በቅሬታ የምትናጠው አዲስ አበባ – ሪፖርተር

dribaበአዲስ ከንቲባና ነባር ካቢኔ ሥራውን የጀመረው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰባተኛ ወሩን ይዟል፡፡

አስተዳደሩ የቆየባቸው ሰባት ወራት የሥራ ክንውን የከተማውን ነዋሪዎች ብሶትና ችግር የፈታ ሳይሆን፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ጐልተው የታዩበት ነበር ማለት ይቻላል፡፡

ከ2001 ዓ.ም. እስከ 2005 ዓ.ም. ለአምስት ዓመታት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን በከንቲባነት ሲመሩ ከነበሩት አቶ ኩማ ደመቅሳ የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤትን ቁልፍ የተረከቡት አቶ ድሪባ ኩማ፣ የከተማውን ነዋሪዎች ሲያንገሸግሻቸው የቆየውን የመልካም አስተዳዳር እጦት ችግር በመጠኑም ቢሆን ይፈቱታል የሚል ግምት ተሰጥቶዋቸው እንደነበር ሪፖርተር ያነጋገራቸው አንዳንድ የከተማው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ ነዋሪዎቹ ቅድሚያ ግምት የሰጡት ዝም ብለው ሳይሆን በፌዴራል መንግሥት ጭምር ትኩረት ተሰጥቶ መሠራት ያለባቸው በዋናነት፣ የመልካም አስተዳደር እጦትና የሙስና ጉዳዮች በመሆናቸው ጭምር ነው፡፡ የፌዴራል መንግሥት መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ለሚጠይቋቸው የመብትም ሆነ ሌሎች ጥያቄዎች ተገቢ የሆነ ምላሽ ማግኘት ባለመቻላቸው፣ የመልካም አስተዳደር እጦትን በማንሳት ጠዋት ማታ ሲያማርሩ መክረማቸው የአደባባይ ሚስጥር መሆኑን አስተያየት ሰጪዎቹ ይገልጻሉ፡፡ Continue reading from the Reporter –>

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on March 31, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to በቅሬታ የምትናጠው አዲስ አበባ – ሪፖርተር

  1. ጦጲያ

    March 31, 2014 at 6:15 AM

    ምን አልባት ለችግሮቹ ወድፊትም ቢሆን ምንም አይነት እልባት ሊገኝለት አይችልም የሚል ጥርጣሬና ፍራቻ አድሮብኛል: ምክንያቱም በፈደራል ውስጥ ያስተዳደር ስልጣን ተሰጥቷቸው የሚሰሩ ሰዎች ያላቸው አላማ እና ፍላጎት: አንድ በፈደራል ተጸንጾ ታቅዶና ትዋቅሮ በስራ ፍጻሜ እልዲያልቅ የታሰበ ፕሮጄክት እንድይሳካና ከክልል ጋር የፍላጎት አለመጣጣምና ያላማ ግጭት እንዲኖረው የማድረግ ሊሆን ስለሚችል ነው::