በሸዋዬ በቃ!!

ከአክሊሉ ታደሰ

በምስኪኗ ሸዋዬ ሞላ ላይ የጋዳፊ ልጅ ሚስት የፈፀመችባን ዘግናኝ ድርጊት በቴሌቪዠን ስመለከት ያላወቅናቸው ስንትና ስንት ሸዋዬዎች በተለያዩ የአረብና ሌሎች ሀገራት በግፈኞች እጅ አበሳቸውን እንዳዩና ዛሬም በመከራ ላይ እንደሚገኙ እንዳስብ አስገደደኝ….

ይህም እስከመቼ ሊቀጥል እንደሚችልና መቼስ ሰው መሆናችንን አስረግጠን እንደ ሰው መኖር እንደምንችል እንዲሁ…..

የሀገሬ ሰው ከሀገሩ ርቆ ለመሄድ ሲነሳ ማልቀስ መላቀሱ ተረት ሆኖ በምትኩ እንኳን ደስ ያለህ ከተተካ ሰነበተ፡፤ ወላጅ ለልጁ እርሱነቱን ከነኩራቱ ማውረሱ ቀርቶ የልጁ አፍ መፍቻ የስደት ሀገር ስም …ህልምና ምኞቱም ስደት እንዲሆን ማድረጉ የወላጅ ግዴታና ሀላፊነት ይመስል ከተለመደ ቆየ::

ለዚህም ምክንያቱ በተለይ ባለፉት 40 ዓመታት ዜገፐች ሊሸከሙት ያልቻሉት የአንባገነንና ዘረኛ ስርአት ቀንበር መሆኑና ቀንበሩንም አሽቀንጥሮ ለመጣል የተደረጉት ሙከራዎች ውጤት አልባ መሆን ያስከተለው ተስፋ መቁረጥ መሆኑ በዙዎች ሲናገሩ በተደጋጋሚ ተደምጠዋል::

በጥቂቶችና በጊዜያዊነት የተከፈተው የስደት ጎዳና ዛሬ ሚሊዮኖቻችንን ከቀዬችን ጠራርጎ በየሰዉ ሀገር ሊበትነን በቅቷል፡፤ ትናንት በማንነታችንና በኩራታችን ያውቁን ያከብሩን የነበሩ ዛሬ እንደ እንጉዳይ ፈልተንና ረክሰን ማግኘታቸው ለንቀት አልፎም ለማንም መጫወቻነት ዳርጎን ያገኛል፡፤

ትናንት ኢትዮጲያዊነት መገለጫው የራሱን የማይሰጥ የሰው የማይፈልግ፤ ለነፃነቱ ቀናኢ ጀግናና ኩሩ ህዝብ እንዳልነበር እነሆ ለነፃነት መከፈል ከሚገባው በላይ ለስደት እየተከፈለ ካለንበት ደረጃ መድረሳችን ከአለማችን ብቸኛ መገዛት የሚወድ ህዝብ ለመባል አብቅቶናል፡፤ ….ታዲያ ቆም ብሎ ለማሰብ ምነ መሆን ይቀረናል?

ጃፓን መሬት ተንቀጠቀጠ …..የኑክሌር ጣቢያ ፈነዳ …..ቱኒዝያ ህዝባዊ አመፅ ተቀሰቀሰ….. ግብፅ ቀጠለ…. የመን ተከተለ …ካሊፎርኒያ ደን ተቃጠለ….ወዘተ…ከአደጋው ሰለባዎች ውስጥ ኢትዮጵያውያኖች አሉ፡፤በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሰራሽ አደጋዎች ሳቢያ በአብዛኛው ስፍራ ውሻና ድመት ሰብሳቢ ሲያገኙ የእኛ ሰዎች ደራሽ አጥተው ሲያነቡ በየሬዲዮው መስማት….

Shwygar Mullah, a nanny for Hannibal and Aline Gadhafi, says Aline burned her with boiling water.

Shwygar Mullah, a nanny for Hannibal and Aline Gadhafi, says Aline burned her with boiling water.

በተለያዩ የአረብ ሀገራት በብዛት የተሰደዱ እህቶቻችን ላይ በተፈፀመውና እየተፈፀመ ያለውን ስቃይና ፍዳ……

ሀገር ጥሎ በመሸሽ በየሰው ሀገር ድንበር በጥይት የሚገደለው ኢትዮጵያዊ ብዛት…..

ባህር በጀልባ ለመሻገር ሲሞክሩ የአሳ ነባሪ እራት የሆኑ ወገኖቻችን ቁጥር ብዛት…..

በአሁኑ ሰአት በተለያዩ ሀገራት በህገ-ወጥ ስም በየእስር ቤቱ እየማቀቁ የሚገኙ ወንድም እህቶቻችን…..

አረ–ስንቱ ይቆጠራል?

ባጠቃላይ ከጨቋኝና ብልሹ አንባገነኖች ለመሸሽ የተመረጠው ስደት ከመፍትሄነቱ ይልቅ ከእሳት ወደ ረመጥ የተያዘ ጉዞ መሆኑን ለመረዳት ምን ያህል ወንድም እህቶቻችንን ወደ ሲኦል መላክ እንደሚገባን አላውቅም፣..

+ የነፃነት ትርጉሙ ገብቶን ወደ ቀድሞው ማንነታችን የመልስ ጉዞ ለማድረግ ከዚህ በሗላ ምን ያህል ህይወት መገበርና የምን ያህሎቹን የጣር ድምፅ መስማት እንደሚገባንም አላውቅም::..

፤ወላጆች ከሀገር በላይ እናት ከነፃነት በላይ ክብር እንደሌለና ይህን የሰው መሆን መገለጫ ውርስ ለልጆቻቸው ማውረስ እንደሚገባቸው አምነው ለመቀበል ያልከፈሉት ምን የቀራቸው እንዳለም አላውቅም..

፤ስደትን እየተመኙ ቀናቸውን በመቁጠር ላይ የሚገኙ ወገኖቻችን የስደት አስከፊነት ገብቷቸው ከስደት ይልቅ በጥቂት ተባዮች ሰላም ያጡበትን ቤታቸውንበጋራ ለማፅዳት ለስደት ከሚከፍሉት ዋጋ ያነሰ መሆኑን ለመረዳት ከአሁን በሗላ ምን ያህል ወንድምና እህቶቻቸውን ማጣት እንዳለባቸውም አላውቅም…

ብዙ ብዙ ማለት ይቻላል ….በአጭሩ ከኛ በላይ የግፍ ግፍን የተሸከመ ህዝብ ያለ አይመስለኝምና እንደ እኔ እንደ እኔ ምላሹ ሊሆን የሚገባው የእስካሁኑ በቃ! ….በሸዋዬ  በቃ!!…

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on September 1, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.