፡፡

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on January 13, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.