ቃልቲ ማረሚያ ቤት የሚገኙት ሁለት የስዊድን ጋዜጠኞች ዛሬ ፍ/ቤት ይቀርባሉ

– ጋዜጠኛ ስለሺ ሀጎስና አርቲስት ደበበ እሸቱ ሐሙስ እና ዓርብ ይቀርባሉ

“ያለፍቃድ የአገሪቱን ድንበር አቋርጠው የገቡትና በሽብርተኝነት ከተፈረጀው ከኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር/ኦብነግ/ጋር ሲንቀሳቀሱ ተገኝተዋል” ተብለው በቃልቲ ማረሚያ ቤት የሚገኙት ሁለት የስዊድን ጋዜጠኞች ዛሬ ልደታ በሚገኘው ከፍተኛ ፍ/ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት እንደሚቀርቡ ከተያዘው ቀጠሮ መረዳት ተችሏል፡፡

ቀደም ሲል ፍ/ቤት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃላቸውን የሰጡት ጋዜጠኞች መከሰሳቸውንና ከኦብነግ ጋር የትጥቅ ትግል ለማድረግ ተንቀሳቅሰዋል ምባሉን አስተባብለው በኬኒያ ሱማሌ በኩል አድርገው ወደ ኢትዮጵያ ድንበር የዘለቁት የጋዜጠኝነት ዘገባ ለመሥራት መሆኑን ገለፀዋል፡፡ ዐቃቢ ህግ በበኩሉ “በሽብር ተግባር ሲንቀሳቀሱ መገኘታቸውን የሚያረጋግጥ የሰው ማስረጃ አለኝ” በማለቱ ፍ/ቤቱ መስክሮቹን ለዛሬ አስቀርቦ እንዲያሰማ ቀጠሮ
መያዙ ይታወቃል፡፡

በሌላ በኩል “በሽብርተኝነት”ተጠርጥረው ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ የሚገኙት ጋዜጠኛ ስለሺ ሀጐስና አርቲስት ደበበ እሸቱ በሚቀጥለው ሐሙስና ዐርብ ለ3ኛ ጊዜ ፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ችሎት እንደሚቀርቡ ከቤተሰቦቻቸው ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡ ባገኘነው መረጃ መሠረት ጋዜጠኛ ስለሺ ሀጐስ ሐሙስ የሚቀርብ ሲሆን አርቲስት ደበበ እሸቱ ዐርብ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፡ ፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on November 2, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.