UPDATED NEWS: በአምስት ከተሞች የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ሁኔታ (የመቐለው ተሰረዘ፤ በሌሎች ከተሞች ሰልፉ ተጀምሯል!)

EMF – በአንድነት ፓርቲ አስተባባሪነት – ዛሬ በመቐለ፣ በባህር ዳር፣ በጅንካ፣ በወላይታ እና በአርባ ምንጭ ሊደረግ የታቀደው ሰላማዊ ሰልፍ ልዩ ልዩ እንከኖች ቢያጋጥሙትም፤ አሁን በባህር ዳር የሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ የተጀመረ መሆኑን ለማወቅ ችለናል። በመቐለ ሊደረግ የነበረው ስብሰባ በህወሃት ሰዎች የሃይል እርምጃ ሊደረግ አልቻለም። ህወሃት በስፍራው የተገኙትን የአንድነት ፓርቲ አመራር አባላት አስሯቸዋል። በመሆኑም ስብሰባውን ማድረግ አልተቻለም። በህጋዊ እና በሰለጠነ መንገድ እየተንቀሳቀሱ ያሉትን የሌላ ፓርቲ ሰዎች ማሰር፤ ያለመሰልጠን አንደኛው ምልክት ሆኖ አልፏል።

በጅንካ የሚደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማክሸፍ በሺ የሚቆጠሩ ታጣቂ ሃይሎች የከተማውን ዋና ዋና ጎዳናዎች በመቆጣጠር ህዝቡን እያሸበሩት ቢሆንም፤ ሰላማዊ ሰልፉ ግን በአሁኑ ሰዓት እየተከናወነ ነው። በወላይታ የአመራር አባላቱን አፍኖ ማሰር ብቻ ሳይሆን፤ ከአስተባባሪዎቹ ልጆች አንዱን አፍነው ወስደውታል። በአርባ ምንጭ ቅስቀሳ ሊደረግባት የነበረችው መኪና ጎማዎች ሙሉ ለሙሉ እንዲተነፍስ ቢደረግም ሰላማዊ ሰልፉ ግን እየተከናወነ ነበር። ሆኖም የፖሊስ እና የደህንነት አባላት ሰልፉ መሃል ገብተው እየበጠበጡ እና አስተባባሪዎቹን “እንገላችኋለን!” በማለት እያስፈራሯቸው ነው – ሌላው ያለመሰልጠን ምልክት!!

Bahr dar

Bahr dar


በወላይታ ሶዶ ህዝቡ የተጠራው ለሰላማዊ ሰልፍ ሳይሆን ለህዝባዊ ስብሰባ ነው። ታጣቂዎች ህዝቡ ወደ ስብሰባ አዳራሽ እንዳይሄድ ቢከለክሉም፤ ህዝቡ ግን፤ “መብቴ ነው!” እያለ ነበር ወደ አዳራሹ እየጎረፈ የሄደው። ለዚህም ነው፤ ስብሰባው በተጀመረበት ወቅት ሰብሳቢው፤ ህዝቡን “ጀኖች ናቹህ! ጀግኖች ናቹህ!” በማለት ንግግግራቸውን የጀመሩት። በወላይታ ሶዶ የታሰሩትን የአንድነት ፓርቲ ተጠሪ ወ/ሮ ሃድያንም በዚህ አጋጣሚ አስታውሰዋል። ስብሰባው ሞቅ ደመቅ ብሎ እንደቀጠለ ነው።
በባህርዳር መንግስታዊ ውንብድና እየተከናወነ ይገኛል። በባህር ዳር የመንግስት አካላት አረንጓዴ ሽብር የሚል ወረቀት እየተበተኑ ናቸው። “አረንጓዴ ሽብር” የሚል በነጭ ወረቀት የተባዛ እና የአንድነትን የስልክ ቁጥር የያዘ በራሪ ወረቀት እየተበተነ መሆኑ ታውቋል፡፡ አንድነት ፓርቲ የበተነው በራሪ ወረቀቶች ቢጫና ቀይ ብቻ መሆኑ ይታወቃል፡፡
Bahr dar

