በሳዑዲ አረቢያ የደረሰው ግፍና መሠረታዊ ችግራችን – አንዱ ዓለም ተፈራ

የእስከመቼ አዘጋጅ – አንዱ ዓለም ተፈራ

ሕዳር ፱ ቀን ፳ ፻ ፮ ዓመተ ምህረት

November 18, 2013

ዘግናኙ የስደተኛ ኢትዮጵያዊያን ግፍ በሳዑዲ አረቢያዊያን እጅ፤ ከፊታችን ተደቅኗል። ሁላችን በያለንበት፤ “ለምን? ምን አደረግን? መጨረሻው ምንድን ነው? መቼ ነው ይኼ ሁሉ የሚያበቃው?” እያልን እርስ በርሳችን እየተጠያየቅን ነው። እኛ ወደ የምንፈልገው መንገድ ካልገባን፤ ሌላ ሊይስገባን የሚችል ኃይል የትም የለም። በሳዑዲ አረቢያ የተደረገውን ኢሰብዓዊ ድርጊት፤ ሁላችን ኢትዮጵያዊያን በግል በራሷና በራሱ እንደተደረገ በደል አድርገን ወሰደነዋል። ተገቢም ነው። ኢትዮጵያዊያን እንደ ትቢያ ተረገጥን፣ ተዋረድን፣ ተገደልን። እናም አንድ ነገር ማድረግ አለብን። ሀገራዊ መልስ ሠጪ መንግሥት የለንም፤ ሀገራችንን የሚወክል መንግሥት የለንምና። እኛ ግን በኢትዮጵያዊነታችን ኢትዮጵያዊ ኃላፊነት አለብን። ኃላፊነታችን እስከምን ደረስ ነው? የሚለውን በዚህ ጽሑፍ እቃኛለሁ። Read story in PDF: በሳዑዲ አረቢያ የደረሰው ግፍና መሠረታዊ ችግራችን…

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on November 21, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

