በሙስና ምርመራ መበላላት እንዳይጀመር ስጋት አለ

በጉምሩክና ገቢዎች ባለስልጣን የተጀመረው የጸረ ሙስና ዘመቻ ተከትሎ እየተካሄደ ያለው ምርመራ እየተወሳሰበ መሔዱ ተሰማ። በከፍተኛ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ተከሳሾች የሚሰጡት መረጃ መበላላት ያስነሳል የሚል ፍርሃቻ እያስነሳ ነው። “ሰፈር የለየው” የጸረ ሙስና ዘመቻ የፈጠረው ስጋት የሃይል ሚዛን የያዙትንም ስጋት ውስጥ ከትቷል።

በኢትዮጵያ ባለፉት 10 ዓመታት ውስጥ የታየው የውስን ሰዎች በድንገት በመበልጸግ ከባለስልጣኖችና ከከፍተኛ የስርዓቱ ሰዎች ቤተሰቦች ጋር በሚከናወን መተሳሰር አማካይነት እንደሆነ ከህዝብ የተሰወረ አይደለም። ሰሞኑንን ይፋ የተደረገው የባንክና የንብረት እግድ እንዳመለከተው የዝርፊያው ሰንሰለት በቤተሰብ የታጠረ መሆኑን ነው።

አቶ መለስ ከድነው ያቆዩትና የሳቸውን ሞት ተከትሎ ከፖለቲካው ልዩነት ጋር በተያያዘ እንደተጀመረ የሚነገርለት የጸረ ሙስና ዘመቻ፣ በመንግስት በኩል “ቆራጥ” አቋም የተያዘበት እንደሆነ ቢነገርም አስጊ ሁኔታ እየተፈጠረ ስለመሆኑ የጎልጉል የጸረ ሙስና ኮሚሽን ምንጮች ይናገራሉ። …

ሙሉውን በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on June 18, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.