ቃለመጠይቅ – ከተስፋዬ ገብረአብ ጋር (“ላይፍ” መፅሄት)

life…የምንሰማው እውነት ከሆነ ከመቀሌው አባይ በስተጀርባ ቴዎድሮስ ሃጎስ አለ። ከአዲሳባው አባይ ስር እነ ጌታቸው አሰፋ፣ እነ ደብረፅዮን መሰለፋቸው ይሰማል። ሳሞራ የአዲሳባውን አባይ ተቀላቅሎአል። አዜብ ‘አርፈሽ ቁጭ በይ! የመለስን ፋውንዴሽን ተከታተይ’ ተብላለች። እብድ ስለሆነች ያልተጠበቀ ነገር እንዳትፈፅም በመስጋት ሰንሰለቷን ሁሉ በጣጥሰውባታል። የዘረፋ ቀዳዳዎቿን እየዘጉባት ነው። ያም ሆኖ አዜብ አርፋ ትቀመጣለች ተብሎ አይታመንም። መሞከሯ አይቀርም። የግል አስተያየቴን ለመስጠት ያህል፣ የመቀሌ – አዲሳባ ሽኩቻ ይፋ ሳይወጣ ውስጥ ውስጡን ሊጠናቀቅ ይችላል። ሁለቱ ተቀናቃኝ ወገኖች ሽጉጥ ከተኮሱ ቤተመንግስቷን ለዘልአለሙ እንደሚያጧት ያውቃሉና ሽጉጥ ወደ መምዘዝ የሚገቡ አይመስለኝም። ከሁለቱ ቡድኖች አንደኛው እስኪያሸንፍ ሃይለማርያም ወንበሩን በታማኝነት ይጠብቅላቸዋል። ማን በአሸናፊነት ሊወጣ እንደሚችል አብረን እናየዋለን። የአዲሳባው ቡድን የሚበረታ ይመስለኛል። ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከሁለቱም ቡድኖች ገለልተኛ ሆኖ የአስታራቂነት ሚና ለመጫወት እሞከረ ነው። ምናልባት እሱን በማንገስ ልዩነታቸውን ይፈቱ ይሆናል።… ሙሉውን የ “ላይፍ” መፅሄት ቃለ-መጠይቅ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ…

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on September 28, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

