በሀገረማርያም የአንድነት ምክርቤት አባልን ጨምሮ 9 ሰዎች ታሰሩ

* ሀዝቡ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ተዘጋጅታል
* አቶ አስራት ወደ ቅሊንጦ ወህኒ ቤት ተወሰዱ

የአንድነት ፓርቲ የምክር ቤት አባል አቶ ጌታቸው በቀለን ጨምሮ 9 የሀገረ ማርያም ደብረ ገነት ቅድስተ ማርያም ቤተክርስቲያን ሽማግሌዎች መታሰራቸውን በስፍራው የሚገኘው የግኖተ ነፃነት ሪፖርተር ዘገበ፡፡ ዘገባው እንደሚያስረዳው ካለፈው አመት ጀምሮ በቤተክርስቲያኒቱ የአስተዳዳሪ ለውት ከተደረገ ጀምሮ ሙስናና የተለያዩ የስነምግባር ቸግሮች በመታየታቸውን ተከትሎ በአካባቢው ህዝብ ከተመረቱት ሽማግሌዎች መካከል የአንድነት ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ጌታቸው በቀለን ጨምሮ 9 ግለሰቦች ታስረዋል፡፡ የደቡብ ኢትዮጵያ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የሆኑት አቡነ ገብርኤል ችግሩን ለመፍታታ ወደ ስፍራው በማምራት ላይ ይገኛሉ፡፡ የአካባቢው ህብረተሰብ ተጨማሪ ታሳሪዎች ሊኖሩ ይችላሉ በሚል ስጋት ላይ ቢሆንም እስሩን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እየተዘጋጀ መሆኑ ታውቋቋል፡፡

አቶ አስራት ወደ ቅሊንጦ ወህኒ ቤት ተወሰዱ
February 10, 2014

አቶ አስራት ጣሴ በአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ለ3 ቀናት እንዲቆዩ ከተደረገ በኋላ ምክን ያቱ ለጊዜው ግልፅ ባልሆነ ውሳኔ ወደ ቂሊንጦ ከፍተኛ ጥበቃ ወህኒቤት እንዲዛወሩ መደረጉን የፍኖተ ነፃነት የፖሊስ ምንጮች አሳውቀዋል፡፡
የፖሊስ ምንጮቹ እንዳሉት ኦአስራት በፖሊስ ጣቢያው በቆዩባቸው ጊዜያት በእስረኛው ተገቢው አክብሮትና መልካም አቀባበል ማግኘታቸው አሳሪዎቻቸውን አላስደሰተም፡፡
አንድነት ፓርቲን ከምስረታው ጀምሮ በከፍተኛ አመራርነት ሲያገለግሉ የቆዩትና በአሁኑ ወቅትም በፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤትና ስራ አስፈፃሚ የፓርቲዎችን ውህደት እንዲመሩና የአማካሪ ምክርቤት እንዲያቋቁሙ ኃላፊነት የተሰጣቸው መሆኑ ይታወቃል፡፡ አንድነት “የሚሊዮኖች ድምፅ ለፍትህ” በሚል መሪቃል የመንግስት የተለያጡ ሀላፊዎችን ለመክሰስ እንቅስቃሴ ማድረጉን ተከትሎ መንግስትም የአንድነት ፓርቲ አመራሮችን ምክንያት እየፈለገ መክሰስና ማሰር መጀመሩ ገዢው ፓርቲ አለመረጋጋት ውስጥ እንደገባ የሚያመላክት ነው፡፡

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on February 12, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.