በቴሌ ቃጠሎ የአስተዳደር መረጃዎች ወደሙ

03 June 2009 (በፍሬው አበበ) የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ባለፈው እሁድ ማለዳ የደረሰበትን የእሣት አደጋ የመልሶ ጥገና እያካሄደ መሆኑ ተገለፀ፡፡ በደረሰው ቃጠሎ የአስተዳደር መረጃዎች ወድመዋል፡፡የቃጠሎው መነሻ ኤሌክትሪክ ሊሆን እንደሚችል እሣት አደጋ ግምቱን ባደረገው ርብርብ የአንድ “ሊዮን ብር ግምት ያለው ንብረት ማዳኑን ገል”ል፡፡ 

አቶ አብዱራሂም አህመድ የኮርፖሬሽኑ ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ኃላፊ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፁት በኮርፖሬሽኑ ዋና ጽ/ቤት አራተኛ ፎቅ ላይ በተነሳው ቃጠሎ የደረሰው ውድመት መጠን እየተሠራ መሆኑን በመግለፅ በአሁኑ ወቅት ሕንፃውን ሥራ ለማስጀመር ጥገናው እየተካሄደ ነው፡፡

በአራተኛ ፎቅ ጉዳት የደረሰበት የኢንተርናል ስፖርት መምሪያ ስር የሚገኘው የሰው ኃይል፣ የስልጠናና ዴቨሎፕመንት፣ የሠራተኛ ማስተዳደሪያ ክፍሎችን የሚመለከቱ መረጃዎች በቃጠሎ ወድመዋል፡፡

እንደ አቶ አብዱራሂም ገለፃ ከደንበኞች አገልግሎት ጋር የተያይዘ አንዳችም ጉዳት አለመድረሱን ተናግረዋል፡፡

አቶ ከበደ ለገሰ የአዲስ አበባ እሣትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ኤጀንሲ የማስታወቂያና ሕዝብ ግንኙነት ኦፊሰር ስለ ጉዳዩ ከሪፖርተር ጋዜጣ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ በኮርፖሬሽኑ ላይ ቃጠሎ መነሳቱን እሁድ ዕለት ከጠዋቱ 1፡55 ሰዓት ጥሪ እንደደረሳቸው ወደ ቦታው ተንቀሳቅሰው 2፡27 ደቂቃ በፈጀ ጥረት እሳቱ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

በቃጠሎው 4ኛ እና 5ኛ ፎቆች ላይ የሚገኙ ሰነዶች መውደማቸውን የጠቀሱት አቶ ከበደ እሣት አደጋ ባደረገው ጥረት አንድ ቢሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ከቃጠሎ ማዳን ተችሏል ብለዋል፡፡

በቃጠሎው ወቅት በየብሎኩ በሮች በመዘጋታቸው መግቢያ በማጣት ምክንያት በሮች እስኪሰበሩ ጊዜ መውሰዱን ትልቅ ችግር እንደነበር ተናግረዋል፡፡

የቃጠሎው መነሻ ለማወቅ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን፤ ምናልባት ግን መነሻው ከኤሌክትሪክ ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on June 3, 2009. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.