9 Responses to ቃለመጠይቅ – ከተስፋዬ ገብረአብ ጋር (“ላይፍ” መፅሄት)

 1. Pingback: ቃለመጠይቅ – ከተስፋዬ ገብረአብ ጋር (“ላይፍ” መፅሄት) - EthioExplorer.com | EthioExplorer.com

 2. ሰለሞን

  September 29, 2013 at 5:01 PM

  ተስፋዬን ክሀገር ከወጣ ል3ኛ ጊዜ ከስደተኛው ጋዜጠኛ በሚል ልናገኘው ነው ማለት ነው።
  ቀደም ሲል የወጡት ሁለቱ መጽህፎቹ በተቆራረጡ ጹሁፎች የተሞሉ ሲሆን ምስጢር አዋቂ ነኝ ከማለቱ አንጻር ግን አጥጋቢ አልነበሩም ።በአሁኑ ቃለ መጠይቅም ላይ ተስፋዬን ያገኘሁት ከነ ትቢቱ ነው። ተስፋዬ በዛች ምድር ላይ የ ኦሮሞ ህዝብ ተቆርቃሪ በመምሰል አሮሞንና አማራን ለማጋጨት ያልቆፈረው ድንጋይ የለም ።
  ከሁሉም የገረመኝ ከ ኦሮሞው ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የበለጠ የ ኦሮሞ ተቆርቃሪ ነኝ ማለቱ ነው። ጠያቂው በብዙ ጹሁፎችህ ለኦሮሞ መብትና ጥቅም የመቆም ዝንባሌ ታሳያለህ። ነጋሶ እንዳሉትከ ኦሮሞ በላይ ኦሮሞ ነኝ ማለትን ታበዛለህ ምላሽህ ምንድነው ተብሎ ለተጠየቀው ሲመልስ።
  የነጋሶን አባባል ሰምቻለሁበማለት ለሎችን ለማስደሰት እንጂ የውስጣቸውን ተናግረው አያውቁም በማለት ካሽማጠጠ በሃላ የዶክተር ነጋሶን ከብሄር ድርጅት ወጥተው ወደ ህብረ ብሄር ፓርቲ መምጣታቸው አልወደደውም እንዲያውም መርህ አልባ ናቸው በማለት በፕሬዝደንት ዘመናቸው የተናገሩትን አንዳንድ ነገሮች ጥቅሶ አሁን 180 ዲግሪ ዞረው የራስ ጎበና ዳጪ ተከታይ ሆነዋል ይለናል።
  ተመልከቱ ለተስፋየ የዶክተር ነጋሶ ለ ኢትዮጵያ አንድነት መቆም መርህ አልባ አስኝቶአቸዋል እንደገናም ለ ኢትዮጵያ አንድነት መቆም ዛሬም ለተስፋዬና መሰሎቹ ጎበና ዳጪነት ነው። በ እርግጥ ራስ ጎበና ዳጪ አሁን ለምናውቃት ኢትዮጵያ የራሳቸውን ጉልህ ድርሻ የተወጡ በ ኢትዮጵያ አንድነት ለሚያምኑ ሁሉ የጀግኖች ጀግና ናቸው።
  በመቀጠል ከጳጳሱ ቄሱ እንዲሉ ስለ ኦሮሞ ህዝብ ጥብቅና እኔ ከነጋሶ የበለጠ እየሰራሁ ነው ምክንያቱም በኦሮሞ ህዝብ መካከል ደብረዘይት ተወልጄ ያደግሁ ራሴን ኦሮሞ ብዬ ለመጥራት የሞራል ብቃት ያለኝ ሰው ነኝ ይለናል ተስፍዬ። በመጀመሪያ ደረጃ ደብረዘይት ከተማ ወያኔ ወደ ስልጣን ከመምጣቱ በፊት በተለይ ኦሮሞውና አማራው በፍቅር የሚኖሩባት እኔ እራሴ የነዚህ ሁለት ታላላቅ ብሄረሰቦች አብራክ የተገኘሁ ነኝ ከሁለቱ ብሄረሰቦች ውጭ በስራው የሚኮራው የጉራጌና እንዲሁም የትግሬ ብሄረሰቦች ሌሎችም የሚኖሩባት ብርቅዬ ከተማ ነበረች ። በነገራችን ላይ ትግሬ ስል ሁለቱንም ያጠቃልላል።
  የተስፋዬ ለኦሮሞ ህዝብ ጥብቅና መቆም የሚመነጨው በጦርነቱ ወቅት በመሃል ህገር የሚኖሩ አብላጫው ዔርትራዊ ከሚያሰሙት እሮሮ ማለትም አማሮች ዘመዶቻችንን ፈጁ ከሚለው ተደጋጋሚ ቃል በመነሳት ነው። ይህንን ልል ያስቻለኝ ወያኔ አዲስ አበባን ሻቢያ አስመራን ሲቆጣጠሩ አብሮ አደግ ጋደኞቻችን የነበሩ የተስፋዬ ዘመዶች በሁሉም የ ኢትዮጵያ ከተሞች ምን እንዳደረጉ የምናውቀው ጉዳይ ነበርና ነው። እንዲያውም ተስፋዬ ከዛ ጥላቻ ውስጥ አለመውጣቱን በዚሁ ቃለ መጠይቅ ላይ ስለ ዔርትራና ኢትዮጵያ የወደፊት ውህደት ሲጠየቅ የመለሰው መልስ ላይ እንዴት ተደርጎ ነው አንድ የሚሆኑት 30 ዕመት ጦርነት ለምን ተደረገ እንደገናስ በባድመ ጦርነትስ ያ ሁሉ ህዝብ ካለቀ በሃላ አንድነት የሚባል ነገር አይታሰብም ጥሩ ጎረቤት ከሆኑ በራሱ በቂ ነው ባይ ነው። ተስፋዬ በቡርቃ ዝምታ መጽሀፉ ላይ ኦሮሞን ለበቀል ይጋብዛል ። በበቀል እና በጥላቻ የታወረው አይምሮው አሁንም በጎ ማሰብ ተስኖት በውጭው አለም የአኢትዮጵያውያኑንና የ ዔርትራውያኑን ምልካም ግኑኝነት እያየ ምሁራኖች ቢቻል በፌዴሬሽን ካልትቻለም በኮንፌዴሬሽን መኖር አለብን እያሉ ባሉበት ሰአት ነው ተስፋዬቁርሾ የሚቀሰቅሰው ለማንኛውም ተስፋዬ አንተ በምንም ምክንያት ከነጋሶ በበለጠ ለኦሮሞ አሳቢ ልትሆን አትችልምና ቀልድህን ብታቆም መልካም ነው።

