በሞስኮው የአትሌቲስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ አትሌቶች ውጤት

ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ አገኘች

በሞስኮው የአትሌቲስ ሻምፒዮና በ10ሺ ሜትር ወንዶች ፍፃሜ ኢብራሄም ጀይላን ሁለተኛ በመሆን ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የብር መዳሊያ አስገኝቷል፡፡

ኢብራሄም ጀይላን 27፡22፡23 ሰዓት በመግባት በሁለተኛነት አጠናቋል፡፡ የኦሎምፒክ አሸናፊው እንግሊዛዊ ሞፋራህ ርቀቱን 27፡21፡71 በሆነ ሰዓት አንደኛ ሆኖ ገብቷል፡፡ አበራ ኩማ ውድድሩን 5ኛ ሁኖ ሲያጠናቅቅ ኢማና መርጊያ ደግሞ 12ኛ ወጥቷል፡፡

Ibrahim J vs Mo Farah

Ibrahim J vs Mo Farah

አትዮጵያውያን አትሌቶች በዚህ ርቀት የሚታወቁበትን የቡድን ስራ ሲተገብሩ አለመታየታቸው ለእንግሊዛዊው ሞፋራህ ምቹ ሁኖ ፈጥሮለታል፡፡ በዚህ ውድድር የኬንያ አትሌት ሶስተኛ በመውጣት የኬንያን የመዳሊያ ቁጥር ወደ ሁለት አሳድጎታል፡፡

በሴቶች ማራቶን ኬንያዊቷ ላጋት የውድድሩን የመጀመሪያ ወርቅ ለሀገሯ ማስግኘት ችላለች፡፡

ዛሬ በተካሄደውና ኢትዮጵያ መዳሊያ ታገኝበታለች ተብሎ የተጠበቀው የሴቶች ማራቶን ውድድር 5 ልምድ ያላቸው አትሌቶች ቢሰለፉም ዉጤታማ መሆን ተስኖአቸው ታይቷል፡፡

አበሩ ከበደ ውድድሩን 13ኛ ደረጃ በመያዝ ስታጠናቅቅ ሌሎች አትሌቶች ውድድሩን አቋርጠው ወጥተዋል፡፡ በውድድሩ እንደምታሸንፍ ሰፊ ግምት አግኝታ የነበረችው ቲኪ ገላና በውድድሩ ጅማሬ አቋርጣ ወጥታለች፡፡

በ3ሺ ሜትር መሰናክል የሴቶች ማጣሪያ ኢትዮጵያኖቹ እቴነሽ ዲሮ፣ ህይወት አያሌውና ሶፊያ አሰፋ ማጣሪያውን በቀላሉ ማለፍ ችለዋል፡፡

በሁለት ምድብ ተከፍሎ በተካሄደው ውድድር እቴነሽ ዲሮ በሁለተኛው ምድብ በአንደኝነት ስታጠናቅቅ በዚሁ ምድብ ህይወት አያሌው ሶስተኛ ሁናለች፡፡

በመጀመሪያው ምድብ ሶፊያ አሰፋ ማጣሪያውን የሚያሳልፋትን ውጤት ሶስተኛ በመውጣት አግኝታለች፡፡ ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ በሶስት ሺ ሜትር መሰናክል ሴቶች ያሰለፈቻቸው ተወዳዳሪዎች በሙሉ ማጣሪያውን ማለፍ ችለዋል፡፡

ኢትዮጵያን በ8 መቶ ሜትር የወከለው መሀመድ አማን የመጀመሪያውን ማጣሪያ 1 ደቂቃ ከ44 ሰከንድ ከ93 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት በአንደኝነት አጠናቋል፡፡

የኬኒያና እንግሊዝ አትሌቶች መሀመድ አማንን ተከትለው ገብተዋል፡፡

ውድድሩ ነገ ቀጥሎ የሚካሄድ ሲሆን ምሽት 1፡30 በ8 መቶ ሜትር ፍጻሜ መሀመድ አማንና አማን ወጤ የሜዳሊያ ጅምራችንን የሚያሳድግ ውጤት ለማምጣት ይሮጣሉ፡፡ መሀመድ በዳይመንድ ሊግና በዛሬው ማጣሪያ ካሳየው ብቃት በመነሳት ያሸናፊነት ቅደሚያ ግምት እያገኘ ነው፡፡
ሌላው ከምሸቱ 3 ሰዓት አካባቢ የሚደረገው የሴቶች 10ሺ ሜትር ፍጻሜ የርቀቱን የዓለም ቁጥር አንድ ጥሩነሽ ዲባባን ያሰለፈችው ኢትዮጵያ ወርቁ እንደማትነጠቅ ግምት ተሰጥቷል፡፡

ጥሩነሽ ዲባባ በጥሩ አቋም ላይ መገኘቷ ደግሞ ግምቱን የሚያጠናክር ሁኗል፡፡
-አዝመራው ሞሴ እንደዘገበው

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on August 10, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.