በቻን የመክፈቻ ውድድር ሊቢያ – ኢትዮጵያን 2- 0 አሸነፈች

(ኢ.ኤም.ኤፍ) በዛሬው የኢትዮጵያ እና ሊቢያ ጨዋታ የሊቢያ ቡድን 2-0 አሸንፏል። ይህ በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ያለው የአፍሪካ ቻን ዋንጫ፤ ኢትዮጵያ ያለችበት ምድብ C ውስጥ ሲሆን፤ በዚህ ምድብ ውስጥ ኢትዮጵያን ጨምሮ፤ ሊቢያ ኮንጎ እና ጋና ይገኙበታል። ኮንጎ እና ጋና ዛሬ ባደረጉት ጨዋታ፤ ጋና 1-0 አሸንፏል።
ቀጣዩ ጨዋታ የሚሆነው፤ ኢትዮጵያ ከኮንጎ እና ጋና ጋር የምታደርገው ሲሆን፤ ሁለቱንም ቡድን ማሸነፍ ወደቀጣዩ ማጣሪያ እንድታልፍ ያደርጋታል። ሆኖም ዛሬ ደካማ በተባለችው ሊቢያ መሸነፏ፤ ቀጣይ እድሏን ያጨለመው ይመስላል። ምክንያቱም ኮንጎ እና ጋና ጠንካራ ቡድኖች ናቸው። ሌላው ቀርቶ በ2009 በነበረው የቻን ሻምፒዮና ላይ ለዋንጫ ደርሰው፤ 1ኛ እና 2ኛ የወጡ ቡድኖች ሲሆኑ፤ ኢትዮጵያ እና ሊቢያ ግን ከምድባቸው እንኳን ለማለፍ ሲቸገሩ ይታያል።
ኢትዮጵያ እንግዲህ በቀጣይ ከነዚህ ሁለት ቡድኖች ጋር የምታደርገው ጨዋታ፤ የወደፊት እድሏን ይወስነዋል። አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው በዚህ ጨዋታ ታዋቂዎቹን፣ ሽመልስ በቀለ፣ ሳላዲን ሰኢድ፣ አዲስ ህንጻ እና ጌታነህ ከበደን አላሰለፉም። በረኛው ሲሳይ ባንጫም ባለፈው የናይጄርያ ጨዋታ ላይ፤ መልበሻ ክፍል ውስጥ ከአበባው ቡጣቆ ጋር በመደባደቡ የገንዘብ መቀጫ ተደርጎበት፤ በዚህም ጨዋታ ላይ እንዳይሳተፍ ተደርጓል። ስለዚህ በረኛ ሆኖ 90 ደቂቃውን የሸፈነው ጀማል ጣሰው ነበር።
በዚህ ጨዋታ ሊቢያ ጨዋታው እንደተጀመረ በ4 ደቂቃ ላይ እና ጨዋታው ሊጠናቀቅ 4 ደቂቃ ሲቀረው ባስቆጠሩት ሁለት ግቦች አሸናፊ ሆነዋል። ሊቢያ 2 ተጫዋቾች ቢጫ ሲያዩባት፤ በአስራት መገርሳ አማካኝነት ኢትዮጵያ አንድ ተጫዋች ቢጫ ካርድ አግኝታለች።
ከ4ቀናት በኋላ… ማለትም ጃኑዋሪ 17 ቀን ኢትዮጵያ ከጋና ጋር ትጫወታለች። ጃኑዋሪ 21 ደግሞ ከኮንጎ ጋር ትጋጠማለች። ብዙ ባይጠበቅም… “መልካም እድል!” ማለቱ አይከፋም።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on January 13, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

2 Responses to በቻን የመክፈቻ ውድድር ሊቢያ – ኢትዮጵያን 2- 0 አሸነፈች

 1. HG

  January 13, 2014 at 5:28 PM

  Very fortunately I was in Bloemfontein, South Africa this week and was able to watch this game. It was unbelievable. It looks Ethiopians were playing on their home country-Addis. There more than 5000 Ethiopia sport fans from all over South Africa and there was huge excitement and expectation that they will be able to easily defeat Libya. It was devastating. even if it was very encouraging to see a team composed of significant number of young players. It was also very clear that the team lacks significant experience and coordination. Today’s game clearly evident that Ethiopians will not advance into the next level. I still wish them all the best, but am also happy that I am not going to be there for the other games. Limen Likatel Wodage.

  Apart from the football, it was my very first encounter with Ethiopians in South Africa and I have at least enjoyed that part and become proud of them.

  Thanks,
  HG

 2. አህፍስት

  January 14, 2014 at 3:36 PM

  The weak Ethiopian squad with no slightest doubt will be routed devastatingly 5-0 and plus by the great Ghanian Black stars. unless the ignorant coach and woyane planted Sewnet Bishaw sacked ,the Ethiopian foot ball remain to be defeated by any Africans,let alone Libya .