በኢትዮጵያ ህዝባዊ አመጽ እንዳይነሳ አሜሪካ ጥረት ጀመረች

EMF – በሰሜን አፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ እየተቀጣጠለ ያለው ህዝባዊ አመጽ በኢትዮጵያ እንዳይቀጥል በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ጥረት እያደረገ መሆኑ ታወቀ:: አዲስ ነገር ምንጮቹን በመጥቀስ ይፋ እንዳደረገው: ከሰሜን እየተጓዘ ጅቡቲ የደረሰው ህዝባዊ አመጽ በኢትዮጵያ ውስጥም ሊቀጣጠል እንደሚችል ምልክቶች እና ይህንንም የሚያሳዩ ፍንጮች እንዳሉ ጠቁሟል::

ይህንን ህዝባዊ አመጽ ከወዲሁ ለመግታት እንዲያስችል የአሜሪካ ኤምባሲ የተቃዋሚ ሃይሎችን ከአንባገነኑ የመለስ መንግስት ጋር ለማወየየት ቀነ ቀጠሮ መያዙ ተዘግቧል:: የህዝብ ድምጽ ሲዘረፍ: ሰላማዊ ዜጎች ሲገደሉ: ወዘተ… ዝም ብሎ የነበረው የአሜሪካ ኤምባሲ አሁን ተቃዋሚዎችን ለውይይት መጥራቱ ለምን እንዳስፈለገ ለብዙዎች ግልጽ ነው::

የአሜሪካንን እና የምእራባውያንን አጀንዳ እያስፈጸመ ያለው መለስ ዜናዊ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ ከተነሳ እንደመለስ ያለ የሀገርን እና የወገንን ጥቅም በገንዘብ የሚለውጥ ታማኝ አገልጋይ ሊኖር አይችልም የሚል ስጋት አላቸው::

በቅርቡ ዊኪሊክ በርሊንን ዋቢ በማድረግ ይፋ እንዳደረገው መለስ ዜናዊ በኢኮኖሚክስ እውቀት ደንቆሮ ይሁን እንጂ ለምእራቡ መንግስታት ፍጹም ታማኝ አገልጋይ መሆኑን ዘግቧል::

ከዚያ አስቀድሞ የወጣው የዊኪሊክ ሰነድ: መለስ ሶማልያን እንዲወር ከአሜሪካ መንግስት ቀጭን ትእዛዝ እንደደረሰው ይተነትናል:: የአሜሪካ መንግስት የሶማሌን ወረራ በይፈ እያወገዘ በድብቅ ግን መለስን ይህንን ቆሻሻ ስራ እንዲሰራ በስውር ያዝዘው እንደነበር ዊኪሊክስ ይፋ አድርጓል::

አሜሪካ ዛሬ በኢትዮጵያ ውስት ህዝባዊ አመጽ እንዳይነሳ ጥረት ማድረጓ የሚያስገርም ጉዳይ አይደለም:: በአደባባይ እያዋረዱት ነገር ገን ቆሻሻ ስራቸውን ሊሰራላቸው የሚችል መሪ በታሪክ ቢኖር መለስ ዜናዊ ብቻ መሆኑን የታሪክ ሰዎች ይመሰክራሉ:: የአሜሪካንን ፖሊሲ ሊያስፈጽሙ ሶማሌ ላይ ህይወጣቸውን ስላጡ በሺዎች የሚቀጠሩ ወገኖቻችን ጉዳይ መለስ ዜናዊ በፓርላማ ተጠይቆ: “ለህዝብ ተወካዮች” የሰጠው ምላሽ: “ይህ እናንተን አይመለከታችሁም!” የሚል ነበር::

መለስ ከምእራባውያን ለሚያገኘው ፍርፋሪ ሲል ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አፍሪካንም ማዋረዱን አንድ የዊኪሊክስ ኬብል ይፋ አድርጓል:: አፍሪካውያን ኢትዮጵያን አምነው በአለም ዓቀፉ የአካባቢ ጥበቃ ጉባኤ ላይ እንዲሳተፍ መለስን ኮፐንሃገን ልከውት እንደነበር የሚያወሳው ይኽ የዊኪሊክ ምስጢር: መለስ አስቀድሞ ከአሜሪካ መንግስት ጋር በሚስጥር ባደረገው ስምምነት የአፍሪካን ጥቅም በገንዘብ አሳልፎ መስጠቱን ዘግቧል::

እንደመለስ ዜናዊ በወረደ ደረጃ አይሁን እንጂ የቱኒዝያም ሆነ የግብጽ አንባገነን ገዢዎች በገንዘብ እየተደለሉ የአሜሪካ ፖሊሲ አስፈጻሚዎች ነበሩ:: የህዝብ ሃይል ሲበረታ እና የአንባገነኖቹ ጉልበት ሲፈታ ስትመለከት አሜሪካም በአንባገነኖቹ ላይ ፊቷን ስታዞርባቸው ታይቷል:: የሃይል ሚዛን ወዳዘነበለበት መሄድ ለምእራባውያኑ አዲስ ነገር አይደለም::

አሜሪካ በግልጽ ያልተገነዘበችው ነገር ቢኖር: በቁም እስር ላይ ያሉ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሃይሎች ከመለስ ዜናዊ ጋር ተነጋገሩም: አልተነጋገሩ ሊመጣ ያለውን ህዝባዊ ቁጣ ሊያቆሙት አይችሉም:: ከሌሎቹ ልምዶች እንዳየነው አመጹን የሚመሩት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሳይሆኑ ብሶቱ የከፋበት ህዝብ ሳይታሰብ ባስነሳው ቁጣ ነው:: በኢትዮጵያ ከምን ግዜውም በላይ እየከፋ የመጣው የኑሮው ውድነት: የሰብአዊ መብት ረገጣ እና አፈናን አሜሪካ ማቆም ከቻለች ሊመጣ ያለውን አመጽ ማቆም ይቻል ይሆናል::

የጠቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችም ካለፉት የወያኔ የማጭበርበር የ “ውይይት” ተሞክሮዎች በመውሰድ ከፍተኛ ጥንቃቄ ካላደረጉ ጉዳቱ በራሳቸው ላይ ሊበረታ ይችላል::

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on February 20, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.