በኑቨንበርግ ከተማ (ጀርመን) የተካሄደውን ህዝባዊ ስብሰባ አስመልክቶ የተዘጋጀ ዘገባ

ከዚህ ጭብጥ በመነሳት፣ የወቅቱ የሀገራችን የፖለቲካ ምህዳር መጥበብ ያሳሰበው የኢትዮጵያ የፖለቲካና ሲቪክ ማህበራት አንድነት ድርጅት በጀርመን እነሆ ፌብሩዋሪ 18 ቀን 2012 ዓ.ም እ.አ.አ በኑቨንበርግ ከተማ ታላቅ ህዝባዊ የምክክር መድረክ አዘጋጅቶ ነበር። በዚህ መድረክ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ሲቪክ ማህበራት፣ የሃይማኖት መሪዎችን ጨምሮ በጠቅላላው  ከ300 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ተገኝተዋል።

ስብሰባውን በመክፈቻ ንግግር የከፈቱት የአዘጋጅ ኮሚቴው አስተባባሪ አቶ በላይ ወንዳፍራሽ እንደተናገሩት፣ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን እጅግ አሳሳቢ የሆነውን የዜጎችን መብት ረገጣ ለማስቆም በሚደረው ወሳኝ ፍልሚያ፣ የወጣቱ ተሳትፎ የበለጠ ለማሳደግና ተጨማሪ የትግ አጋር ሃይል ሆኖ ከአንድነት ሃይሎች ጎራ በቀዳሚነት እንዲሰለፍ ማስቻል ነው ካሉ በሁዋላ፣ የወጣቱን የትግል መንፈስ የሚያነሳሳና በትግሉ አውድ ዙሪያ ወጥ ሀገራዊ ራእይ የሚያስጨብጥ የጋራ የመግባቢያና መረዳጃ ስልት ነድፎ መንቀሳቀስ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ አስገንዝበዋል። አያይዘውም፣ በአሁኑ ወቅት በአዲስ የትግል መንፈስ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ማዕከል ያደረገ፣ የዓላማና የትግል አንድነትን የሚያስተሳስርና የሚገነባ ጠንካራ መሠረት ያለው ሁለገብ ማእቀፍ ውስጥ መሰባሰብ አስፈላጊ መሆኑን በማመልከት፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ አሳሳቢ እየሆነ የመጣውን የስደተኛውን ችግር ለመፍታት የሚያስችል የተሻለ አደረጃጀት እስከአሁን ስላልነበር ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ለአያሌ ችግሮች ተጋልጠው ቆይተዋል። ይህንኑን ችግር በጋራ ለመቅረፍ የሚያስችልና ሀገርን ከጥፋት ለማዳን በሚደረገው ርብርብ ጉልህ አስተዋፅኦ ለማድረግ ይቻለን ዘንድ በጋራ መግባባትና መሥራት እጅግ አስፈላጊያችን  በመሆኑ ሳቢያ፣ እነሆ የኢትዮጵያ የፖለቲካና ሲቪክ ማህበራት አንድነት ድርጅትን ለማቋቋም ችለናል ብለዋል።

በማያያዝም፣ በኢትዮጵየዊነቱ የሚያምን፣ የግዛትና የህዝብ ሉዓላዊነቷን የሚያከብር፣ ማንኛውም ሀገራዊ አዠንዳ አለኝ የሚል የፖለቲካም ሆነ የሲቭክ ስብስብ፣ እንዲሁም ግለሰብ ጭምር ተባብሮ ለመስራት ድርጅታቸው ዝግጁ መሆኑን በመግለፅ፣ ለኢትዮጵያ ትንሳኤ ከዘረኝነትና ከጎጠኝነት የፀዳ፣ በእኩልነትና በመከባበር ላይ የተመሰረተ የበሰለ የፖለቲካም ሆነ የልማትና የእድገት ሥራዎችን ከሚያራምዱ ሃይሎች ጋር ለአንዲት ኢትዮጵያ ትንሳኤ እጅ ለእጅ ተያይዘን በመቻቻል በጋራ መግባባት እንሥራ በማለት ጥሪ አድርገዋል።

በማስከተልም፣ የድርጅቱ ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ፀሀፊ፣ የድርጅቱን አላማና አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ፣  እንዲሁም፣ የስብሰባውን ጥሪ አስፈላጊነት በማስመልከት አጭር ንግግር ያደረጉ ሲሆን። በንግግራቸው ላይ እንዳመለከቱት በአሁኑ ወቅት የስደተኛው ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ በመምጣቱ ሳቢያ ችግሩ በዛው ልክ እየተባባሰ ሄዷል ካሉ በሁዋላ፣ በተለይ በአንዳንድ ሀገራት በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ እየተፈፀመ ያለው አሳዛኝ ሁኔታ ወደሌላም እንዳይዛመት በሁሉም ደረጃ አስፈላጊው ጥረትም ሊደረግ እንደሚገባ አበክረው አስረድተዋል። አያይዘውም እንደዚህ አይነቱን መሠረታዊና አሳሳቢ ጉዩዳይ ለመፍታት የሚያስችል አቅም ከወዲሁ ለመፍጠር እንዲቻል በማሰብ ይህ ዝግጅት እንደተደረገና ሁሉን አቀፍ በሆነው ድርጅታዊ ማእቀፍ ስር ተሰባስቦ በየጊዜው እተገኛኙ የጋራን ችግር በጋራ ለመፍታት ሚያስችል እስትራቴጂ ነድፎ መሥራትና ለስደተኛው መብት መከበር በጥምረት መስራት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው ሲሉ አስምረውበታል።

በቀጣይ ንግግር ያደረገችው የሴቶች ተወካይ ስትሆን፣ በንግግሯ ላይ እንዳለችው፣ በኢትዮጵያ ከግማሽ በላይ የጠቅላላውን የሀገሪቱን ህዝቡ ቁጥር የሚሸፍኑት ሴቶች መሆናቸው ገልፃ፣ በሀገራችን የሴቶች ጥያቄና ችግር ገና አልተፈታም በማለት ገልፃ፣ ሴቶች እንደማንኛውም የህብረተሰብ አባል፣ በአንድ ሀገር ላይ የሚከሰት፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ፣ ባህላዊና ሃይማኖታዊ ቸግሮች ተካፋይ ናቸው በማለት፣ በኢትዮጵያ ባለው አምባ ገነን ሥርዓት፣ ሳቢያ የሴቶችን ጭቆና ድርብ ድርብርብ አድርጎታል ካለች በሁዋላ፣ የፖለቲካው ትርምስ ገፈት ቀማሾች በአመዛኙ ሴቶች ናቸው። መውለድ ወንጀል የሆነበት ሀገር ቢኖር ኢትዮጵያ ብቻ ነች ማለት ይቻላላ በማለት፣ የሥርዓቱ አስከፊ ገፅታ ጠቅለል ባለ መልኩ አስረድታለች።

 

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on March 10, 2012. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.