በማንዴላ ሞት መንግሥቱንከግፍ ለማንፃት? በልጅግ ዓሊ

mengistu_HMየማንዴላን ሕልፈተ ሕይወት ተመልክቶ በዓለም ደረጃ የሚያስደንቅ ሁኔታ ስናይ ሰነበትን። ማንዴላ የሠራውን መስራት ሳይሆን እሱ የታሰረበትን ዓላማ በተጻራሪ የሚተገብሩ ሁሉ በቀብሩ ላይ ለመገኘት ከተደበቁበት ብቅ ብቅ ማለታቸው የሚስደምም ነው።

በተለይ አንዳንዶቹ በተለያየ የመገናኛ ዘዴዎች ስለ ማንዴላ ጥሩ ምግባር ቃለ መጠይቅ የሰጡትን  ስናጤናቸው ብዙ የሚያስተዛዝብ ሁኔታዎችን እንገነዘባለን።  በሺህ መጽሐፍ፣ በሽህ ሬዲዩ ቢታገዙም በደም የወየበ ታሪካቸውን  የማይሰርዝላቸው ፋሽሽቶች ይህችን ወቅት ተጠቅመው ለሕዝብ ሃሳቢ ሆነው ለመታየት መራወጣቸው የሚገረም ነው። ይህንን ወቅት ለመጠቀም “እኔም ነበርኩበት“ የሚለው ፋሽሽቱ መንግሥቱ ኃይለማርያምም ሳይቀር ከዚምባዌ ድምጹን አስምቷል። Read story in PDF: በማንዴላ ሞት መንግሥቱንከግፍ ለማንፃት? ….

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on December 15, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

4 Responses to በማንዴላ ሞት መንግሥቱንከግፍ ለማንፃት? በልጅግ ዓሊ

 1. Dagmawi

  December 15, 2013 at 10:55 PM

  እርግጠኛ ሆኖ መናገር ባይቻልም ቃለ መጠይቁን ያደረጉት ጣቢያዎች የመንግስቱ ደጋፊዎች ሆነው አይመስለኝም፦ የታሪክን ፈለግ በመከተል እንጂ። በታሪክ አጋጣሚ ማንዴላ በዓጼው ዘመንም ሆነ በደርግ ዘመን ተገቢ ድጋፍ ሲደረግላቸው መቆየቱ የማይካድ የታሪክ ሀቅ ነው። ታዲያ ይህን ሀቅ ማቅረቡ የመንግስቱ ደጋፊ ማሰኘት አለበት? ወይስ ሁሉም ሰው መንግሥቱን በኢሕአፓ መነጽር ማየት አለበት? ለኔ ኢሕኣፓና ደርግ የሚለያዩብኝ አንዱ ስልጣን ላይ የነበረ ገዳይ አንዱ ስልጣን የለሽ ገዳይ መሆናቸው ብቻ ነው። መንግስቱ በመጥፎም ሆነ በጥሩ ይነሳል። በዓለም እንደ ሂትለር ታሪኩ የተነገረለት ሰው ይኖር ይሆን?

 2. much

  December 16, 2013 at 3:23 AM

  ምነው ወንድሜ ዘላላም ስለ መንግስቱ ሃለማሪያም ጨካኝነት እና ገዳይነት ስትሰብኩ ትኖራላችሁ አወ ማንዲላ የተሰራበትን ግፍ በመተው ለግፍ አድራጊዎች ይቅርታ በማድረክ ሃገሩን እዚህ አድርሶ ያለፈ ጀግና ነው። አወ አንተ እንደምትለው መንግስቱ ጨካን ነው ሰው በላ ነው ግን የነበረበት ጊዜ አልፎ ሌሎች ሰው ከመብላት አልፈው ሃገር ወደመግደል የደረሱ ጠላቶች ተጋርጠውብናል አሁን ማሰብ ያለብን እነዚህን ሰዎች አስወግደን ሃገራችን እንደ ሃገር ህዝባችን እንደህዝብ የሚቀጽልበትን መንገድ ነው መፈለግ ያለብን ወደ ሆዋላ ለተሰራ ነገር ታሪክ እራሱ ይፋረዳል እና ወንድሜ ብዙ ጊዜ በመንግስቱ ሃለማሪያም ላይ ስታላዝኑ ትታያላችሁ እባካችሁ 40 ዓመት የታገላችሁበትን መንገድ ቀይር በማድረግ ስልታችሁን ለውጣችሁ ታገሉ እና ለውጥ ለማምጣት ሞክሩ ዘላለም ወሪ ምንም አይጠቅምም።

 3. ኩኩ

  December 16, 2013 at 5:07 PM

  ማለፊያ ብላችኹል ዳግማዊና መች:: መንግስቱንም ሆነ ሂትለርን ኢሳት ቢያናግራቸው ምን ያህል የተለያዩ ሃሳቦችን ላማንሸራሸር ዝግጁ መሆኑን የሚያመለክት እንጂ ‘ደርግ’ የሚያሰኝ አይደለም:: ኢሳቶችን ለቀቅ! ወያኔን ጠበቅ!

 4. ጃወሳ

  December 18, 2013 at 10:36 AM

  አቶ ብልጅግ አንትና ፓርቲህ ኢሕአፓ አርባ ዓምት ሙሉ ጥላቻ ስትስብኩ አይስላቻቸሁም አንዳ ምች ንው ስው ይምትሆኑት?