በሐውዜን፣ ትግራይ ጥያቄ ያቀረቡ ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ እየተገረፉ ነው

ከትግራይ የደረሰን ዘገባ እንዲህ ይላል። በሓውዜን የልማት ጉዳይ አንስተው ከመንግስት አካላት ጋር ተከራክረው ያለ ምንም ወንጀል ከታሰሩ ስድስት ሰዎች በሦስቱ ታሳሪዎች ላይ አሰቃቂ መግረፍት (ቶርቸር) እየደረሰ መሆኑ ከሓውዜን የደረሰኝ መረጃ ይጠቁማል።

ህዝብ የወከላቸው ስድስቱ ልጆች ጥያቄ ስለጠየቁ ብቻ በዝግ እስርቤት ይገኛሉ።

ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዳይገናኙ ተደርገዋል። ያለ ምንም ፍርድ ከ48 ሰዓታት በላይ (እስካሁን ለሦስት ቀናት ያህል) ታስረው ምግብ እንደማያገኙ ታውቋል።

በአሁኑ ግዜ መግረፍት (ቶርቸር) እየተፈፀመባቸው ያሉ እስረኞች

(1) ሳሙ ኤል ገብረመድህን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተወካይ
(2)ሃይሉሽ ሓጎስ (ወዲ ኣፍሮ)፡ ኣቦ መንበር ባዜን ባንድ
(3)ካልኣዩ ሂወት ተምሃራይ ኣጋርፋ ሕርሻ ኮሌጅ

የሚድያ ሰዎች እየተፈፀመ ያለ አሰቃቂ ግፍ በማጋለጥ ሙያዊ ግዴታቸው እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

(አብርሃ ደስታ ከስፍራው እንደዘገበው)

Tortured Ethiopian victim

Tortured Ethiopian victim

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on August 6, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to በሐውዜን፣ ትግራይ ጥያቄ ያቀረቡ ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ እየተገረፉ ነው

  1. Teshale

    August 12, 2013 at 10:17 AM

    ወያኔ ለትግራይ የቆመ ይምሰል እንጂ ጭካኔው የሚበረታው በትግራዮች ላይ ነው። ልክ ዛሬ ሻቢያ በኤርትራዎች ላይ እንደሚጨክነው። ለኔ እስከሚገባኝ ድረስ ወያኔ በትግራይ ልጆች ደም ለኤርትራ የሚሰራ አካል ነው። ወያኔ ቁንጮ ላይ ያሉ ግለሰቦች አሁንም ስለኤርትራ ይጨነቃሉ። ህልማቸውም ትግራይን ገንጥለው የኤርትራ ባሪያ ማድረግ ነው።