በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች የተነሱ ጥሪ ወረቀቶች መበተናቸው ቀጥሉአል

April 14, 2011 -በኢትዮጵያ ላይ የተጫነው ግፈኛና ዘረኛ አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያዊያን ትከሻ ላይ ተሽቀንጥሮ ይውድቅ ዘንድ ግፊቱና ህዝብንም ለዚሁ ትግል የማያነሳሳ ጥሪ መቅረቡ ተጡዋጡፎ መቀጠሉን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ባወጣው ዘገባ ገለጸ::

እንደ ኢሳት ዘገባ በአዲስ አበባ ከተማ ከተበተኑት ጽሁፎች ውስጥ አባይ ወንዝን በላያችን ላይ ያለውን የአምባገነንነት ቀምበር ካስወገድን በሁአላ እንሰራዋለን የሚል እንደሚገኝበት ተገልጹአል::

ከበርካታ ቀናት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የተለያዩ ቀስቃሽ ወረቀቶች በየግድግዳው እንደሚለጠፉና ሲበተኑም እንደነበር በተደጋጋሚ የተዘገበ ሲሆን ሰሞኑን ደግሞ በቃ የሚሉ ጽሁፎ በየመንገዱ ተበትነው እንደሚገኙ ይህንም ወረቀት ማን እንደበተነ አጋልጡ በመባል ሴተኛ አዳሪዎች እየታሰሩ መሆኑን ኢሳት ምንጮቹን በመጥቀስ ዘግቡአል::

ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ በተለይም የሰሜን አፍሪቃው ህዝባዊ አብዮት ከተቀሰቀሰ ወዲህ በሃገር ውስጥ ያለው እንቅስቃሴ እጂግ እያስፈራውና እያስጨነቀው እንደመጣ ሲዘገብ የቆየ ሲሆን ከዚህ ጭንቀት መውጫ መንገድ አድርጎ እየወሰደ ያለው ርምጃም ንጹሃን ዜጎችን በጂምላ ወደ እስር ቤት ማጎር እንደሆነ በርካታ የዜና አውታሮች የዘገቡት መሆኑ ይታወቃል::

ከስድስት ኪሎ ወደ ጊዮርጊስ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው የሃብተ ጊዮርጊስ ድልድይ (አፍንጮ በር ድልድይ) ላይ ሞት ለወያኔ የሚል ጽሁፍ በትላልቅ ፊደላት ተጽፈው እንደነበር መግለጻችን ይታወሳል ፣፡ በራሪ ወረቀት በከተማ ውስጥ የመበተኑ ሥራ ተፋፉሞ በመቀጠል ሰሞኑን በመርካቶ ውስጥ እየተበተነ እንደሆነ ለማረጋገጥ ተችሎአል።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on April 15, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.