 3. ezra musse

  September 29, 2013 at 7:21 PM

  ተስፋዬ ገ/አብ ያለበትን የዝቅተኝነት ስሜት ስቃይ መወጣት የሚችለው አይደለም ከእርሱ ጋ ከዛሬው አባቱ ከኢሳያስ አንጎል በላይ የሆኑትን ታላላቅ ሰዎች በመዘረጠጥ ነው:: እንዲህ ሲያደረግም ነው የአይምሮ ትንሽነቱን መደበቅ የሚችለው:: ምክኒያቱም ተስፋዬ ገ/አብ እድሜ ለእነ በረከት ይበልና /// በሞላው ጭንቅላቱና ማህይምነቱ ተጀቡኖ ከእነ ሙሉጌታ ሉሌ ወንበር ላይ በረከት አስቀመጠውና እነ በረከት ስምኦን እንዳሻቸው ሲጋልቡት ኖረው..ሲበቃቸው ደግሞ አሳፍረው/ጭነው ወደ እብዱና የባሮች ኮርማ እሳያስ አፈወርቂ ጫማ ስር ወተፉት :: ትንሽ እዉቀት አደገኛ ነው የሚለው አባባል የተስፋዬን ሥነ ልቦና ገላጭ መሆኑን መቀበል አቅቶት እነሆ አሁን ደግሞ የሰላቶን የ60 ዓመት የባረነት አገዛዝ የጥጋብ ጊዘ እያለ የሚያወድሰዉን አባቱን ኢሳያስ አፈወርቂ ትፋ የሚለዉን እያቀረሼ ይገኛል:: ውሻ በበላበት ይጮሃል አለ የሚጣላው አማራ ቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

 4. Kebede

  September 29, 2013 at 7:41 PM

  ዝም ብለህ በአፍህ አትቅዘን እባክህ:: እንተ እንደገና አሥር ጊዜ ምተህ አሥር ጊዜ ብትፈጠር የተስፋዬን ጭሎታ ማግኘት አትችልም:: ለፍላፊ ባለጌ::እንዲሁ እንዳወራህ በጉራ ትሞታለህ:: አንት የኮምፕዩተር አርበኛ!!የደንቆሮዎች ችሎታ ያው ስድብ ነው:: ሌላ ምን ታውቃለህ?

 5. Tesfaye Gebreab

  October 1, 2013 at 1:37 PM

  ከተሰደድኩ ወዲህ የብእር ስም ተጠቅሜ ፅፌ አላውቅም። አገር ቤት እያለሁ ግን “ዳግማዊ መንቆርዮስ”፣ እና “ዋለልኝ ብርሃነ” የሚሉ የብእር ስሞችን በመጠቀም እፅፍ ነበር። የመንግስት ስራ ሆኖብኝ መጣጥፍ እንድፅፍ ስገደድ በብእር ስም እለቀው ነበር። ምክንያቱም የኔ መሆኑ እንዲታወቅ አልፈልግም ነበር። የማምንበትን ስፅፍ ግን በኩራት ስሜን እፅፋለሁ። በመሆኑም በአብዛኛው የብእር ስም የሚጠቀሙ ሰዎች የሚፅፉትን አያምኑበት ይሆናል። “በአብዛኛው” አልኩ እንጂ “ሁሉም” አላልኩም። የተከበሩ የጥበብ ስራዎችን በብእር ስም የሚፅፉ ሰዎችን አውቃለሁ።

  ለአብነት “ወለላዬ” በሚል የብእር ስም ግጥሞችን የሚፅፈው ሰው ራሱን ለመደበቅ ብሎ አይደለም። ማቴዎስ ከተማ ይባላል። ስቶክሆልም ነው የሚኖረው። አንድ ጊዜ ስለብእር ስም ስናወራ፣ “ሴት መስዬአቸው የስጦታ ሊፒስቲክ የሚልኩልኝ አሉ” ብሎ አስቆኛል። ቢሳሳቱ ተገቢ ነው። ሽታዬ፣ ሙናዬ፣ ዋጋዬ፣ ወለላዬ እንዲሉ።

  በቀጥታ በስማቸው የሚጠቀሙ ፀሃፊዎች ሃላፊነት ስለሚሰማቸው በሚያነሱት አሳብ እና በሚመርጡት ቃላት ላይ በጣም ይጠነቀቃሉ። ባይጠነቀቁም የሚከተለውን ሙገሳም ሆነ ወቀሳ የሚሸከሙት ራሳቸው ናቸው።

  ኤልያስ ክፍሌ ለዚህ ጥሩ አርአያ ነው። ለህይወቱ አደጋ ሊሆን የሚችለውን አጀንዳ ሳይቀር በስሙ እና በአባቱ ስም ቁጭ ያደርገዋል። መስዋእትነት መክፈል ከሆነ እንዲህ ነው። ዶክተር ጌታቸው ሃይሌ እና አልማርያም በተመሳሳይ አርአያ ሊሆኑ ከሚችሉት መካከል ናቸው። ከፃፉ በስማቸው ይፅፋሉ። ካልፃፉ የሉም ማለት ነው። መሳይ ከበደ፣ ክንፉ አሰፋ፣ ተክለሚካኤል አበበ በስማቸው ከሚፅፉት መካከል ናቸው። ልጅ ተክሌ ስሙን ብቻ ሳይሆን የሚኖርበትን ከተማ ጭምር ይፅፋል። የቤት ቁጥሩን ሊፅፍ ትንሽ ነው የሚቀረው። በርግጥ ብእር ስም ስር ተሸሽገው መሳደብ የለመዱት በአብዛኛው ስደተኞች ናቸው። በአገርቤት ያሉ በዚህ አይታሙም። መስፍን ወልደማርያም፣ ተመስገን ደሳለኝ፣ አብርሃ ደስታ እያልን ብዙ መጥራት ይቻላል…

  በልጅግ አሊ በሚል የብእር ስም የግለሰቦችን ስም እያነሳ የሚዛለፍ ፀሃፊ አለ። የወተት ስሙ እንዳይታወቅበት በጣም ይፈራል። አንዳንዶቹ እንዲህ ፊትለፊት በስማቸው መውጣት የሚፈሩት የሚሳቀቁበት ታሪክ ቢኖራቸው ይሆናል። እኔ በፃፍኳቸው መፃህፍት ላይ በስማቸው አስተያየት የፃፉት በጣም ጥቂት ናቸው። ዶክተር ጌታቸው ሃይሌ፣ በፍቃዱ ሞረዳ፣ መስፍን ነጋሽ፣ አለማየሁ ገላጋይ ትዝ ይሉኛል። ባርኔጣዬን በክብር አነሳላቸዋለሁ። ስድብ የተሞላበት ፅሁፍ ኢትዮሜድያ ላይ ሲፅፉ የነበሩት አብዛኞቹ ሰላቢ ፀሃፊዎች በፍርሃት ጥቁር ብርድልብስ የተጠቀለሉ ናቸው። ወይም ያልሆኑትን በመምሰል ድብቅ አጀንዳቸውን የሚረጩ ናቸው።

  “ሰላቢ” ከማለት የተሻለ ስም ላገኝላቸው አልቻልኩም። እነዚህ ጥልማሞቶች “ሸሚዛችን እስኪቃጠል የሃገር ፍቅር አለን” ይላሉ። ሆኖም ህይወታቸውን ቀርቶ ስማቸውን እንኳ ለሚወዷት ሃገራቸው መሰዋት አይችሉም። ፈሪና ጨካኝ ናቸው። ፈሪ የሆኑት በራሳቸው ስለማይተማመኑ ነው። ማንም ስለማያውቃቸው ደግሞ ጨካኝ ይሆናሉ። ሃላፊነት አይሰማቸውም። ፅሁፋቸውን የሚያትሙበት ድረገፅ ሃላፊነቱን እንዲሸከምላቸው ይፈልጋሉ።

  በቅርቡ ግን አንድ ወሬ ሰምቻለሁ።

  በብእር ስም ተሸሽገው የተሳሳተ መረጃ የሚፅፉና የሚሳደቡ ሰላቢ ብእረኞችን ላለማስተናገድ የድረገፅ ዋና አዘጋጆች በመነጋገር ላይ ናቸው። በቅርቡ ኢትዮሜዲያ በብእር ስም የፃፈ ሰላቢ ካስተናገደ በሁዋላ መልሶ ፅሁፉን አስወግዶታል። ይህ አንድ ትልቅ እርምጃ ነው። አሉባልታውን ይቀንሰዋል። ሃላፊነት የሚሰማቸው አሳቦችም ለመነበብ ይበቃሉ።

  • mulugeta

   October 4, 2013 at 8:25 AM

   ተስፋየ የጥበብ ፍቅር ኣለህ፣ ደግሞም በጣም ጥሩ ጸሃፊ ነህ
   ነገር ግን ፣የምትጽፈው በፖለቲካ ነክ ነገሮችን ኣስበህ ምን ልጻፍ ፣ማነን ልንካ ብለህ ኣጥንተህ ነው፣ጸሃፊ ደግሞ ፣ተሰጦው ወየም የጥበብ ኣባዜው ከላይ ይሁን ከውስጥ ፣ሲገፋው ኣያሳስበዉም፣አንደው አንደመጣለት ያወርደዋል አንጂ እዚህላይ ፣ቅርጽ መስጠቱ፣መቼቶቹን መቀባባቱ፣አንዳለ ሆኖ ፣ማለት ነው ፣የደከመ የመሰለዉን ታሪክ፣ቀንጨብ በማድረግ ፣ተደብቆ የነበረዉን፣መርምሬ፣ ኣወጣዉት ፣ሰራሁላቸው፣ኣይነት ፣ተራ፣ከዉስጥ የሚታገለህን ፣የፍርሃት ይሁን የነጋቲቭ፣ ስሜጥን፣ለመወጣት፣ሁሌም፣ በሃገራችን ፣ላይ፣እንደምትጥር፣ በብዙ ፣ጽሁፎጭ፣እና ፣መጽሃፎጭ ላይ ታንጸባርቃለህ ፣
   ከቃለ መጠይቕህ ላይ ፣፤ራሰህ፣አንደተናገርከው፣ ጸሃፊ፣ያልኖራትን፣ባይነካ፣ይመረጣል ፤፤፤ኣንተ የታሪክ ጸሃፊ፣ኣይደለህ፣ወይ ተመራማሪ፣ ላንተ ድክመት፣ ወይም፣ምስጢር፣የመሰለህን፣የነገስታቶች ታሪክ፣ነካ እያደረገህ፣ ሚስጢሩ ፣ከምን፣ይሆን፣ለዛዉም፣እኔ፣ኣንተ፣ልናደርገው፣ወይም ፣ሊገጥመን፣ከሚችሉት፣የመወለድ፣ወየም የመዛመድ፣ሰዋዊ፣ኣጋጣሚ፣፣ውጪ፣ ለጎርጎር ትሞክራለህ፤፤፤በወያኔስ፣ዘመን፣ሳልፈልግ፣ኣብረኣቸው ስለኖርኩ ፣ነው ብለሃል፣በምኒሊክ፣በሃይለስላሰ፡ዘመነስ፣፣
   ሌላዉ፣ደግሞ የኢትዮዽያ፣ እና፣የ አርትራ ዉህደት፣ሃሳብህን፣ሲተይቕ ደነገጥክ፣ምነው፣ምን፣ያስፈራሃል ፣የመታውቃቸው፣ህዝቦች፣እኮ፣ናቸው።ባይመስለህ እንኩኣን፣ሁለቱንም፣ሃሳቦች፣ጠቀስ ኣድርገህ።ኣይዋሃዱም፣የሚለዉን፣መደምደሚያ፣ስለምትፈራ።ማቅረብ ትችላለህ፣ግን፣እኛ፣ኣኢትዮጵያውያን፣ይኸዉልህ፣መጽሃፍህን፣እናነባለን፣፣አንገዛለን፣ድግሞም፣የኛ፣ልጅ፣ነው፣ብለን እናስባለን፣ኣንተ፣፣ተኝተህ፣ኣታድርም ፣ለዚህች፣ሃገር ፣ቢሽፍቱን ትናፍቃለህ፣ሃብታም፣ሆነህ፣ቱሪስት፣ሆነህ ፣ልትንደላቀቅባት ፣ሚስጥሩ፣ምን ፣ይሆን፣ምን፣ኣስቀየምንህ፣፣፣፣ምን፣ይሆን

 6. ezra musse

  October 3, 2013 at 7:06 AM

  አዬ ተስፋዬ ገ/አብ ! አንተም እነደዚህ አልክ…? አስገራሚ ፍጡር ነህ:: ተስፋዬ ገ/አብ እንደህም ይለላል – “በብዕር ሰም የሚፅፉ” ይልና በራሳቸው የማይተማመኑና የሚፅፉትንም የማያምኑበት ሰለሆነ ነው እያለ የእርሱን “ንጹኃንን” ወደ ጉድጉዳ የወረወረበትን የጭካኔ ድፋረቱን ያሞግሳል ቂ ቂ ቂ ቂ:: አዬ ተስፍሽ! ሰው መሳይ በሸንጎ ይልኃል እንዲህ ነው:: እንኳንስ የሠላይን እና የነብሰ ገዳይን አጫፋሪ ሥነ ልቡና ቀርቶ የዝንብ ጠንጋራም እናውቃለን እንልኃልን:: ብዙ ጊዘ የሰው ደም የጠጡ: ሰዎችን በአሠቃቂ ሁኔታ የገደሉና ያስገደሉ ግለሰቦች ንጽህ ሰው ለመመስል አስቀደመው ጣጣቸዉን ወደሌላ ይቀስራሉ:: ይሄ ደግሞ የሰው ደም የሚያቃዥቸውና በሰው ህይዎት ላይ እንደ እንስሳ “የተጫወቱ” ሰዎች እውነተኛ ባህሪ ነው:: እስቲ በፈጣሪ አሁን ማን ይሙት ተስፋዬ ገ/ኣብ እና ሽፈራው ሽጉጤ በምን ይለያያሉ..? አዎን ምን አልባት አሁን ተስፋዬ ጌታ ቀይሩአል ትናንት በረከት አስደግድጎታል አሁን ደግሞ አዲሱ ጌታው ኢሳያስ ጫማ ሥር ተደፍቱአል:: ተስፋዬ ገ/አብ እዉነቱን እነንገርህና … እንዳአንተ በሕፅናት ደም እጁን የታጠበ ሰው ማንንም ምንምም አይፈራም – ምክንያቱም ሕፅናትን ወደ ገደል ለመወረወረ ህሊናው የደፈረ ሰው ማንን ሊፈራ ይችላል ህሊናውን ያልፈራ ? ስለዚህ በዓለም ላይ ጤነኛ የሆኑ ሰዎች እንደ አንተ ዓይነቱን ሰው እየፈሩ እየሸሹ ይኖራሉ እንጅ እንዴት ከአዉሬ ጋር ለመጠጋት ይደፍራሉ…? አውሬው ነው ራሱ ሰዎችን እያዘናጋ ቀረቦ ለመቀረጠፍ የሚሞከረው እንልሃልን:: የአንተ ዓይነት ሰው በራሱ ፈቃድ ራሱ የሰዉነት ክበሩን አሳልፎና አዉርዶ በሕፅናት ደም ያጨማለቀና ያጨቀዬ ሰው ዘወተር በፍርሃት ነው የሚኖረው;; ያ ፍርሃቱን ለመደበቅ ከሁሉም ጋር ይናደፋል:: አስቀደሞም ሰዎችን ጭቃ ይቀባል:: ለዚህም ነው እንደ ዶክተር ንጋሶ ጊዳዳ ዓይነት ሰዎችን ከፍና ዝቅ ማደረግ የሚያስደስተው:: ለምን ተስፋዬን ያውቁታል እና ነው:: እንጂማ እንደ አንተ ዓይነት ሰው ልክ እንደ ታምራት ላይኔ አፍን ዘገቶ መቀመጥ የነበረብህ ሰው ነህ:: ግን ምን ይሆናል የገብርኤልን መገበሪያ የበላ ሰው ያስለፈልፈዋል ሆኖብህ በሕፅናት ደም የታጠብክበት አይምሮህ እንቅልፍ ስለሚነሳህ ዘወትር እንደባነንክ ትኖራለህ:: ሠላይ ነህና የሰው ነፍስ የማጥፋጥ ዛርህ ዛሬም ስለሚያቅበጠብጥህ እነሆ ይሄንን ዛረህን ገላጭ የሆነው መረጃ በዳኛ ወልደ ሚካኤል መሸሻ ለኢትዮጵያዊያን ተበትኑአል:: ዳኛ ወለደ ገብርኤል እግዚአብሔር ይስጣቸው::

 7. mulugeta

  October 3, 2013 at 8:08 AM

  ልተስፋየ የጥበብ ፍቅር ኣለህ፣ ደግሞም በጣም ጥሩ ጸሃፊ ነህ
  ነገር ግን ፣የምትጽፈው በፖለቲካ ነክ ነገሮችን ኣስበህ ምን ልጻፍ ፣ማነን ልንካ ብለህ ኣጥንተህ ነው፣ጸሃፊ ደግሞ ፣ተሰጦው ወየም የጥበብ ኣባዜው ከላይ ይሁን ከውስጥ ፣ሲገፋው ኣያሳስበዉም፣አንደው አንደመጣለት ያወርደዋል አንጂ እዚህላይ ፣ቅርጽ መስጠቱ፣መቼቶቹን መቀባባቱ፣አንዳለ ሆኖ ፣ማለት ነው ፣የደከመ የመሰለዉን ታሪክ፣ቀንጨብ በማድረግ ፣ተደብቆ የነበረዉን፣መርምሬ፣ ኣወጣዉት ፣ሰራሁላቸው፣ኣይነት ፣ተራ፣ከዉስጥ የሚታገለህን ፣የፍርሃት ይሁን የነጋቲቭ፣ ስሜጥን፣ለመወጣት፣ሁሌም፣ በሃገራችን ፣ላይ፣እንደምትጥር፣ በብዙ ፣ጽሁፎጭ፣እና ፣መጽሃፎጭ ላይ ታንጸባርቃለህ ፣
  ከቃለ መጠይቕህ ላይ ፣፤ራሰህ፣አንደተናገርከው፣ ጸሃፊ፣ያልኖራትን፣ባይነካ፣ይመረጣል ፤፤፤ኣንተ የታሪክ ጸሃፊ፣ኣይደለህ፣ወይ ተመራማሪ፣ ላንተ ድክመት፣ ወይም፣ምስጢር፣የመሰለህን፣የነገስታቶች ታሪክ፣ነካ እያደረገህ፣ ሚስጢሩ ፣ከምን፣ይሆን፣ለዛዉም፣እኔ፣ኣንተ፣ልናደርገው፣ወይም ፣ሊገጥመን፣ከሚችሉት፣የመወለድ፣ወየም የመዛመድ፣ሰዋዊ፣ኣጋጣሚ፣፣ውጪ፣ ለጎርጎር ትሞክራለህ፤፤፤በወያኔስ፣ዘመን፣ሳልፈልግ፣ኣብረኣቸው ስለኖርኩ ፣ነው ብለሃል፣በምኒሊክ፣በሃይለስላሰ፡ዘመነስ፣፣
  ሌላዉ፣ደግሞ የኢትዮዽያ፣ እና፣የ አርትራ ዉህደት፣ሃሳብህን፣ሲተይቕ ደነገጥክ፣ምነው፣ምን፣ያስፈራሃል ፣የመታውቃቸው፣ህዝቦች፣እኮ፣ናቸው።ባይመስለህ እንኩኣን፣ሁለቱንም፣ሃሳቦች፣ጠቀስ ኣድርገህ።ኣይዋሃዱም፣የሚለዉን፣መደምደሚያ፣ስለምትፈራ።ማቅረብ ትችላለህ፣ግን፣እኛ፣ኣኢትዮጵያውያን፣ይኸዉልህ፣መጽሃፍህን፣እናነባለን፣፣አንገዛለን፣ድግሞም፣የኛ፣ልጅ፣ነው፣ብለን እናስባለን፣ኣንተ፣፣ተኝተህ፣ኣታድርም ፣ለዚህች፣ሃገር ፣ቢሽፍቱን ትናፍቃለህ፣ሃብታም፣ሆነህ፣ቱሪስት፣ሆነህ ፣ልትንደላቀቅባት ፣ሚስጥሩ፣ምን ፣ይሆን፣ምን፣ኣስቀየምንህ፣፣፣፣ምን፣ይሆን

 8. ezra musse

  October 4, 2013 at 9:47 AM

  ተስፋዬ ገአብ የኤርትራና የኢትዮጵያውያን መስማማት ይረብሸዋል:: ምክንያቱም ግልፅ ነው:: ተስፋዬ ለኢትዮጵያ ሆነ ለኤርትራ አስቦ ሳይሆን የራሱ የሆነ የሕሊና ቁስል አላስቆም አላስተኛ እያለ ስለሚያውከው ነው::ተስፋዬ ኢትዮጵያ ውስጥ በነበረበት ጊዜ (ያኔ ደግሞ ለእነ በረከት እየሠለለ እና ሲያደገድግ በነበረበት ጊዜ) ማለትም ኤርትራዊያንን ከኢትዮጵያ እነ በረከት ሲያባርሩ ተስፋዬ ገ/አብ ዋና ተዋናኝ የነበረና የኤርትራዊያንን ስም በሊስት ይዞ እነ በረከት ለመመንጠር ሲነሱ የሚያውቃቸዉን እየጠቆመ ሲሰጥ የነበረ ለመሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው:

  ኢሳያስ አፈወርቂም ተስፋዬ አዲስ አበባ በቆየበት ጊዜ ሚናው ምን እንደነበር ጠንቅቆ በደንብ ያውቃል:: አሁን ግን ኢሳያስ ለጊዜው ተስፋዬ አስፈልጎታል:: ይሁንና ስለ ተስፋዬ ማንነት እያውቁም ቢሆን እነ ኢሣያስ አስፈልጓቸዋል:: ለዚህም ነው የተስፋዬ ገ/አብን ማንነት በተመለከተ ዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ ሰሞኑን ለድረ ገጾች በለቀቁት መረጃ ተስፋዬ ራሱ ለእነ ኢሳያስ በጻፈው የራሱ የእጅ ጽሁፍ መረጃ ላይ እንዳመልከተው “የእኔን ደካማ ጎን እና ባህሪ ታውቃላችሁ ግን….” ብሎ የራሱን ባኃሪ ገላጭ የሆነ ሰነድ ያስቀመጠው:: እናመሠግናል ዻኛ ወልደሚካኤል!

  ተስፋዬ ገአብ ኤርትራን ዛሬ ሞትኩልሽ የሚላት ቂ ቂ ቂ ቂ ቂ …. ዾሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት ዓይነት ነው እንጅ እውነቱ ግን ሌላ ነው:: ተስፋዬ ለሠራው ወንጀል እና ላጠፋው ነፍስ ኤርትራን አሁን ለጊዜው የሚሸሸግባት ጓዳው አደርጎ ስለሚያስብ እንጅ ለኤርትራዊያን ፈፅሞ አስቦ አይደለም::

  ኤርትራዊያንንማ ትናንትና ኢትዮጵያ ውስጥ በነበረበት ጊዜ እነ በረከትን ለማስደሰት ብሎ ከነ በረከት በላይ ኤርትራዊያንን ሲያሳደድ እንደነበር መረጃ ማቅረብ እንችላለን::

  ግን ዛሬ ተስፋዬ በተሰደደበት ዓለም አንዴ ኢትዮጵያዊ ነኝ አንዴ ምነትስ ነኝ ሲል እንዳልነበር አሁን ደግሞ በመረጃ ተደግፎ ኤርትራዊ መሆኑ ሲታወቅ ይሄንን መቀበል አቅቶት (ያሳፍረዋል ማለት ነው) ወዲያና ወዲህ በመርገጥ የሚይዘዉና የሚጨብጠዉን አሳጥቶታል:: ፍርጃ እኮ ነው ጎበዝ! የማነነት ቀውስ የሚፈጥረው የህይወት ዲስ-ኦርደር ማሳያው ይኽው የተስፋዬ ገአብ ባህሪ ነው:: መጥኔ እንደዚህ ከመሆን ያድነን!

  ተስፋዬ ገ/አብ ከፍተኛ የሆነ የማነነት ቀውስና የዝቅተኝነት ስሜትም ስለሚያንገዋልለው ይሄንን የዝቅተኘነት ስሜቱን ለመረሳት ወይም ለመሽፈን የሚጠቀምበት ፍቱን መድኃኒት ደግሞ ሁሉንም ነገር አውቃለሁ: ሁሉም ሰው ጓደኛዬ ነው: ሁሉም ነገር ከእኔ እውቀት ሞልቶ የፈሠሠና የተረፈ ነው በሚል የደንቆሮዎች ወይም የጆሮ ጠቢዎች ፍልስፍና ታጥሮ: ራሱን ሰማዬሰማያት ላይ ሰቅሏል::በመሆኑም ተስፋዬ ቂንጣሚንጢ ነገር ለመፃፍ ሲያስብ በትንሹም በትልቁ እርሱ በዘባረቀ ቁጠር ትልቅ ነኝ ለማለት (አዬ ይህ ዝቅተኝነት) ሊቀ ሊቃውንት ጌታቸው ኃይሌን እንደ ቆሎ ጓደኛው ያህል ስማቸዉን በማንሳት አቋጥሩኝ ዓይነት ጥሪ ያቀርባል:: ከዚህ በላይ የማነነት ቀውስ መገለጫ ምን አለ?
  ተስፍሽ እንደገና ሰው ለመሆን ከፈልግህ አሁንም በራስህ ቁም:: ዘወትር ብር ላሳየህ ሁሉ አትደፋ:: 10:000 ኢሮም ሆነ ሌላ ተጨማሪ ብር ያንተን የማንነት ቀውስ አያጥብም:: ቀውስህን ለማጠብ ከፈልግህ ከሕሊናህ ጋር ታረቅ ያኔ አዲዎስ ዝቅተኘነት ብልህ ትቆማለህ ተስፍሽ!