በሃራማያ ዩኒቨርስቲ በተጣለ ቦንብ አደጋ ደረሰ (Video @ AAU)

(ኢ.ኤም.ኤፍ) – በኦሮሚያ ከፍተኛ ተቋማት ውስጥ የተጀመረው ረብሻ ወደ ከተሞች እየተዛመተ መሆኑን ዛሬ ምሽት ያገኘነው መረጃ አሳውቋል። የአምቦ ዩኒቨርስቲ ረብሻ ወደ ከተማው ተዛምቶ ሰባት ሰዎች ተገድለዋል። በመዳ ወላቡም ከዩኒቨርስቲው አልፎ በከተማው በተነሳ ረብሻ ሶስት ሰዎች ሞተዋል።

ዛሬ ቀን ላይ ደግሞ በሃረማያ ዩኒቨርስቲ ኳስ ጨዋታ ይመለከቱ የነበሩ ከመቶ በላይ ተማሪዎች ላይ ቦንብ ተጥሎባቸው፤ ሰባ ያህሉ ላይ የመቁሰል አደጋ ሲደርስ አንድ ተማሪ ሞቷል። በጅማ እና በሌሎች ዩኒቨርስቲዎች ከኦሮሞ ተማሪዎች ጋር ያልተባረሩ ወይም የሌላ ክልል ተወላጆች ላይ ትንኮሳ እና ድብደባ እየተፈጸመባቸው ነው። “ኦሮሚያ ለኦሮሞ” የሚል መፈክር ይዞ የሚንቀሳቀሰው አመጽ፤ አጀማመሩ ሰላማዊ ቢመስልም፤ በውስጡ ግን በሌላው ብሄረሰብ ላይ ጥላቻን የሚያሰፋ በመሆኑ፤ በሌላው ኢትዮጵያዊ ዘንድ ህዝባዊ ድጋፍን እየተነፈገ ነው።

ይህም ሆኖ የኦህዴድ እና የህወሃት ሃይሎች በተቀናጀ መልኩ ሃሳባቸውን በሰላማዊ መንገድ በሚገልጹ ተማሪዎች ላይ እየወሰዱ ያሉት የግድያ እርምጃ ብዙዎችን ቅር አሰኝቷል።

በመጨረሻም “በተቃዋሚዎቹ በኩል የተነሳውን ቀላል ጥያቄ ወደ ጥላቻ የሚወስዱ አካሎችም ሆኑ የሃይል እርምጃ እንዲወሰድ ትዕዛዝ የሚሰጡ ባለስልጣናት ጉዳዩ ወደከፋ ደረጃ እንዳይሸጋገር አንድ አፍታ ቆም ብለው ሊያስቡበት ይገባል” የኢ.ኤም.ኤፍ መልዕክት ነው።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on May 1, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

2 Responses to በሃራማያ ዩኒቨርስቲ በተጣለ ቦንብ አደጋ ደረሰ (Video @ AAU)

  1. andnet berhane

    May 1, 2014 at 11:28 PM

    የከተማ መስፋፋት ጉዳይ ሳይሆን በትልቁ በሃገራችን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ታላቅ እመብት ጥሰት የኦሮሞ ተወላጆችን ብቻ የጎዳ ሳይሆን ሁሉንም የኢትዮጵያውያን/ት ዜጎችን ሀገሪቱንም ወደከፋ የእርስ ግጭት ለማስገባት የሚደረጋ ታላቅ ፈተና በወያኔና በስሩ በጥቅም ትሥር ያስቀመጣቸው ሆዳም ኦሮሞ አማራ ትግሬ ደቡብ ሱማሌ ቢኒሻንጉል አፋር አኝዋክ ሌሎቹም እንዳሉ እያወቅን በተናጠል በጎሳ ስም ተነስቶ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ የጋራ ጠላታችንን በአንድነት በመቆም ማስወገድ ይቻል ነበር፡ ነገርግን ጠላቶቻችን በነደፉልን የልዩነት መንገድ መሰለፍ ለነሱ ብርታትና ጥንካሬ በመሆኑ፡ በተናጠል እንድንዳከም እያደረጉን መሆኑን ቆም ብለን እንመልከት፡ ከተማ ማስፋት ጥቅም እንዳለው ቢታወቅም የሰፋሪ ዜጎችን ማፈናቀል አሳሳቢና የሁሉም ችግር በመሆኑ፡ ኢትዮጵያን በማስቀደም ሁላችን በመተባበር በመከባበ ተዋውጠን የተረጋጋች ሰላም የሰፈነባት ሁሉም ዜጎች ያቀፈች ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ለመመስረት እንታገል በጎጥ መነቋቀር ለእምባገነን ገዥዎች ጥንካሬ መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡ ጋዜጠኞችም የኦሮሞ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሰልፍ ወጡ ከማለት ይልቅ በሃረር በአምቦ በወለጋ በአዲስ አበባ ተማሪዎች ተቃውሞ ወጡ ተብሎ ቢጻፍና ቢነገር የወያኔን የጥፋት ፍላጎት ማምከን በተቻለ ነበር፡ እባካችሁን እውነት በዩኒቨርሲቲ ደረጃ የደረሳችሁ ታዳጊዎች የሸመታችሁትን ትምህርት ተጠቀሙበት አመዛዝኑ ለዚህች ሃገር የሚጠቅማትን እናንተንም የሚጠቅማችሁን ከሌላው ሃገር በማወዳደር ለመጠቀም አጥብቃችሁ ጣሩ አለበለዝያ የናንተ ትምሕርት የጥቂት ቦድ አደሮች ፍላጎት ማሟያ እንድሚሆን ማወቅና ከዚህ ጠባብ ስርአት ራሳችሁን አውጡ፡

  2. Kibrom

    May 2, 2014 at 3:43 PM

    I am not surprised why Oromo speakers are saying ‘Oromia for Oromos/Oromia”.There is no current generation believing in Unity and Love for better future and togetherness under the umbrella of Ethiopia. So long so narrow and racist being displayed in Oromia.