Bahr dar


በባህር ዳር ህዝቡ ሲያሰማቸው ከነበሩት መካከል…. ያማራው ህዝብ ጨዋ እንጂ ፈሪ አይደለም! ለሱዳን ተቆርሶ የተሰጠው መሬታችን ይመለስ! የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ባስቸኳይ ይፈቱ! እስክንድር ነጋ ጋዜጠኛ እንጂ አሸባሪ አይደለም።! የሚጠቀሱ ናቸው።
አንድነት ፓርቲ በባህር ዳር የጠራው ሰላማዊ የተዋውሞ ሰልፍ በድምቀት ከመጠናቀቁ በፊት፤ የምዕራብ ጎጃም የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ ማሩ ንግግር ካደረጉ በኋላ የዝግጅቱ ፍጻሜ ሆኗል፡፡

bahrdar

በሁሉም ስፍራዎች እየተደረገ ያለው የኢህአድጋውያን ህገ ወጥ እርምጃ ብስለት እንደሚያንሳቸው ብቻ ሳይሆን ዛሬም አለመሰልጠናቸውን በጉልህ የሚያሳየን መስታወት ሆኗል። በዚህ ሁሉ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ አንድነት ፓርቲ ቅስቀሳውን እና ሰላማዊ ሰልፉን ለማድረግ ሙከራውን እንደቀጠለ ነው። ከላይ እንደገለጽነው፤ ከመቐለው ስብሰባ በቀር በሌሎቹ ከተሞች ከአፋኝ ሃይሎች ጋር እየተፋለሙ ሰላማዊ ሰልፉን ለማድረግ የሚደረገው ጥረት እንደቀጠለ ነው።
በጂንካ እየተደረገ ያለው ሰላማዊ ሰልፍ እስካሁን ምንም እንከን ሳያጋጥመው በሰላም በመካሄድ ላይ ይገኛል።
bahrdar2
በጂንካና በባህርዳር እየተስተጋቡ ያሉ መፈክሮች በከፊል
==========================================
• የታሰሩ የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች ይፈቱ
• መንግስት ህገ-መንግስቱን ያክብር
• መንግስት በኃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን ያቁም!
• መንግስት ለብሄራዊ መግባባት ባስቸኳይ መልስ ይስጥ!
• ውሸት ሰልችቶናል! ይቁም!!!
• የጸረ – ሽብር ህጉ ባስቸኳይ ይሰረዝ!
• ዘርን መሰረት ያደረገ ማፈናቀል ባስቸኳይ ይቁም!!
• ሙወስና የስርአቱ መገለጫ ነው!!
• የአባይ ጉዳይ የኢትጵያ ሕዝብ ነው!
• ለተከሰተው የኑሮ ውድነት ተጠያቂው መንግስት ነው!!
• የዜጎች ሰብአዊ መብታቸውን የማግኘት መብታቸው ይከበር!!
• ዜጎች በሀገራቸው ስራ የማግኘት መብታቸው ይከበር!!
• በአባይ ጉዳይ ወሳኙ የኢትጵያ ሕዝብ እንጂ ግብጾች ይደሉም!!
• የፓርቲ አባልነት በፍላጎት መሆን አለበት!!

 

ለአርባምንጭ ሰላማዊ ሰልፍ በቅስቀሳ ላይ መሰማራቷ ያልተወደደላት መኪና እንቅስቃሴዋን ለመግታት ከ6 የቱሪስት መኪናዎች ተለይታ 4ቱም ጎማዎቿ ተንፍሰው ተገኙ ለሴቻ ወረዳ ፖሊሶች ሪፖርት ቢደርሳቸውም የበላይ አካል ካላዘዘን መጥተን ልንመለከት አንችልም የሚል ምላሽ በመስጠት የአለቆቻቸውን ትዕዛዝ እየተጠባበቁ ነው፡፡ (Photo source: Abugida)

ለአርባምንጭ ሰላማዊ ሰልፍ በቅስቀሳ ላይ መሰማራቷ ያልተወደደላት መኪና እንቅስቃሴዋን ለመግታት ከ6 የቱሪስት መኪናዎች ተለይታ 4ቱም ጎማዎቿ ተንፍሰው ተገኙ ለሴቻ ወረዳ ፖሊሶች ሪፖርት ቢደርሳቸውም የበላይ አካል ካላዘዘን መጥተን ልንመለከት አንችልም የሚል ምላሽ በመስጠት የአለቆቻቸውን ትዕዛዝ እየተጠባበቁ ነው፡፡ (Photo source: Abugida)

በመቐለ ሰላማዊ ሰልፉ ለአሁኑ ይሰረዝ እንጂ ወደፊት የሚደረግ መሆኑን ፓርቲው አሳውቋል። በአሁኑ ወቅት የአመራሩ መታሰር ብቻ ሳይሆን ንብረታቸው በታጣቂዎች መዘረፉም በጣም የሚያሳዝን ነው። ከምንም በላይ ግን፤ “ለመብት እና ለነጻነት ታግለናል” የሚሉት ህወሃቶች እንዲህ ያለ ድርጊት መፈጸማቸው አሳፋሪም ጭምር ነው። አብርሃ ደስታ በቁጭት ካስተላለፈው መልዕክት መሃል ይሄንን እናስነብባቹህ። እንዲህ አለ… “በትግራይ ሰለማዊ ሰልፍ ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ ነው። ምክንያቱም የትግራይ ህዝብ የደርግን አገዛዝ ለመጣል ብዙ መስዋእት ከፍሏል።
መሰረተ ሓሳቡ:
ብዙ መስዋእት የከፈለ ህዝብ ብዙ ዓፈና ይደርሰዋል። ስለዚህም ብዙ መስዋእት የከፈለ ህዝብ ሰለማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቱ ተነፍጓል።
በሌሎች ክልሎች ቢያንስ ህዝብ ሰለማዊ ሰልፍ እየወጣ ነው። በትግራይ ግን ሰልፍ መውጣት ከድሮ ጀምሮ ወንጀል ተደርጎ ይወሰዳል። ይሄው እስካሁን ድረስ አለ።
አዎ! ብዙ መስዋእት የከፈለ ብዙ ጭቆና ይደርሰዋል። ብዙ መስዋእት ለብዙ ጭቆና!” በሚል ስላቅ አዘል አጻጻፍ ነው የትግራይን ህዝብ አፈና የገለጸው።

በወላይታ የተፈጠረውን አፈና በተመለከተ ደግሞ አቡጊዳ በድረ ገጹ ላይ ሲዘግብ እንዲህ ብሏል። …”አቶ ማሞ ዳሞ በወላይታ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አመራር አባል ናቸው፡፡ለህዝባዊ ስብሰባው ስኬት በማሰብም ሙሉ ጊዜያቸውን በመሰዋት ጠንካራ ስራ ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ማሞ ከዚህ ቀደም በህገ ወጥ መንገድ ሲታሰሩና ሲፈቱ ሁሉንም በጸጋ በመቀበል በሰላማዊ ትግል ሃሳባቸውን ከመግለጽ መንግስት መብቴን ሊያከብር ይገባዋል በሚሉት ሁሉ ያለምንም ፍርሃት ድምጻቸውን በማሰማት በወላይታ ነዋሪዎች ዘንድ አክብሮትን አትርፈዋል፡፡

ዛሬ ከሰዓት በኋላ በሶዶ ቀለም መሰናዶ ት/ቤት አካባቢ ዘንድሮ የ12ኛ ክፍልን ብሄራዊ ፈተና የወሰደ ልጃቸውን በማግኘት ጥቂት ጊዜ አብረውት ካሳለፉ በኋላ በፖሊስ የታሰረች አባልን ለመጠየቅ ወደ ፖሊስ ጣብያ ሲያመሩ ስልካቸው ይጠራል‹‹በስልኩ የሰሙት ሰው ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በአካል ያገኙት ልጃቸው ከባለ ሶስት እግር ባጃጅ ነው በወረዱ ሁለት ሰዎች ታፍኖ የድረሱልኝ ድምጹን እያሰማ መወሰዱን ይነግራቸዋል፡፡

አቶ ማሞ ባጃጁ ሄደበት ወደተባለ ቦታ አጋራቸውን በማስከተል አምርተዋል፡፡ነገር ግን ልጃቸውን ሊያገኙት አልቻሉም፡፡እንዲህ አይነት ድርጊቶች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ለፖሊስ የአንድነት አባላት ሰሞኑን ሲያመለክቱ ቢቆዮም ፖሊስ የምትሉት ቅጥፈት ነው በማለቱ ጥበቃ ሊያደርግ አልቻለም፡፡ወዴት እያመራን ይሆን? የወላይታ ህዝብ በአዳራሽ ውስጥ እንዲሰበሰብና ከደህዴን/ኢህአዴግ የተለየ ሃሳብ እንዳለ በመስማት ያሻውን እንዲመርጥ በመጋበዙ የአቶ ማሞ ልጅ በጠራራ ጸሐይ ታፍኖ መወሰድ አለበት?” በማለት ዘገባውን አጠናቋል።

እስካሁን እየተደረገ ያለውን የክልሎች ሁኔታ ስንመለከት… በትግራይ የዲሞክራሲ ስርአቱ ጨርሶ የሞተ መሆኑን ለመታዘብ ችለናል። ባህር ዳር ሻል ያለ ነው። በወላይታ እና በአርባ ምንጭ የተደረገውን ያልሰለጠኑ ሰዎች ትንኮሳ፤ ከጅንካው ሁኔታ ጋር ስናነጻጽረው፤ የኢህአዴግ ሰዎች የሰለጠነ ፖለቲካ ምን መሆን እንዳለበት ለማወቅ ትምህርት የሚያስፈልጋቸው ይመስላል… ከዚያ አንጻር ሲታይ ደግሞ የጅንካ ህዝብ የተሻለ ስልጡን ሆኖ ተገኝቷል። በዘገባችንም መጨረሻ ህዝቡ የሚነጋገርበት እና ቁርጥ ያለ ምላሽ የሚሰጥበትን ጥያቄ መተው እንሻለን። ኢህአዴግ እና ደጋፊዎቹ በየክልሉ የፈጸሟቸው ድርጊቶች ስልጡን ያሰኛቸዋል ወይስ ኋላ ቀር? ተወያዩበት።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on August 4, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

3 Responses to UPDATED NEWS: በአምስት ከተሞች የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ሁኔታ (የመቐለው ተሰረዘ፤ በሌሎች ከተሞች ሰልፉ ተጀምሯል!)

 1. Pingback: UPDATED NEWS: በአምስት ከተሞች የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ሁኔታ (የመቐለው ተሰረዘ፤ በሌሎች ከተሞች ሰልፉ ተጀምሯል!) | Fitih le Ethiopia

 2. Mesfin

  August 4, 2013 at 7:41 AM

  Brovo Andinet! This is what peaceful struggle means. Now with such determination and brave move you are approaching to the inevitable victory! Tyrants may bring pressure up you but that shouldn’t hinder you from your aim. They thought they will extinguish the light of the struggle when they arrest our hero, Andualem Aragie, but the were wrong. Now Andinet has got millions of Andualems throughout Ethiopia. I can imagine how happy he would be seeing/hearing what his party, Andinet is doing. God bless you guys and God Bless our beloved country, Ethiopia.

 3. andnet berhane

  August 5, 2013 at 1:14 AM

  ማንኛውም የመንግስ መዋቅር በሰለጠነና በተሟላ ያስተዳደር ስነ ምግባር የተሟላ ከሆነ ለሚያስተዳደርው ህዝብ መብቱንና እምነቱን ማክበር ይገባዋል: ሕዝቦች የሚጠይቁት በሃገራቸው የተሳትፎ እኩል የሚታዩበት ፍርድና የስራ እድል ሲነፈጋቸው እንደ ዜጋ በሰልፍ በጽሑፍ በስዕል መጠየቅ ሕገ ምንግስታዊ መብታቸው በመሆኑ ያላንዳች ጥያቄ አቤቱታቸውን ማሰማት ይገባቸውዋል::
  ነገርግን ወአነእ ከፍርሃትና ከራድ የተነሳ በጉልበት በሸር የተቆጣጠረውን ስልጣን በማደናገርና በማምታታት ሕዝቦችን በመከፋፈል በሙስናና በሃገር ክህደት አንድነትና በማጥፋት ሕዝብ ከሕዝብ በማናቆር በሶቆቃ በቸነፈር ቀጥቶ በስልጣን ለመቆየት የሚያደርገው ቅዠት ዋጋቢስነቱን ከመሰረቱ የተነሳበት እኩይ ተግባሩ በመሆኑ ዛረእም በግልጽ ሽንፈቱንና ያለመሰልጠኑን በጋሃድ እያሳየ ነው: ወያነ ያልተረዳውና ሊቀበለው አልቻለ በወቅቱ ለዚህ ትግል ዋጋና ለድል ያደረሱት ዛሬ የሚመጻደቅበት ስልጣን እንዲቆናጠጥ ያበቁት የኢቶጵያ ሕዝብቦች መሆናቸው ታሪክ የሚዘክረው ሲሆን: የትግራይ ሕዝብ ያመጣውን በመሰዋት መብት መርገጡ ለታይታ መሆኑን በግልጽ እያሳየነው: የትግራይ ልጆች የተሰውት ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝቦች እና ለውድ ወገኖቻቸው ለመሆኑ አይካድም የሚያሳዝነው በነዛ ጀግኖችና የሃገር ፍቅር ያደረባቸው ለተገነው ስልጣን ማታለያና መዋሻ ቃላት በመጠቀም ሲነግዱና በነሱም ላይ ይህን የመሰላ በደል ግፍ ሲጭኑባቸው አረመኔና ሕሊናቢሶች ለመሆናቸው ቋሚው የሚያየው በመሆኑ ይህን ፍርድ በጥቅም ታውረው በየ ዓለሙ ተበትነው በሕዝባቸው ላይ የሚፈጸመውን ግፍ እንድ እድገት የሚመጻደቁት ሆድ አደር የትግራይ ተወላጆችና እንዲሁም ቅንጣቢ ጠባቂዎች ከተለያየ ስብጥር ብሄሮች የሚሰነዝሩት የውሸት ሕዳሴ ራሳቸውን እንዲጠይቁ ያስቡበት የዲሞክራሲን ምንነት አጥብቀው ይረዱ ከመጋረጃ ወጥተው እውነትን ለማግኘት ይጣሩ:: የሕዝቦችን መብት አፍኖ በስልጣን ለመቆየት ማሰብ የጸደይ ማእበል ያመጣውን በጥላቅ ያለማሰብ በመሆኑ ሕዝብ አይፈራም እናንተ የምትፈልጉት ኃይል በሃገራችን ጥቅምና በሕዝባችን ሕይወት የሚያመጣውን ከናንተ ባላይ ጠንቅቀን ያምናውቅና በሰለጠነ መንገድ ያለውን ያስተዳደር ብልሹነት የህግ በላይነት የመብትና የፍትሕ ጥሰትን በሰላም እየሞትን ዘላቃዊ ሰላምና እድገት ለማምጣት በናንተ መከላከልና ጥቃት ከታለመውና የሕዝብ መብትና ነጻነትን ካቀድነው ፍንክች እንደማንል ሕዝብም በቅቶትና ምንነታችሁን ጠንቅቆ ስላወቀ ከጀመረው ላለመለሱ ጽናቱን እያሳየ በመሆኑ በመቻቻል የሀገራችንን የህዝባችን ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት ጥሪያችን እንድታከብሩ መፍትሄም እንዲሰጠን ለተጠየቀው መልስ እስካልተገኘ ቀጣይነቱንና ድሉም የማይቀር መሆኑን አናስገነዝባልን

  ኢትዮጵያ ለዘላለሙ በነጻነት ትኑር
  ድል ለመላው የትግል አጋሮች