በመላው አገሪቱ ተጠርቶ የነበረው የሙስሊሞች ተቃውሞ ተሰረዘ

EMF – በመላው ኢትዮጵያ፣ በተለይም በአዲስ አበባ ፍልውሃ አካባቢ በሚገኘው መስጊድ አካባቢ ህዝበ ሙስሊሙ፤ በዛሬው እለት ተቃውሞውን በዝምታ ነገር ግን በጽሁፍ የተዘጋጁ መፈክሮችን በማሳየት በሰላማዊ መንገድ ስሜቱን እንዲገልጽ ጥሪ መደረጉ ይታወሳል። ሆኖም የፌዴራል ፖሊስ ይህንን ጥሪ ተከትሎ ትላንት ምሽቱን መኪኖችን በመፈተሽ እና ቤት ለቤት አሰሳ በማድረግ ሰዎችን በማሰሩ፤ በተለይ በፍልውሃ አካባቢ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የታጠቀ ሃይል በማሰማራቱ ህዝበ ሙስሊሙን በሽብር ውስጥ እንዲቆይ አድርጎት ነበር። በተለይም የፌዴራል ፖሊስ ያወጣው “አስፈላጊውን እርምጃ እንወስዳለን” የሚለው መግለጫ ተጨምሮ፤ ጥሪ አቅራቢው አካል የተቃውሞ ጥሪውን ሰርዞታል።

 ጥሪውን ያቀረበው የ’ድምጻችን ይሰማ’ አካል ባወጣው መግለጫ፤ “የመንግስት የሽብር መግለጫ የሕዝብን አሸናፊነት ያረጋገጠ ነው!” በሚል ር ዕስ መነሻነት የሐምሌ 26ቱ ተቃውሞ እንዲሰረዝ ማድረጉ በህዝቡ ዘንድ ሁለት አይነት ስሜት አጭሯል። አንደኛው ወገን፤ “ሊመጣ የሚችለውን አደጋ አይቶ እንዲህ ያለ ውሳኔ መስጠቱ በሳልነት ነው።” ይላል። ሌላኛው ወገን ደግሞ፤ “መንግስት የፈለገውን መግለጫ ቢያወጣም የተቃውሞ ጥሪው መሰረዝ አልነበረበትም” የሚል ሃሳብ ያቀርባሉ። ይህም ሆኖ የፌዴራል ፖሊስ በህዝበ ሙስሊሙ ላይ ሊወስድ ያሰበውን እርምጃ አጠናክሮ የሚቀጥል ነው የሚመስለው። በሚቀጥሉት ሰአታት የሚፈጠረውን ማወቅ አይቻልም። ሆኖም አዲስ ነገር ካለ ዘገባችንን እንቀጥላለን። እስከዚያው ግን፤ ለጁምአ ሐምሌ 26 የታቀዱ ተቃውሞዎች በመላው አገሪቱ መሰረዙን ይፋ ያደረገውን መግለጫ፤ ሙሉ ቃል ከዚህ በመቀጠል እናቀርባለን። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ።)
Ethiopian-Muslims-Protest

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on August 2, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.