2 Responses to በሳዑዲ አረቢያ የደረሰው ግፍና መሠረታዊ ችግራችን – አንዱ ዓለም ተፈራ

 1. አቢይ ኢትዮጵያዊ+ሥጋዊ-ወመንፈሳዊ

  November 21, 2013 at 8:04 AM

  ))ቅማሎቹን ትተን፣
  አንጠግብም ፎክተን።((((((((
  አህያውን ፈርተን-ለምን ዳውላውን?
  +++++++++++++++++++++
  እነዚህ ቅማሎች፣የተቅመለመሉ፤
  ከሸበጥ ከልዋጭ ዛሬ ፈቀቅ ያሉ፤
  ዘርፈው አዘርፈው ሕዝብ እየገደሉ፤
  በአገራችን ንብረት፣ሐብታም ነን የሚሉ፤
  ሰርተው-ያገኙት ሳይሆን ከድሆች አፍ ነጥቀው፤
  በሚሊዮን ገድለው በሚሊዮን ሰርቀው
  ያደባባይ ሚሥጥር መሆኑም ቢታወቅ፤
  ሁሉም ልቡ ፈራ በደም ለመጠየቅ።፡
  ለምን’ስ ይዋሻል በሰበብ አስባቡ፤
  አጋዚ ቅማሏ ቆማ ካጠገቡ፤
  የምን መፎከት ነው ይለይለት እንጂ፤
  ወያኔ ይፈራርስ በሕዝብ አመፅ-ፈንጂ።
  እናም እናስተውል እንወቅ ለይተን፤
  ቅማሎቹን ትተን፣
  አንጠግብም ፎክተን።
  ደማችንን መጠው፣መጠው ሲያስመጥጡን፤
  ያውም ሳውዲ ልከው በዶላር የሸጡን፤
  አልበቃ ብሏቸው እያስቀጠቀጡን፤
  ከግድያ ስንተርፍ በቁም-መሞት ቀጡን።
  እስከመቼ እንተወው ወያኔ-ባንዳውን፤
  አህያውን ፈርተን-ለምን ዳውላውን?
  ዳውላና አህያን በፍርሃት ሲስሉ፤
  የአባቶች ትርጉሙ ጠሊቅ ነው አባባሉ።
  የዘመኑ አህያ ዳውላውስ ማነው?
  አይተን እንዳላየን በቀን የፈራነው።
  አህያው አጋዚ ዛሬም የመሸበት፤
  በቀን ሰው ይመስላል፣
  ቆዳው ዥብ አለበት።
  ችግራችን ደግሞ ተነግሮ ያላለቀው፤
  ዳውላው እኛ ነን የማንደብቀው።
  ጅቦቹ በቀትር ጅብ አህያም ናቸው፤
  ወቸገል ከሞተ አጡ የሚያናምናቸው።
  እርኩሶች በቀን-ፊት ሰዎች ይመስላሉ፤
  የሕዝብ ደም ሲመጡ ማታ እየገደሉ።
  የትናንቱን ታሪክ መዝግቦታል አለ፤
  እነማን ተገድለው ማን እንዳስገደለ።
  ወገን ሲሻ ርቆ የዕለት እንጀራውን፤
  ሰላሙን ሰርቀውት ንብረት ያፈራውን፤
  ባገሩ አዋርዶ ባሪያ-ሁን ያለውን፤
  አህያውን ፈርተን-ለምን ዳውላውን? ? ?
  እናም እናስተውል እንወቅ ለይተን፤
  ቅማሎቹን ትተን፣
  አንጠግብም ፎክተን።
  ይኸውና ደግሞ ግድያቸው ዘልቆ፤
  በስደትም ታየ ባደባባይ ታውቆ።
  እኮ ጀርባ ማከክ በስቃይ መማቀቅ፤
  ቅማሏ ደም መጥጣ ጥጉን ስትደበቅ፤
  እዚህ እዚያ ቢፎከት ሺህ ቢገላበጡ፤
  ቅማሎቹም በዝተው ደሙን እየጠጡ፤
  መፎከቱ ብሶ ቆዳን መላጥ ሲደርስ፤
  ደም መክፈሉ አይቀርም እስካልሞተች ድረስ።
  እናም እስከመቼ ችግሩን ስታዩ፤
  ምክንያት ከሰበብ ቀራችሁ ሳትለዩ።
  በሰበቡ ጮኸን ውግዝ ብንለውም፤
  በቁም ከመሞት ቢሻል:-
  መፍትሔ አይኖረውም።
  ምሥጢሩ ይሄው ነው የአህያ የዳውላው፤
  ፍርሃት ነፃነትን ባሪያ አድርጎ በላው።
  ወገን አርቆ-ሲሻ የዕለት እንጀራውን፤
  ሰላሙን ሰረቁት ንብረት ያፈራውን፤
  ባገሩ አዋርዶ ባሪያ-ሁን ያለውን፤
  አህያውን ፈርተን-ለምን ዳውላውን? ? ?
  ለምን’ስ ይዋሻል በሰበብ አስባቡ፤
  አጋዚ ቅማሏ ቆማ ካጠገቡ፤
  የምን መፎከት ነው ይለይለት እንጂ፤
  ወያኔ ይፈራርስ በሕዝብ አመፅ-ፈንጂ።
  እናም እናስተውል እንወቅ ለይተን፤
  ቅማሎቹን ትተን፣
  አንጠግብም ፎክተን።

  +++++++መታሰቢያነቱ+++++++++
  በሳውዲና በዓለም ላይ
  በስደት ላይ ለሞቱና አሁንም ለሚሰቃዩ ወገኖቼ።
  ተገጣጠመ፣
  ሕዳር ፬ ፳፻፮

 2. Andu Alem Tefera

  November 22, 2013 at 9:29 PM

  አቢይ ኢትዮጵያዊ+ሥጋዊ-ወመንፈሳዊ ሆይ!
  ያቀረቡት ግጥም የልባችንን የሚናገር፤ ጽሑፉ የርስዎ ለቡ ግን የሁላችን ነው።
  በጣም አመሰግናለሁ።
  ከታላቅ አክብሮት ጋር
  አንዱ ዓለም ተፈራ