በቃ! ቃለ ምልልስ ከነአምን ዘለቀ ጋር

VOA | 10 March 2011 |

ንቅናቄው በአራቱ ዋና ዋና የሀገሪቱ ቋንቋዎች በአማርኛ፥ በኦሮምኛ፥ በትግርኛና በሱማልኛ – በቃ፥ ገኤ፥ ይአከል፥ ባስ የሚል መፈክር አንግቧል።

“በቃ ስንል – ይላሉ አቶ ነዓምን – ዘረኝነት በቃ፥ አምባገነንነት በቃ፥ ድህነት በቃ፥ ማን አለብኝነት ይብቃ፥ ፍትሕ-አልባው ሥርዓት ይብቃው፥ የሃያ ዓመታቱ የወያኔ አገዛዝ ያብቃ ማለታችን ነው።”

«መልዕክቱን ለማድረስ በዋናነት የምንፈልገው፥ ለኢትዮጵያ ሕዝባችን ነው። ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ በራስ ተነሳሽነት በተለያዩ አካባቢዎች ሕዝቡ እራሡን እያደራጀ ይገኛል። ለነፃነትና ፍትሕ ጥማት እንዳለው ለመረዳት ችለናል። ከያካባቢው የምናገኛቸው መረጃዎችም፥ የኢትዮጵያ ሕዝብ ልክ እንደ ቱኒዝያና ግብፅ ሕዝቦች ይህንን አስከፊ ሥርዓት ለመጣል ባጭር ጊዜ ውስጥ ሊንቀሳቀስ እንደሚችል የሚጠቁሙ ናቸው። በዚሁ መሠረት ከሕዝባችን ጐን ለመቆም እንፈልጋለን» ሲሉም አቶ ነዓምን ዘለቀ ያስረዳሉ።

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on March 10, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.