በአዲስ አበባና አካባቢዋ የጅብ መንጋ ሰዎችን መብላቱ በምልኪነት እያነጋገረ ነው -ነፃነት ዘለቀ (ከአዲስ አበባ)

ሙከራውን ማድረጉ ቢያንስ ኪሣራ የለውም፡፡ ውጤታማነቱን ግን እጠራጠራለሁ ብቻ ሣይሆን እንዲያውም መሣቂያ እንዳያደርጉን እሰጋለሁ፤ ክፉዎችና በሰው ስቃይ የሚደሰቱ ስለሆኑ በእሪታችን ቢሣለቁብን ማን ይከሳቸዋል? ከስም ባለፈ የሰላምን ምንነት ከማያውቅ ወያኔ በሰላማዊ መንገድ ችግርን ማስረዳትና መፍትሔ ለማግኘት መመኘት ከምኞትና ከህልም አያልፍም፡፡ እናም ወያኔን በእሪታ ለማስበርገግ የሚቻል አይመስለኝም፤ ተስፋ ለማስቆረጥ አይደለም – ተስፋ ብሎ ነገር ቀድሞውንም ከሀገራችን ከጠፋች ሰንብታለችና ማንም ማንንም ተስፋ ሊያስቆርጥ አይቻለውም፡፡ መቼም የጨነቀው እርጉዝ ያገባል ነውና ወደአእምሯችን የመጣልንን ዘዴ ሁሉ አሟጠን መጠቀሙን የመደገፍ የሞራል ግዴታ ስላለብን እንጂ በአራት ከተሞች አይደለም በአራት መቶ ከተሞች እሪታችንን ብናቀልጠው ወያኔ ንቅንቅ አይልም፤ በጩኸታችን ከማላገጥም በዘለለ አንጀቱ በሀዘኔታ አይላወስም፡፡ የጅቦች ስብስብ በጩኸት እሩምታ ሣይሆን በአልሞ ተኳሽ አናብስት ነው የማያዳግም እርምጃ ሊወሰድበት የሚገባ፡፡ ዓሣማው ወያኔ በሰላማዊ መንገድ ይወገዳል ወይም በምርጫ ሥልጣኑን ያስረክባል ብላችሁ ተጃጅላችሁ የምታጃጅሉ ወገኖች ካላችሁ – እንዳላችሁም ይታወቃል – ሕዝብን ከምታነሆልሉ ሌላ አማራጭ ብትፈልጉ ይሻላልና ጊዜና ምኞትን አታባክኑ፡፡ Continue reading –>

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on March 27, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to በአዲስ አበባና አካባቢዋ የጅብ መንጋ ሰዎችን መብላቱ በምልኪነት እያነጋገረ ነው -ነፃነት ዘለቀ (ከአዲስ አበባ)

  1. andnet berhane

    March 29, 2014 at 9:33 PM

    እሪታ ማስበርገጊያ ሊሆን አይችልም ነፃነት ዘለቀ እውነትና የማይታበል የደፋር ጀግኖች ቃል ነው:: ነገርግን ተጅጃሎ በእሪታ መቆም ወያነን ባዶ ጉልበቱን ጠንካራ ማስመሰል ይሆናል: ነገግን እውንና የሕዝብ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል እንድ ዩክሬን ሕዝብ ብርድና ቁር ረሃብና ጥም ጨላማንና ብርሃንን በመፈራረቅ የሚፈልገውን ለውጥ ለማስገኘት በራሱ ፍላጎትና የሃገርሩን ክብርና የወገኑን ምሬት የተጫነበትን እገዥዎች ድፍረት በጽናት ታግሎ ውጤት ማስገኘቱ ለዓልም ሕዝብ አሳይቷል: እኛም እንደ ሕዝብ ስለ ራሳችንና ስለሀገራችን የሚጠበቅብንን መስዋእትነት የመክፈል ግዴታ አለብን ነጻነት በነጻ እንደሌለ አውቀን እንደ አበው በቆራጥ በጽናት ታሪክ ለማደስ ያስፍፈልጋል: