በመንግስት ጥያቄ የጎንደርን ሰላማዊ ሰልፍ ለሐምሌ ሰባት አዘዋውረናል!!

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ
አንድነት ፓርቲ የሶስት ወራት ህዝባዊ ንቅናቄ የትግል ስልት በመንደፍ የመጀመሪያውን የአደባባይ ላይ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ሰኔ 30/10/2005 በጎንደር ከተማ እንደሚያደርግ ማሳወቁ የሚታወስ ነው፡፡ ሁልጊዜም የሀገሪቱን ህግ ጠብቆ በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሰው ፓርቲያችን የአገሪቱ ህገ መንግስት አንቀፅ 30ና የሰላማዊ ሰልፍ አዋጅ 50ኛ ዓመት ቁጥር 4 በሚደነግገው መሰረትም ከህዝቡ ጋር የሚያደርገውን ሰላማዊ ሰልፍ በጎንደር ከተማ ማወቅ ለሚገባው አካልና ለዞኑ አስተዳደር አሳውቆ ወደ ቅስቀሳ በመግባት ከ80 ሺ በላይ በራሪ ወረቀቶችን በማሳተም ከ20 ሺ በላይ በራሪ ወረቀቶችን በጎንደር ከተማ አሰራጭቷል፡፡ በመዋቅራችን አማካኝነትም የቤት ለቤት ቅስቀሳ በማድረግ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ ድምፁን እንዲያሰማ እያደረግን ባለንበት ወቅት በክልሉ መንግስት የማደናቀፍና የማሰር ርምጃ እየተወሰደ ነው፡፡ (ቀሪውን በPDF ያንብቡ)

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on July 9, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.