በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ወጥታችሁ ድምጻችሁን ላሰማችሁ ውድ የኢትዮጵያ ልጆች ምስጋና እናቀርባለን።

በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ወጥታችሁ ድምጻችሁን ላሰማችሁ ውድ የኢትዮጵያ ልጆች ምስጋና እናቀርባለን። ነፃነት በነፃ እንደማይገኝ አውቃችሁ ለሀገራችሁ እና ለህዝባችሁ መስዋእትነት ለመክፈል ለቆረጣችሁና ፍርሀትን ለሰበራችሁ የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጆች በመላው አለም ተበትነን የምንገኝ የኢትዮጵያ ወቅታዊ መወያያ መድረክ (ECADF) ታዳሚዎች አድናቆታችንና ምስጋናችንን እናቀርባለን።

በተጨማሪም ይህንን ህዝባዊ ሰልፍ ለጠራው እና ላስተባበረው የሰማያዊ ፓርቲ፣ አባላቱና ደጋፊዎቹ እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲን ጥሪ ለደገፉና ለተባበሩ የፖለቲካና ሲቪክ ድርጅቶች፣ በማህበራዊ መገናኛ መረቦች ስትቀሰቅሱና ስታስተባብሩ ለነበራችሁ ለውጥ አራማጆች ያለንን አድናቆት ልናስተላልፍ እንወዳለን።

እንደተለመደው እኛ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች መወያያ መድረክ (ECADF) የምንሰባሰብ ኢትዮጵያውያን ምንግዜም ከለውጥ አራማጅ ኢትዮጵያውያን ጎን ተሰልፈን የሚጠበቅብንን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደምንቀጥል በድጋሜ ቃል-እንገባለን።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

ሀገራችን ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች መወያያ መድረክ
Ethiopian Current Affairs Discussion Forum (ECADF)

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on June 3, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ወጥታችሁ ድምጻችሁን ላሰማችሁ ውድ የኢትዮጵያ ልጆች ምስጋና እናቀርባለን።

  1. betty

    June 3, 2013 at 3:13 PM

    ECADF, you should stop attacking the entire tigrians and only focus on weyane