በአዲስ አበባ ሕዝባዊ የሰላማዊ ሰልፍ ሊጠራ ነው

May 2005 March in Addis Ababa(25 Jan. 2009) በእስር ላይ ያሉትን የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳን ለማስፈታት የተደረገው ሙከራ በሙሉ በገዢው ፓርቲ ስራ አስፈፃሚዎች አማካኝነት ተገቢውን ምላሽ ባለማግኘቱ ሰለማዊ ሰልፍ ለመጥራት በመዘጋጀት ላይ መሆኑን አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ አስታወቀ፡፡ የታሰሩበትን አንደኛ ወር አስመልክቶም በርቲው ጽ/ቤት ውስጥ የሻማ ማብራት ስነስርአት ይካሄዳል፡፡

የወ/ሪት ብርቱካን ጠበቃ ደንበኛቸውን ለማነጋገር በተደጋጋሚ ወደ ማረሚያ ቤት ቢሄዱም ፍቃድ አግኝተው ደንበኛቸውን ለማነጋገር ባለመቻላቸው፤ የሊቀመንበሯ ዘመድ፣ ወዳጅና ደጋፊ እንዲጎበኛቸው አለመፈቀዱ፤ እስካሁን ሁለት በሁለት በሆነ ቆርቆሮ ቤት ውስጥ ለብቻቸው መታሰራቸው ፓርቲውን ሰላማዊ ሰልፍ ለመጥራት እንዳስገደደው ያገኘነው መረጃ ያለመክታል፡፡

የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ዶ/ር ሀይሉ አርአያ ስለጉዳዩ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ እንዳስታወቁት ሰልፉን ለመጥራት መዘጋጀታቸውን ጠቅሰው ‹‹ሰልፉን የምናደርገው ህጉን ጠብቀን ይሆናል›› ብለዋል፡፡ ጨምረውም የወ/ሪት ብርቱካን ጠበቃ ደንበኛቸውን እንዳያገኙ መከልከላቸውን አስመልክቶ የፍትህ ሚንስቴር አስተዳደራዊ እርምጅ እንዲወስድ ለመጠየቅ ማሰባቸውን ገልፀዋል፡፡

ወ/ሪት ብርቱካን ከታሰሩበት ጊዜ አንስቶ ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ለመነጋገር ጥረት ሲደረግ ቢቆይም እስካሁን የሀገር ሽማግሌ ተብዬዎቹንም ሆነ ተወካዮችቸውን አግኝቶ ለማነጋገር አልተቻለም፡፡ የሊቀመንበሯ መታሰር በሀገር ውስጥና በውጭ ሚዲያዎች ሽፋን ያገኘ በመሆኑ እንዲሁም የፓርቲው አመራሮች ከሽማግሌዎቹ ጋር ለመነጋገር ሙከራ ማድረጋቸው እየታወቀ ምንም ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ አለመሆናቸው አሁንም መነጋገሪያ እንደሆነ ነው፡፡ ፓርቲውም በዚህ በኩል እንዳልተሰዳካለት በተደጋጋሚ አስታውቋል፡፡

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on January 26, 2009. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.